Learning materials for your health  Learn

Our Blog

የቤል ፓልሲ    

መጋኛ ?  የቤል ፓልሲ (Bell’s Palsy)                       የቤል ፓልሲ በተለምዶ ‹‹መጋኛ›› እየተባለ የሚጠራው በሽታ የፊት ጡንቻዎችን የሚቆጣጠረው ነርቭ (facial nerve) ጉዳት ሲደርሰበት ወይም ሙሉ በሙሉ መሥራት ሲያቆም የሚከሠት ነው፡፡ ይህ በሽታ የፊት ጡንቻዎች እንዲዳከሙ ወይም ሽባ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ፡፡ የቤል ፓል...

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ 

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ  (HIV exposed neonate) - ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ (በደሟ ውስጥ) የአለባት አንዲት እናት በእርግዝናዋ ወቅት፣ በምጥና በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ጡት በምታጠባበት ጊዜ ልጇ ለኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ኢንፌክሽን የተጋለጠ ይሆናል።     - ስለዚህም ሕፃኑ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ በጤና ተቋም ውስጥ ክትትል ይደረግለታል።  ለመጀመሪያዎቹ 6 ወራት በየወሩ ከዚያም በየ3 ወሩ ይቀጥላል፡፡ የሚደረጉት የሕክምና ክትትሎች የሚከተሉት ናቸው :: - አጠቃላይ የጤና ምርመራ  - አካላዊና ሥነ እእምሯዊ ዕድገት ክትትል  - የአመጋገብ ትምህርት፣ ክትባት መስጠት  - የተጓዳኝ በሽታ መከላከያ መድኃኒት( cotrimoxazole Preve...

ከማኅበረሰቡ የአፈነገጠ የሰብእና ቀውስ 

ከማኅበረሰቡ የአፈነገጠ የሰብእና ቀውስ  (Antisocial Personality Disorder) ከማኅበረሰቡ የአፈነገጠ (አንቲ ሶሻል) የሰብእና ቀውስ (Antisocial Personality Disorder) በልጅነት ወይም በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚጀምር እና በብዙ የሕይወት ዘርፎች ውስጥ የሚገለጽ የሰብእና ቀውስ ነው፡፡ ይህ የሥነ ልቦና ሕመም በዋነኛነት የሚገለጸው በሚከተሉት ነጥቦች ነው። እነዚህም የማኅበራዊ ሐላፊነት መጓደል፤ ለማኅበረሰቡ በጎ ባህል፣ ወግ፣ ሥርዓት፣ ሞራል፣ ሥነ ምግባር አለመገዛት፤ ማንኛውንም ሕግና ደንብ አለማክበር፤ የጥፋተኝነት (የፀፀት) ስሜት አለመኖር፡፡ እንዲሁም የሰውን ሕመም፣ ጉዳት፣ ችግር ለመረዳት መቸገር ወዘተ…የሚታዩ መገለጫዎች ናቸው። አብዛኞቹ...

እርግዝና እና ኤች አይ ቪ

እርግዝና እና ኤች አይ ቪ (MTCT & PMTCT) ለሕፃናት በኤች.አይ.ቪ. ኢንፌክሽን መያዝ ዋነኛ መንሥኤ ከእናት ወደ ልጅ የቫይረሱ መተላለፍ ሲሆን ይህም ከሚከተሉት በአንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል።  በቅድመ ወሊድ፣ በምጥ እና በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ በጡት ማጥባት ወቅት ሊሆን ይችላል።  ያለ ምንም ሕክምና እርዳታ የመተላለፍ ዕድሉ ከ 15 - 45% ሲሆን ተገቢውን የሕክምና እርዳታ ከተደረገ ግን የመተላለፍ ዕድሉ ከ 5% በታች ሊቀንስ ይችላል፡፡ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ እርግዝና  የኤች.አይ.ቪን ሕመም አያባብስም፤ ወይም በኤች አይ ቪ የመሞትን አደጋን አይጨምርም። እንዲሁም አብዛኞቹ የኤች. አይ. ቪ ሕክምናዎች በሚወለደው ሕፃን ላይ የሚያመጡት የጤና እክል አይኖርም።  

