Learning materials for your health  Learn

Our Blog

ሄፕታይተስ ኤ (Hepatitis A)

ሄፕታይተስ ኤ በሽታ፤ ሄፕታይተስ ኤ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ የጉበት በሽታ ነው፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2018 በአሜሪካ ውስጥ በአጠቃላይ 12,474 የሄፕታይተስ ኤ ተጠቂዎች እንደሚገኙ ሪፖርት ተደርጓል፡፡ የበሽታው መጠን ከ 1995 ወደ 2011 እ.ኤ.አ. በአሜሪካ ከ 95 በመቶ በላይ ቀንሷል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ግን አሁንም በሽታው በስፋት ይገኛል። ሄፕታይተስ ኤ ቫይረስ የሚሰራጨው እንዴት ነው? ሄፕታይተስ ኤ (Hepatitis A) በሽታ አምጭ የሆነው ቫይረስ ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ይተላለፋል። ቫይረሱ በዋነኛነት በበሽታው በተጠቃ ሰው ሰገራ እና ደም ውስጥ ይገኛል፡፡  ማንኛውም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሰገራ ጋር ንክኪ ያለው ነገር ወደ አፍ ከገባ በሽታው ይተላለፋል። ለዚህም ነው ዋነኛው የመተላለፊያ መንገዱ የተበከለ ምግብ መመገብ እና የተበከለ ውሃ መጠጣት የሆነው። የበሽታው አጋላጭ ሁኔታዎች ምን ምንድን ናቸው? ...

የኪንታሮት በሽታ (hemorrhoids)

ኪንታሮት በታችኛው የፊንጢጣ ክፍል ያሉ የደም መላሽ ደም ሥሮች ሲሰፉ ወይም ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ነው። በሁሉም የዕድሜ ክልል እና በሁለቱም ፆታዎች ላይ የሚከሠት ቢሆንም በብዛት ከ 45 እስከ 65 ዓመት ባሉት ላይ ይታያል።   ኪንታሮት አብዛኛውን ጊዜ ከባድ የጤና ችግር የማያመጣ ቢሆንም፤ ምቾት የሚነሣ እና የሚረብሽ ስሜት ይኖረዋል ፡፡  የኪንታሮት ዓይነቶች ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoids) ፡- በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ  ሲሆን  ሕመምም አለው ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoids) ፦ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ  ሲሆን  ሕመም  የለውም ውስጣዊ ኪንታሮት አራት ደረጃዎች አሉት፡፡ የኪንታሮት ምልክቶች የ...

የጡት ካንሰር (Breast Cancer)

የጡት ካንሰር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ዕድገት እና በጡት ኅብረ ሕዋስ ላይ በሚከሠቱ ለውጦች ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሴቶች ላይ ሁለተኛው የተለመደ የካንሰር መንሥኤ ሲሆን በማደግ ላይ በአሉ ሃገራትም  እየጨመረ የመጣ  አሳሳቢ የጤና እክል ነው።  እ.ኤ.አ. በ 2018 የተደረገ ጥናት ወደ 2.1 ሚሊዮን  የሚጠጉ ሴቶች የጡት ካንሰር በሽታ እንደተገኘባቸው ያሳያል።  ከ 8 ሴቶች መካከል አንዷ (13%) በሕይወት ዘመኗ  በጡት ካንሰር በሽታ የመያዝ ዕድል ሲኖራት፤ ከ 39 ሴቶች መካከል አንዷ (3%) ደግሞ በዚህ በሽታ ምክንያት ለሞት ትዳረጋለች፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እ.ኤ.አ በ2018 እንደአወጣው  ዘገባ፣ በኢትዮጵያ  ውስጥ የጡት ካንሰር  በፈጣን ሁኔታ እያደገ ነው፡፡ ከሁሉም የካንሰር ዓይነቶች 22.6 በመቶ የሚሆነውን የሚያካትት ቀዳሚ የካንሰር መንሥኤም ሲሆን ከ100 ሺሕ ሕዝቦቿ  ውስጥ 22.9 የሚሆኑ...

የኮቪድ 19 በሽታ ምንነት እና ምልክቶች

ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ የተለያዩ ቫይረሶች ስብስብ ነው። ኮሮና የተባሉበትም ምክንያት፤ ከእንግሊዘኛው “ክራውን” ከሚለው ቃል በመነሣት በቫይረሶቹ የውጪ ክፍል ላይ ”ዘውድ” የመሰለ ከሰውነት ኅብረ ሕዋስ ጋር የሚጣበቅ ፕሮቲን ስለአላቸው ነው።  የኮቪድ 19 ሕመምተኞች የሚያሳዩት ብዙ ዓይነት ምልክቶች፣ ከቀላል ምልክቶች እስከ ከባድ ሕመም ድረስ ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ ግን ሕመምተኞች በቫይረሱ ​​ከተያዙ ከ 2 - 14 ቀናት በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶችን ያሳያሉ ፡፡   ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት ሳል፣ የመተንፈስ ችግር ድካም፣ የጡንቻ ሕመም፣ ራስ ምታት  መቅመስ እና ማሽተት አለመቻል ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ፣ ተቅማጥ ...

