Learning materials for your health  Learn

Our Blog

የአስም በሽታ

የአስም በሽታ እየተደጋገመ የሚመጣ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ፣ የመተንፈሻ ቱቦ እና የሳምባ ሕመም ነው።  በሽታው የአየር ቱቦዎችን በማጥበብና በማስቆጣት መተንፈስን ከባድ ያደርገዋል፡፡  የአስም በሽታ በበለፀጉት አገራት የበለጠ ቢከሠትም፤ አሁን አሁን ግን በታዳጊ አገሮችም እየጨመረ ይገኛል። በዓለማችን 10 - 12% የሚሆኑት ጎልማሳዎችና እና 15% የሚሆኑት ሕፃናት  በዚህ በሽታ ይጠቃሉ። ወንዶች ሕፃናት ከሴት ሕፃናት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። በወጣቶች ላይ ግን ሁለቱም እኩል ተጋላጭ ሲሆኑ፤ ዕድሜያቸው ከ 40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ይጠቃሉ።  ለአስም በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? በቤተሰብ የአስም ሕመም ከአለ፤ በልጆች ላይ  የቆዳ ወይም ማንኛውም ዓይነት የመተንፈሻ አካላት አለርጂ ከአለ ፤ ታማሚው  አዋቂ ከሆነ...

ኮሌስትሮል ምንድን ነው? በጤና ላይ ያለው ጥቅምና ጉዳትስ?

ኮሌስትሮል በደም ውስጥ የሚገኝ ስብ መሳይ ንጥረ ነገር ሲሆን መጠኑ ይለያይ እንጅ በሁሉም ሰው ደም ውስጥ ይኖራል። ሰውነታችን ኮሌስትሮልን ከየት ያገኛል? አብዛኛውን ጊዜ ጉበት ሰውነታችን የሚፈልገውን የኮሌስትሮል መጠን ማምረት ይችላል። በተጨማሪም ኮሌስትሮልን ከምንመገበው ምግብ ውስጥ ማግኘት እንችላለን፡፡  የዶሮ እና የከብት ሥጋ እንዲሁም እንደ እንቁላል እና ወተት ያሉ የእንስሳት ተዋጽኦዎች ኮሌስትሮልን ይይዛሉ፡፡ ኮሌስትሮል ለጤናችን ምን ጥቅም አለው? ኮሌስትሮል ለጤናችን የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣል። እነዚህም፤ የሕዋሳትን (Cell) ሽፋኖች እና አወቃቀሮች ይሠራል። ይህም ሕዋሳትን በመጠበቅ፣ ቅርፃቸውን በመለዋወጥ የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን እንዲያስገቡ እና የሙቀት መጠንን እንዲቆጣጠሩ ይረዳቸዋል። ሰውነታችን እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ሆርሞኖችን ለመሥራት ኮሌስትሮልን ይጠቀማል፡፡ ለም...

scroll top