Learning materials for your health  Learn

Our Blog

ሲጋራ የማጨስ ጉዳቶች (Effects of cigarette smoking )

ሲጋራ የማጨስ ጉዳቶች (Effects of cigarette smoking ) ሲጋራ ማጨስ ለበርካታ አካላዊ እና ስነ አእምሮአዊ  በሽታዎች መከሰት መንስኤ ነው። በአለም የጤና ድርጅት ጥናት መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ሲጋራ ያጨሳል።  ሲጋራ በውስጡ ኒኮቲን የተባለ ንጥረ ነገር አለው። ኒኮቲን የአንጎልን ነርቭ አስተላላፊዎችን በማወክ  ጊዜያዊ የሆነ የደስታ ስሜት እዲፈጠር የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው።  ሲጋራን የሚያጨሱ ሰዎች ተመሳሳይ የሆነ የደስታን ስሜት ለማምጣት የሚወስዱትን የኒኮቲን መጠን መጨመር ይኖርባቸዋል፤ ከዚህ የተነሳ በዛ የአለ ሲጋራን ለማጨስ ይገደዳሉ።  በተጨማሪም ማ...

ሲጋራ የማጨስ ጉዳቶች

ሲጋራ የማጨስ ጉዳቶች (Effects of cigarette smoking ) ሲጋራ ማጨስ ለበርካታ አካላዊ እና ስነ አእምሮአዊ  በሽታዎች መከሰት መንስኤ ነው። በአለም የጤና ድርጅት ጥናት መሰረት በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ሲጋራ ያጨሳል።  ሲጋራ በውስጡ ኒኮቲን የተባለ ንጥረ ነገር አለው። ኒኮቲን የአንጎልን ነርቭ አስተላላፊዎችን በማወክ  ጊዜያዊ የሆነ የደስታ ስሜት እዲፈጠር የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው።  ሲጋራን የሚያጨሱ ሰዎች ተመሳሳይ የሆነ የደስታን ስሜት ለማምጣት የሚወስዱትን የኒኮቲን መጠን መጨመር ይኖርባቸዋል፤ ከዚህ የተነሳ በዛ የአለ ሲጋራን ለማጨስ ይገደዳሉ።  በተጨማሪም ማ...

የጥርስ መቦርቦር

የጥርስ መቦርቦር  (Dental caries)   የጥርስ መቦርቦር (Dental caries) ስኳርን ወደ አሲድ መቀየር የሚችሉ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን (bacteria) የጥርስን ንጣፍን ሲያጠቁ የሚፈጠር የጥርስ በሽታ ነው፡፡   ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቀስ በቀስ የጥርስ ህመም ፣ ቁስለት አልፎ ተርፎም የጥርስ መበስበስ ያስከትላል ፡፡ ይህ በሽታ በሁሉም ዕድሜ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከሌላው እድሜ በተለየ ህፃናት ለጥርስ መቦርቦር የተጋለጡ ናቸው   የጥርስ መቦርቦር በምን ምክንያት ይፈጠራል?  የጥርስ መቦርቦርን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች በምግብ እና መጠጥ ውስጥ ካለው ስ...

ከማኅፀን ውጪ የሚከሠት እርግዝና  (Ectopic Pregnancy)

ከማኅፀን ውጪ የሚከሠት እርግዝና  (Ectopic Pregnancy)  ከማኅፀን ውጪ እርግዝና  የሚከሠተው፤  ከማኅፀኑ ውስጠኛው ግድግዳ በውጭ በኩል ሌላ የሴት መራቢያ አካሎች ወይም የሆድ ክፍል ውስጥ ትክለተ ፅንስ ሲካሄድ ነው። ዘጠና ስምንት በመቶ የሚሆኑት ከማኅፀን ውጭ የሚፈጠሩ እርግዝናዎች  በእንቁላል መተላለፊያ ቱቦ (fallopian tube) ውስጥ ይከሠታሉ።  አልፎ አልፎ በማደግ ላይ ያለው ፅንስ  በማኅፀን በር ጫፍ (cervix)፣ በእንቁልጢ (ovary) ወይም በሆድ እና በተለያዩ ቦታዎች ላይ ሊከሠት ይችላል ፡፡ መንታ እርግዝና በሚኖርበት ወቅት፤  አንዱ  ፅንስ በትክክል  በማኅፀን ውስጠኛው ግድግዳ ላይ ትክለት ሲያካሂድ፣ ሌላኛው ደግሞ ከማኅፀን ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ያልተለመደ ክሥተት ቢሆንም የመሃንነት ሕክምና በሚወስዱ ሴቶች ላይ የመከሠት...

