Learning materials for your health  Learn

Our Blog

አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) በሽታ ህመም ያለው በቆዳ ላይ የሚወጣ ሕመም ያለው ሽፍታ ነው፡፡ሲሆን ቫሪሴላ -ዞስተር (Varicella zoster) በሚባል ቫይረስ አማካኝነት ይከሠሰታል።    ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 20 በመቶ የሚሆነው የዓአለማችን ሕህዝብ በዚህ በሽታ ይጠቃል፡፡ ይህ ሕህመም የሚከሠሰተው አስቀድሞ ጉድፍ (Chickenpox) በተያዙ ሰዎች ላይ ነው፡፡ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች በጉድፍ በሽታ ተይዘው እንደነበረ ላያውቁ ወይም ላያስታውሱ ይችላሉ።  አልማዝ ባለጭራ  (Herpes zoster) እንዴት ይከሠሰታል?   ቫሪሴላ -ዞስተር ሰዎች በጉድፍ እንዲታመሙ የሚያደርግ ቫይረስ  ሲሆን፤ ሕህመሙ ከአካለፈ በኋላ ይህ ቫይረስ በአከርካሪ...

አጠቃላይ የጭንቀት በሽታ

አጠቃላይ የጭንቀት በሽታ (Generalized anxiety disorder) በሕይወት ስንኖር በአንዳንድ አጋጣሚዎች የተነሣ መጠነኛ የሆነ መጨነቅ ወይም መረበሽ ሊገጥመን ይችላል። ይህ የተለመደ እና ጤናማ ነው። ነገር ግን አጠቃላይ የጭንቀት በሽታ (GAD) የአለባቸው ሰዎች ከእውነታው በራቀ ወይም ከሚገጥማቸው ችግር ጋር በአልተመጣጠነ መልኩ ፍርሃት እና ጭንቀት ይታይባቸዋል።  እነዚህ ሰዎች አብዝተው ስለ ጤና፣ ገንዘብ፣ ቤተሰብ፣ ሥራ ወይም ትምህርት ይጨነቃሉ። መረበሻቸውንም በቀላሉ ማቆም አይችሉም ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መካከለኛ ዕድሜ ላይ ያሉትን ሰዎች የሚያጠቃ ሲሆን፤ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በዚህ በሽታ ይያዛሉ። በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ ውስጥ ብቻ ወደ 2 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች የዚህ በሽታ ሰለባ ናቸው። የበሽታው ምልክቶች በተፈጥሮ የመምጣትና የመሔድ ባሕርይ አላቸው። በተጨማሪም...

የቤል ፓልሲ    

መጋኛ ?  የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)                       የቤል ፓልሲ በተለምዶ ‹‹መጋኛ›› እየተባለ የሚጠራው በሽታ የፊት ጡንቻዎችን የሚቆጣጠረው ነርቭ (facial nerve) ጉዳት ሲደርሰበት ወይም ሙሉ በሙሉ መሥራት ሲያቆም የሚከሠት ነው፡፡ ይህ በሽታ የፊት ጡንቻዎች እንዲዳከሙ ወይም ሽባ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ፡፡ የቤል ፓል...

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ 

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ  (HIV exposed neonate) - ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ (በደሟ ውስጥ) የአለባት አንዲት እናት በእርግዝናዋ ወቅት፣ በምጥና በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ጡት በምታጠባበት ጊዜ ልጇ ለኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ኢንፌክሽን የተጋለጠ ይሆናል።     - ስለዚህም ሕፃኑ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ በጤና ተቋም ውስጥ ክትትል ይደረግለታል።  ለመጀመሪያዎቹ 6 ወራት በየወሩ ከዚያም በየ3 ወሩ ይቀጥላል፡፡ የሚደረጉት የሕክምና ክትትሎች የሚከተሉት ናቸው :: - አጠቃላይ የጤና ምርመራ  - አካላዊና ሥነ እእምሯዊ ዕድገት ክትትል  - የአመጋገብ ትምህርት፣ ክትባት መስጠት  - የተጓዳኝ በሽታ መከላከያ መድኃኒት( cotrimoxazole Preve...

