ስለ ብጉር ምን ያህል ያውቃሉ?
ብጉር የቆዳ ቀዳዳዎች በሞቱ የቆዳ ሕዋሳት፣ በቅባት እና በባክቴሪያዎች ሲደፈኑ የሚፈጠር የቆዳ ችግር ነው። ይህም ቆዳው እንዲቀላ፣ እንዲያብጥና እንዲቆጣ ያደርገዋል። በተገቢው ሁኔታ ያልታከመ ብጉር በቆዳ ላይ ጠባሳ በማምጣት የቆዳን ውበት ይቀንሳል፡፡ በዚህ የተነሣም በራስ መተማመንን ዝቅ ሊያደርገው ይችላል። ብጉር በተለምዶ በፊት፣ በግንባር፣ በደረት፣ በላይኛው ጀርባ እና ትከሻ ላይ ይወጣል።ምክንያቱም እነዚህ የቆዳ አካባቢዎች ብዙ የቅባት ዕጢዎች ስለሚኖራቸው ነው። ለብጉር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምንድናቸው? ዕድሜ፤ በተለይም በዓሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ በጣም የተለመደ ነው፡፡ የሆርሞን ለውጦች፤ በጉርምስና ወይም በእርግዝና ወቅት፤ በቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ ካለ፤ ...