ስርቅታ (Hiccups)

ስርቅታ (Hiccups)    ስርቅታ ደረትን ከሆድ የሚለየው ዋና የመተንፈሻ ጡንቻ (Diaphragm) በድንገት ሲኮማተር ይከሠታል፡፡  ይህ የጡንቻ መኮማተር አየር ወደ ውስጥ እንድናስገባ እና የድምፅ ሳጥን እንዲዘጋ ያደርጋል።  በዚህን ጊዜም ”ስርቅ” የሚለው ድምፅ ወይም ስርቅታ ይፈጠራል።    የስርቅታ መንሥኤዎቹ ምንድናቸው?   በ 48 ሰዓታት ውስጥ የሚጠፋ ስርቅታን የሚያመጡ መንሥኤዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ። በአንድ ጊዜ ከመጠን በላይ ምግብ መመገብ የአልኮሆል  መ...

በጨቅላ ሕፃናት ላይ የሚከሠት የዐይን በሽታ (Ophthalmia neonatorum)

በጨቅላ ሕፃናት ላይ የሚከሠት የዐይን በሽታ  (Ophthalmia neonatorum) በተወለዱ በመጀመሪያዎቹ 30 ቀናት ላይ የሚከሠት የጨቅላ ሕፃናት የዐይን ኢንፌክሽን ነው። አብዛኞቹ በጤና ተቋማት ውስጥ የሚወለዱ ሕፃናት ይህ የዐይን በሽታ እንዳያጋጥማቸው ሲባል በተወለዱ በሰዓታት ውስጥ የዐይን ጠብታ ይደረግላቸዋል። ይህ በሽታ በሥርዓት ከአልታከመ የዐይን ብርሃን እስከማጥፋት ይደርሳል።  የበሽታው መንሥኤዎች       የጨቅላ ሕፃናት የዐይን በሽታ መንሥኤዎች   ባክቴሪያዎች  በአብዛኛው ጊዜ በጨቅላ ሕፃናት ላይ የዐይን በሽታ ያስከትላሉ፡፡     ...

ለምፅ (vitiligo)

 ለምጽ (vitiligo) ለምጽ በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ የቆዳ ቀለም እንዲነጣ የሚያደርግ በሽታ ነው፡፡ በዚህ በሽታ የተጠቃው የአካል ክፍልም በጊዜ ሂደት ቀስ በቀስ ስፋቱን እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህ እክል ከውጭኛው ቆዳ በተጨማሪም ፀጉር እና የአፍ የውስጥ ክፍልን ያጠቃል፡፡ በመደበኛነት የፀጉር እና የቆዳ ቀለም የሚወሰነው ሜላኒን (Melanin) በሚባል ንጥረ ነገር ነው፡፡ ለምጽ በአለባቸው ሰዎች ላይ ይህን ሜላኒን (Melanin) የሚባለውን ንጥረ ነገር የሚያመርቱ ሕዋሶች (melanocytes) በተገቢው እየሠሩ አይደለም ወይም ከእነ ጭራሹ የሉም ማለት ነው፡፡  ለምጽ ሁሉንም የቆዳ ዓይነቶች ያጠቃል፡፡ ነገር ግን ጥቁር ቆዳ በአላቸው ሰዎች ላይ የበለጠ በግልፅ ይታያል፡፡ በሽታው ለሕይወት አስጊ ወይም ተላላፊ አይደለም፡፡ ለምጽ በማንኛውም ዕድሜ ክልል ውስጥ ሊጀምር ይችላ...

ጭርት (Ringworm)

ጭርት (Ringworm)  ጭርት በፈንገስ (fungus) ምክንያት የሚመጣ በቆዳ ላይ የሚከሠት የኢንፌክሽን ዓይነት ነው።  መገለጫውም ክብ የሆነ ዳር ዳሩ ቀይ እና መሐሉ የዳነ የሚመስል ሲሆን የማሳከክ ስሜት ሊኖረው ይችላል። ጭርት ከአንዱ ሰው ወደ ሌላ ሰው በቆዳ ለቆዳ ንክኪ በቀላሉ ይተላለፋል።    ምልክቶቹ    ጭርት ቅርፊታማና ጠፍጣፋ ሲሆን አንዳንዴ ቀላ ያለ እና የሚያሳከክ ቁሰለት፣ ክብ ሆኖ ጠርዝ ጠርዙ ቀይ መልክ የሚኖረው እና ቀስ በቀስ የሚሰፋ የቆዳ ላይ ሕመም ነው።   የመተላለፊያ መንገዶች  

scroll top