የአስም በሽታ
የአስም በሽታ እየተደጋገመ የሚመጣ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ፣ የመተንፈሻ ቱቦ እና የሳምባ ሕመም ነው። በሽታው የአየር ቱቦዎችን በማጥበብና በማስቆጣት መተንፈስን ከባድ ያደርገዋል፡፡ የአስም በሽታ በበለፀጉት አገራት የበለጠ ቢከሠትም፤ አሁን አሁን ግን በታዳጊ አገሮችም እየጨመረ ይገኛል። በዓለማችን 10 - 12% የሚሆኑት ጎልማሳዎችና እና 15% የሚሆኑት ሕፃናት በዚህ በሽታ ይጠቃሉ። ወንዶች ሕፃናት ከሴት ሕፃናት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። በወጣቶች ላይ ግን ሁለቱም እኩል ተጋላጭ ሲሆኑ፤ ዕድሜያቸው ከ 40 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ይጠቃሉ። ለአስም በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ምን ሊሆኑ ይችላሉ? በቤተሰብ የአስም ሕመም ከአለ፤ በልጆች ላይ የቆዳ ወይም ማንኛውም ዓይነት የመተንፈሻ አካላት አለርጂ ከአለ ፤ ታማሚው አዋቂ ከሆነ...