የጥርስ መቦርቦር
የጥርስ መቦርቦር (Dental caries) የጥርስ መቦርቦር (Dental caries) ስኳርን ወደ አሲድ መቀየር የሚችሉ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን (bacteria) የጥርስን ንጣፍን ሲያጠቁ የሚፈጠር የጥርስ በሽታ ነው፡፡ ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቀስ በቀስ የጥርስ ህመም ፣ ቁስለት አልፎ ተርፎም የጥርስ መበስበስ ያስከትላል ፡፡ ይህ በሽታ በሁሉም ዕድሜ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከሌላው እድሜ በተለየ ህፃናት ለጥርስ መቦርቦር የተጋለጡ ናቸው የጥርስ መቦርቦር በምን ምክንያት ይፈጠራል? የጥርስ መቦርቦርን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች በምግብ እና መጠጥ ውስጥ ካለው ስ...