ከምጥ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ

ከምጥ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ (Premature rupture of membranes /PROM/) ብዙውን ጊዜ የሽርት ውሃ የሚፈስሰው ምጥ ከጀመረ በኃላ ቢሆንም፤ ከ 8 እስከ 10 % የሚሆኑ ነፍሰ ጡሮች ላይ ምጥ ከመጀመሩ በፊት ሊፈስስ ይችላል። ይህም ፕሮም ይባላል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ እርግዝናው 37 ሳምንት ከመሆኑ በፊት ይከሠታል። ይህም ማለት ፅንሱ ሙሉ በሙሉ ዕድገቱን ከመጨረሱ በፊት ምጥ እንዲጀምር ምክንያት ይሆናል። ለዚህም ነው አንድ ሦስተኛ ለሚሆኑት ያለጊዜያቸው ለሚወለዱ ሕፃናት እንደ ምክንያት የሚቀርበው ከ37 ሳምንት በፊት የሚፈጠረ የሽርት ውሃ መፍሰስ የሆነው። ከፕሮም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ብዙ ችግሮች አሉ። ይህም ለእናትዬዋም ሆነ አዲስ ለተወለደው ሕፃን የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።  ፕሮምን ሊያስከትሉ የሚችሉ አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው? ከዚህ ቀደም ያለ እ...

ከፍተኛ የቅሪት ትውከት

ከፍተኛ የቅሪት ትውከት (Hyperemesis gravidarum) በእርግዝና ወቅት ከ 50 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እናቶች የተወሰነ የማቅለሽለሽ እና የትውከት ስሜት ይኖራቸዋል። ይህ ብዙውን ጊዜ ከ 5 እስከ 18 ሳምንታት በአሉት የእርግዝና ወቅቶች ላይ የሚከሠት ነው፡፡   ከፍተኛ የቅሪት ትውከት እና የቅሪት ትፋት ልዩነታቸው ምንድነው? የቅሪት ትፋት (Morning sickness)  ይህ አብዛኛውን ጊዜ በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የሚከሠት መለስተኛ የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ  ስሜት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ከ16 ወይም ከ18 የእርግዝና ሳምንታት በኋላ ምልክቶቹ እየተሻሉ ይሄዳሉ።  ከፍተኛ የቅሪት ትውከት (Hyperemesis gravidarum) ከፍተኛ የ...

የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች በሴቶች ላይ

የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች በሴቶች ላይ ብዙ ሴቶች ከወሲብ (ግብረ ሥጋ ግኙነት) ጋር የተያያዙ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ይታያሉ። ይህም በትዳራቸው ላይ አሉታዊ የሆነ ጫና እንዳለው ሳይታለም የተፈታ ሐቅ ነው። በዚህ ጽሑፍ በሴቶች ላይ ስለሚፈጠሩ የተለያዩ የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች፣ ምክንያቶቻቸውና መፍትሔ እናብራራለን፤ ይከታተሉን። የተለያዩ ዓይነት ከወሲብ (ግብረ ሥጋ ግኙነት) ጋር የተያያዙ ችግሮች በሴቶች ላይ ሊታዩ ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ በብዛት የሚታዩት፤ ፍላጎት ማጣት  ወሲባዊ መነቃቃት አለመኖር (unable to become aroused) መጨረስ አለመቻል (difficult to achieve orgasm) እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሕመም መሰማት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ምልክቶች ከትዳር አጋር...

በእርግዝና ወቅት የአስም በሽታ

በእርግዝና ወቅት የአስም በሽታ አስም በእርግዝና ወቅት ሳንባን ከሚያጠቁ በሽታዎች ዋነኛው ሲሆን፤  ከ 3 እስከ 8 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች ላይ ይታያል፡፡ አብዛኛዎቹ ነፍሰ ጡር ሴቶች የእርግዝና ለውጦች በአስማቸው ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ያሳድር ይሆን? እና ለአስም  የሚደረጉ ሕክምናዎች ፅንሱን ይጎዱ ይሆን? በማለት ይጨነቃሉ፡፡ ተገቢው የአስም ሕክምና የተደረገላቸው ሴቶች በቀላሉ ምልክቶችን መቆጣጠር እና ጤናማ ልጅ መውለድ ይችላሉ፡፡  📌በደንብ ቁጥጥር ያልተደረገበት የአስም በሽታ፣ የአስም በሽታን ለመቆጣጠር የሚሰጡት መድኃኒቶችን በመውሰድ  ከሚፈጠረው አደጋ እጅግ ይበልጣል፡፡ አስም ያለባቸው ሴቶች ነፍሰ ጡር ከመሆናቸው በፊት ስለ ሁኔታቸው ከጤና ባለሙያ ጋር መወያየት አለባቸው፡፡ በአጋጣሚ ነፍሰ ጡር መሆናቸውን ያወቁ ሴቶች የአስም መድኃኒታቸውን  ሳያቋርጡ መቀጠል አለባቸው፡፡ በድንገት የአስም መድኃኒቶችን ማቆም ለእር...

scroll top