Learning materials for your health  Learn

Our Blog

የትንሹ አንጀት መታጠፍ/ መዘጋት

የትንሹ አንጀት እግደት ወይም መዘጋት ማለት አየር፣ ፈሳሽ እና ምግብ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በትንሹ አንጀት ውስጥ ማለፍ አልቻሉም ማለት ነው። በዚህ ምክንያት አንጀት ከያዘው አየር፣ ፈሳሽ እና ምግብ የተነሣ ሊያብጥ ይችላል፡፡ ይህ እብጠት የአንጀትን ምግብ እና ፈሳሽ የመምጠጥ ዐቅምን በማሳነስ የሰውነት ፈሳሽ ማነስ (Dehydration) እና የኩላሊት ሥራ መዳከም ሊያስከትል ይችላል።    የአንጀት እግደት በሚኖርበት ጊዜ ወደ አንጀት ኦክስጅንን እና የበለፀገ ምግብ የሚያመጡ ደም ሥሮች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ፡፡ ይህም የአንጀት ክፍሎች እንዲጎዱ (Strangulate) እና እንዲሞቱ (Gangrenous) ሊያደርግ ይችላል፡፡ የአንጀት ግድግዳ መጎዳት ወይም መሞት ምንን ያስከትላል? የአንጀት ግድግዳ ከተጎዳ ወይም ምውት ከሆነ በውስጡ ያለው ፈሳሽ እና በሽታ አምጪ ተሕዋስያን ሊወጡ እና የሆድ ዕቃን ሊበክሉ ይችላ...

ልጆቻችንን መቼ እናስከትብ?

ክትባት በተለይም ለሕፃናት ምን ጠቀሜታ አለው? ሕፃናት እንደተወለዱ ለአካባቢያቸው አዲስ ስለሚሆኑ ለብዙ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን የተጋለጡ ናቸው። በሽታ እንዳይበረታባቸውም የሰውነታቸውን የመከላከል ዐቅም ማሳደግ ይገባል፡፡ ስለዚህ  ክትባት ለልጆች በጣም አስፈላጊ ይሆናል። ክትባት በሽታ አምጪ የሚባሉ ተሕዋስያንን በማዳከም ወይም በመግደል አለያም መርዙን በመውሰድና ፕሮቲኑን በማዳቀል የሚሠራ ነው። የክትባት ዋና ሥራው በሽታ ከመከሠቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ነው። የሕፃናት ክትባት አሰጣጥ ፕሮግራም በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ የራሱ የሆነ የተዘጋጀ መመሪያ አለው። በዚህም መሠረት በጤና ተቋማት ውስጥ የሚከተሉት የክትባት ዓይነቶች ለልጆች ይሰጣሉ። ሕፃናት እንደተወለዱ ቢሲጂ (BCG) በ 6 ሳምንት (45 ቀን)   ፖሊዮ፣ ፔንታቫለንት፣ ፒሲቪ እና ሮ...

ክትባት ምንድነው?

ክትባት በሽታ አምጪ የሚባሉ ተሕዋስያንን በማዳከም ወይም በመግደል አለያም መርዙን በመውሰድና ፕሮቲኑን በማዳቀል የሚሠራ ነው። የክትባት ዋና ሥራው በሽታ ከመከሠቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ነው። የክትባት ዓይነቶች 1. ንቁ ክትባት (Active immunization) ይህ ክትባት ሰውነታችን የራሱን የሆነ የበሽታ መከላከል ዐቅም ሥርዓት እንዲገነባ የሚያደርግ ነው።  2. ንቁ ያልሆነ ክትባት (Passive immunization) ይህ ደግሞ ቀድሞውኑ የተመረተውን በሽታ መከላከል ወይም አንቲቦዲ በመስጠት ሰውነታችን  ለጊዜው ከበሽታው እንዲጠበቅ ያደርጋል። ልጅዎትን ለምን ያስከትባሉ? ክትባት በተለይም ለሕፃናት ምን ጠቀሜታ አለው? ሕፃናት እንደተወለዱ ለአካባቢያቸ...