ከምጥ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ

ከምጥ በፊት የሽርት ውሃ መፍሰስ (Premature rupture of membranes /PROM/) ብዙውን ጊዜ የሽርት ውሃ የሚፈስሰው ምጥ ከጀመረ በኃላ ቢሆንም፤ ከ 8 እስከ 10 % የሚሆኑ ነፍሰ ጡሮች ላይ ምጥ ከመጀመሩ በፊት ሊፈስስ ይችላል። ይህም ፕሮም ይባላል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ እርግዝናው 37 ሳምንት ከመሆኑ በፊት ይከሠታል። ይህም ማለት ፅንሱ ሙሉ በሙሉ ዕድገቱን ከመጨረሱ በፊት ምጥ እንዲጀምር ምክንያት ይሆናል። ለዚህም ነው አንድ ሦስተኛ ለሚሆኑት ያለጊዜያቸው ለሚወለዱ ሕፃናት እንደ ምክንያት የሚቀርበው ከ37 ሳምንት በፊት የሚፈጠረ የሽርት ውሃ መፍሰስ የሆነው። ከፕሮም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ብዙ ችግሮች አሉ። ይህም ለእናትዬዋም ሆነ አዲስ ለተወለደው ሕፃን የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።  ፕሮምን ሊያስከትሉ የሚችሉ አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው? ከዚህ ቀደም ያለ እ...

ከፍተኛ የቅሪት ትውከት

ከፍተኛ የቅሪት ትውከት (Hyperemesis gravidarum) በእርግዝና ወቅት ከ 50 እስከ 90 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰ ጡር እናቶች የተወሰነ የማቅለሽለሽ እና የትውከት ስሜት ይኖራቸዋል። ይህ ብዙውን ጊዜ ከ 5 እስከ 18 ሳምንታት በአሉት የእርግዝና ወቅቶች ላይ የሚከሠት ነው፡፡   ከፍተኛ የቅሪት ትውከት እና የቅሪት ትፋት ልዩነታቸው ምንድነው? የቅሪት ትፋት (Morning sickness)  ይህ አብዛኛውን ጊዜ በእርግዝና የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የሚከሠት መለስተኛ የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ  ስሜት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ከ16 ወይም ከ18 የእርግዝና ሳምንታት በኋላ ምልክቶቹ እየተሻሉ ይሄዳሉ።  ከፍተኛ የቅሪት ትውከት (Hyperemesis gravidarum) ከፍተኛ የ...

የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች በሴቶች ላይ

የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች በሴቶች ላይ ብዙ ሴቶች ከወሲብ (ግብረ ሥጋ ግኙነት) ጋር የተያያዙ የተለያዩ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ይታያሉ። ይህም በትዳራቸው ላይ አሉታዊ የሆነ ጫና እንዳለው ሳይታለም የተፈታ ሐቅ ነው። በዚህ ጽሑፍ በሴቶች ላይ ስለሚፈጠሩ የተለያዩ የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች፣ ምክንያቶቻቸውና መፍትሔ እናብራራለን፤ ይከታተሉን። የተለያዩ ዓይነት ከወሲብ (ግብረ ሥጋ ግኙነት) ጋር የተያያዙ ችግሮች በሴቶች ላይ ሊታዩ ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ በብዛት የሚታዩት፤ ፍላጎት ማጣት  ወሲባዊ መነቃቃት አለመኖር (unable to become aroused) መጨረስ አለመቻል (difficult to achieve orgasm) እና በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሕመም መሰማት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ምልክቶች ከትዳር አጋር...

በወንዶች ላይ የሚከሠቱ የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች

በወንዶች ላይ የሚከሠቱ የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች የወሲብ (ተራክቦ) ችግሮች የሚባሉት ማንኛውም በወሲብ የሚገኘውን እርካታ የሚቀንሱ አካላዊም ሆነ ሥነልቦናዊ ችግሮች ናቸው። በወንዶች ላይ የሚከሠቱ የወሲብ ችግሮች በማንኛውም ዕድሜ ሊከሠቱ የሚችሉ ቢሆኑም በዋነኝነት የሚከሠቱት ግን ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ ነው። በወንዶች ላይ የሚከሠቱ የወሲብ ችግሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ። ዝቅተኛ የወሲብ ፍላጎት በወሲብ ጊዜ የብልት አለመቆም ወይም እንደቆመ መቆየት አለመቻል ቶሎ መጨረስ (ቶሎ ኦርጋዝም ላይ መድረስ) በወሲባዊ ግንኙነት ጊዜ መርጨት (መጨረስ) አለመቻል ወይም ቆይቶ መጨረስ   በወንዶች ላይ የወሲብ ችግሮች እንዲከሠቱ የሚያደርጉ ነገሮች ምንድን ናቸው? የወሲብ (ተራክቦ) ች...

scroll top