የኮቪድ 19 በሽታ

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው? ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ የተለያዩ ቫይረሶች ስብስብ ነው። ኮሮና የተባሉበትም ምክንያት፤ ከእንግሊዘኛው “ክራውን” ከሚለው ቃል በመነሣት በቫይረሶቹ የውጪ ክፍል ላይ ”ዘውድ” የመሰለ ከሰውነት ኅብረ ሕዋስ ጋር የሚጣበቅ ፕሮቲን ስለአላቸው ነው። የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ዓይነቶች? የሳይንስ ሊቃውንት ኮሮና ቫይረስን አልፋ (alpha)፣ ቤታ (beta)፣ ጋማ (gamma) እና ዴልታ (delta) ተብለው በሚጠሩት አራት ንኡስ ክፍሎች ከፋፍለውታል። ከእነዚህ ቫይረሶች መካከል ሰባቱ ሰዎችን ሊያጠቋቸው ይችላሉ፡፡  📌 229 E (አልፋ) 📌 NL 63 (አልፋ) 📌 OC 43 (ቤታ) 📌 HKU 1 (ቤታ) 📌 MERS Cov በመካከለኛው ምሥራቅ የዓለም ክፍል አካባቢ በመተንፈሻ አካ...

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት

ኩላሊት ሥራው ምንድነው? ኩላሊት በመደበኛነት ደምን ያጣራል፡፡ እንዲሁም በደም ውስጥ ያሉትን ከመጠን በላይ ጨው፣ ውሃ እና አላስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል፡፡  አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ማለት፤ ኩላሊት በድንገት ሥራውን እየቀነሰ ሲሄድ ወይም  በፍጥነት ሥራውን ሲያቆም  ማለት ነው፡፡ ይህም በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ጨው፣ ውሃ እና የማያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች እንዲጠራቀሙ ያደርጋል። አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት በአግባቡ ሕክምና ከተደረገለት የኩላሊት እጥበት ደረጃ ላይ  እንኳን ቢደርስ ኩላሊት መልሶ ሙሉ ለሙሉ ሊያገግም ይችላል። አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት በጊዜ ሕክምና ከአልተደረገለት እስከ ኩላሊት ሥራ ማቆም ሊደርስ ይችላል። አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት መንሥኤዎች ከተለመደው የደም ዝውውር መጠን ያነሰ ደም ወደ ኩላሊት መፍሰስ

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች ምንድናቸው?

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ማለት፤ ኩላሊት በድንገት ሥራውን እየቀነሰ ሲሄድ ወይም  በፍጥነት ሥራውን ሲያቆም  ማለት ነው፡፡ ይህም በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ጨው፣ ውሃ እና የማያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች እንዲጠራቀሙ ያደርጋል። የአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡ የሽንት መጠን ማነስ ፣ ወይም በጭራሽ አለመሽናት፡፡ ማለትም በ 24 ሰዓት ውስጥ ከ 400 ሚሊ ሊትር ያነሰ መሽናት፡፡ ደም የቀላቀለ ሽንት፣ ቀይ ወይም ቡናማ የሆነ ሽንት፤ ሰውነት ማበጥ፤  ማስታወክ፣ የምግብ ፍላጎት አለመኖር፤ በቀላሉ የመድከም ስሜት፣ የማዞር ስሜት፤ የደረት ሕመም ወይም ግፊት ያልተስተካከለ የልብ ምት ...

ለብጉር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምንድናቸው?

ብጉር የቆዳ ቀዳዳዎች በሞቱ የቆዳ ሕዋሳት፣ በቅባት እና በባክቴሪያዎች ሲደፈኑ የሚፈጠር  የቆዳ ችግር ነው።  ይህም  ቆዳው እንዲቀላ፣  እንዲያብጥና  እንዲቆጣ ያደርገዋል።  በተገቢው ሁኔታ ያልታከመ ብጉር በቆዳ ላይ ጠባሳ በማምጣት የቆዳን ውበት ይቀንሳል፡፡  ለብጉር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው። ዕድሜ፤ በተለይም በዓሥራዎቹ  የዕድሜ ክልል ውስጥ በጣም የተለመደ ነው፡፡ የሆርሞን ለውጦች፤ በጉርምስና  ወይም በእርግዝና ወቅት፤  በቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ ካለ፤ የተወሰኑ መድኃኒቶች (Cor...

scroll top