ምጥ ሲጀምር የሚታዩ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ምጥ ጀመረ የሚባለው የሚከተሉት ምልክቶች ሲታዩ ነው።  የጀርባ / የወገብ ሕመም ወይም የሆድ ቁርጠት ከአለ - እርግዝናው ከ 37 ሳምንታት በላይ ከሆነና ቁርጠት ጀምሮ ወደ ሆስፒታል ከሄዱ፣ ሐኪሙ ምጡ እውነተኛ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ምርመራ ያደርጋል። በዋነኛነት የማሕፀን በር ምን ያህል እንደከፈተ፣ የቁርጠቱ መጠንና ቁጥር መጨመሩን ያያል። እውነተኛ ምጥ መሆኑ የሚታወቀው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ ከሆነና የማሕፀንን በርን መክፈት ከቻለ ነው።  ወፍራም፣ ደም የተቀላቀለበት ፈሳሽ (mucus) ከታየ የእንሽርት ውሃ መፍሰስ - በእርግዝና ወቅት ልጁ የሚገኘው እንሽርት ውሃን በያዘ ከረጢት ውስጥ ነው፡፡ ይህ ከረጢት በሚፈነዳበት ጊዜ በከረጢቱ ውስጥ ያለው ፈሳሽ ይፈስሳል፡፡ ይህም ቷ ብሎ ሊፈነዳ ወይም ቀስ እያለ ሊፈስስ ይችላል፡፡ በሁለቱም መንገድ ቢሆን ይሄ የሚያመለክተው ነፍሰ ጡሯን ሴት ምጥ እን...

ስለምጥ ማወቅ ያለብን ነገር ምንድን ነው?

ምጥ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶች አካል ለመውለድ የሚዘጋጅበት ተፈጥሮአዊ መንገድ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ምጥ ከ 37 እስከ 42 ሳምንቶች ባለው የእርግዝና ወቅት ይጀምራል፡፡  በምጥ ጊዜ የሚከሠቱ የሰውነት ለውጦች ምን ምንድን ናቸው? በምጥ ወቅት ከሚከሠቱ ነገሮች መካከል ዋነኛው እየጨመረ የሚሄድ የማሕፀን መኮማተር ነው። የዚህም ዋና ዓላማው የማሕፀን በር እንዲከፈት ማድረግ ነው። የማሕፀን መኮማተር መጠኑ እና ድግግሞሹ እየጨመረ ሲሄድ እንዲሁም የማሕፀን በር እየሳሳና እየተከፈተ ሲሄድ ወፍራም ደም የተቀላቀለበት ወፍራም ዝልግልግ ፈሳሽ (mucus) ከማሕፀን ይወጣል። የሕክምና ባለሙያዎች “ብለድ ሾው /bloody show” ይሉታል።  ይህም በእርግዝና ጊዜ ቆሻሻ ወደ ማሕፀን እንዳይገባ ለመከላከል የማሕፀንን በር የሚሸፍን ወፍራም ፈሳሽ (mucus) ነው።  ምጥ ሲጀምር እንዴት ማወቅ ይቻላል?&nbs...

በአማካኝ ምጥ ስንት ሰዓት ይፈጃል?

