መካንነት በሴቶች ላይ
መካንነት ከሕክምና አንፃር እንዴት ይገለፃል? መካንነት፤ ጥንዶች ያለምንም ተአቅቦ ወይም የወሊድ መከላከያ ቢያንስ ለ1 ዓመት ሩካቤ ከፈጸሙ በኋላ፣ መፀነስ አልቻሉም ማለት ነው። ከ 35 - 40 ዓመት በላይ ያሉ ሴቶች ላይ ግን ለ 6 ወር ማርገዝ ከአልቻሉ መካንነት እንለዋለን። በዓለማችን ላይ በግምት ከ 10 - 15 በመቶ የሚሆኑ ጥንዶች ለዚህ ችግር ተጋላጭ ናቸው። አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የመካንነት ችግር በሴቶች ምክንያት፣ እንዲሁም አንድ ሦስተኛ የሚሆነው በወንዶች ምክንያት ይከሠታል፡፡ ቀሪው ደግሞ በሁለቱም ፆታዎች ችግር ወይም መንሥኤው የማይታወቅ ሊሆን ይችላል። በሴቶች ላይ ለመካንነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምንድናቸው? ዕድሜ ...