ምጥ ነፍሰ ጡር የሆኑ ሴቶች አካል ለመውለድ የሚዘጋጅበት ተፈጥሮአዊ መንገድ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ምጥ ከ 37 እስከ 42 ሳምንቶች ባለው የእርግዝና ወቅት ይጀምራል፡፡  ምንም እንኳን ምጥ ቀጣይነት ያለው ሂደት ቢሆንም፤ ለክትትል እንዲያመች በሦስት ደረጃዎች ይከፋፈላል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ (First stage)   የመጀመሪያ ደረጃ የሚባለው ምጡ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የማሕፀን በር ሙሉ በሙሉ እስኪከፈት ያለው ጊዜ ነው። የማሕፀን በር ሙሉ በሙሉ ተከፈተ የሚባለው ደግሞ 10 ሴ.ሜ ሲሆን ነው።  ከዚህ በተጨማሪ በዚህ የምጥ ደረጃ ላይ የቁርጠቱ መጠን እየጨመረ፣ እየረዘመ እና እየተቀራረበ ይሄዳል። ይህ ደረጃ ለ 2 ክፍሎች ይከፈላል። የመጀመሪያው ክፍል ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚወልዱ እናቶች እስከ 20 ሰዓታት፤ ከዚህ በፊት ለወለዱ ደግሞ እስከ 14 ሰዓታት...

የማረጥ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ማረጥ የሚባለው ሴቶች የወር አበባ ማየት የሚያቆሙበት ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡ ይህም ብዙውን ጊዜ ከ 45 እስከ 55 ዓመት ባለው ዕድሜ ውስጥ ይከሰታል። ምልክቶቹም አንዳንድ ሴቶች ያለ ምንም ምልክት ማረጥን ያልፋሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ግን ከሚከተሉት ምልክቶች ውስጥ አንድ ወይም ከዚያ በላይ አላቸው። እነዚህ ምልክቶች የሚፈጠሩት እንቁልጢ (ovary) ሥራውን ሲያቆም ነው። በዚህ ጊዜ በሰውነት ውስጥ ያለው የሆርሞኖች (በዋነኛነት የኤስትሮጂን) መጠንን ይቀንሳሉ። ይህም የተለያዩ የማረጥ ምልክቶችን ያስከትላሉ፡፡ ለምሳሌ ፦ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የሙቀት ስሜት - ይህ የሙቀት ስሜት በብዛት የሚጀምረው በላይኛው ደረት እና ፊት አካባቢ ነው፡፡ በመቀጠልም በመላው ሰውነት ውስጥ ተሰራጭቶ ከሁለት እስከ አራት ደቂቃዎች ይቆያል፡፡ አንዳንድ ሴቶች በዚህ ወቅት ያልባቸዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ ሙቀቱ ሲያልቅ ብርድ ብርድ ይላቸዋል፤ ይንቀጠቀጣሉ።ሌሎቹ...

ማረጥ ምንድነው? መቼ ይከሠታል?

ማረጥ ማለት ሴቶች ወርሃዊ የወር አበባ ማየት የሚያቆሙበት ጊዜ ነው፡፡  ይህም ብዙውን ጊዜ ከ 45 እስከ 55 ዓመት ባለው ዕድሜ ውስጥ የሚፈጠር ነው፡፡  በዚህ ጊዜ እንቁልጢ (ovary) እንቁላሎችን መሥራት እንዲሁም ኤስትሮጅንና ፕሮጀስትሮን የሚባሉትን ሆርሞኖችን ማምረቱን ያቆማል። ከወር አበባ መዛባት በተጨማሪ ከማረጥ ጋር የተያያዙ ብዙ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የሰውነት ሙቀት፣ የሌሊት ላብ፣ የእንቅልፍ ችግሮች እና የብልት ፈሳሽ ናቸው፡፡ ማረጥ የሴቶች ሕይወት መደበኛ ክፍል ስለሆነ ሁል ጊዜ መታከም አያስፈልገውም፡፡ ሆኖም ከማረጥ በፊት እና በኋላ የሚከሠቱ ለውጦች የስሜት ወይም የሰውነት መረበሽ  ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ምልክቶች የሚያስታግሱ ውጤታማ ሕክምናዎችን መሞከር ይቻላል። አንዲት ሴት ማረጧን እንዴት ማወቅ ትችላለች? ከማረጥ በፊት እና በኋላ...

scroll top