FAQs
ቀጠሮዎን ካስያዙ በኋላ። ከተቀመጡልዎት 4 የክፍያ አማራጮች የሚስማማዎትን መርጠው መጠቀም ይችላሉ። እነሱም ቴሌብር ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤ We ብር እና አቢሲንያ ባንክ ናቸው። ለበለጠ መረጃ 9394 ላይ ይደውሉልን።
በመጀመሪያ ቴሌብር የሚለውን መርጠው ‘ይቀጥሉ’ የሚለውን ይጫኑ። የ ቴሌብር አካውንት ካለዎ ቀጥታ የቴሌብር መተግበሪያውን ይከፍትልዎታል። የቴሎብር አካውንት እና መተግበሪያ ከሌልዎ ደግሞ QR ኮዱን ስካን አርገው በሌላ ሰው አካውንት መክፈል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚለውን አማራጭ በዊኬር መተግበሪያ ላይ ይምረጡ። የሚመጣልዎትን ኮድ ኮፒ ያድርጉት።. በማስከተል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይክፈቱ ፤ ቀጥሎ Utility አማራጭ ውስጥ ገብተው WeBirr የሚለውን አማራጭ ይክፈቱ። Debit Account የሚለው አማራጭ ውስጥ ይግቡና ኮፒ ያደረጉትን የክፍያ ኮድ ይገልብጡ። continue እና confirm ብለው ይጨርሱ
የቀጠሮው ሰዓት ሲደርስ ሐኪሙን በቤትዎ ሆነው በኦንላይን በቪዲዮ፣ በኦድዮ እና በጽሑፍ መልእክት ማማከር ይችላሉ።
ሐኪሙም ሆነ ታካሚው ጥሪውን ማስጀመር ይችላል። ታካሚው ጥሪውን ለማስጀመር በመጀመሪያ መተግበሪያውን ይክፈቱ። በመቀጠልም ከስር ከተዘረዘሩት ውስጥ ' My appointment' ወይም 'ቀጠሮ' የሚለውን በመጫን ይቀጥሉ። ከዛም የሚመጣዎት ሲጫኑ በቀኝ በኩል ከላይ ከተዘረዘሩት አማራጮች ውስጥ (በቪዲዮ፣ በኦድዮ ወይም በጽሑፍ መልእክት) ውስጥ አንዱን በመምረጥ መደወል ይችላሉ።
የዌኬር መተግበሪያ ሐኪምን እና ታካሚን በኦንላይን የሚያገናኝ መተግበሪያ ነው። መተግበሪያውን ከጫኑ በኃላ ከተዘረዘሩት የሕክምና አማራጮች ውስጥ የሚፈልጉትን ሐኪም መርጠው ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። መተግበሪያውን ለመጫን ማስፈንጠሪያውን ይጠቀሙ። https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient ለበለጠ መረጃ 9394 ይደውሉልን።
አቢሲንያ ባንክ የሚለውን አማራጭ በዊኬር መተግበሪያ ላይ ይምረጡ። የሚመጣልዎትን ኮድ ኮፒ ያድርጉት።. በማስከተል የአቢሲንያ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ይክፈቱ ፤ ቀጥሎ Utility አማራጭ ውስጥ ገብተው WeBirr የሚለውን አማራጭ ይክፈቱ። Debit Account የሚለው አማራጭ ውስጥ ይግቡና ኮፒ ያደረጉትን የክፍያ ኮድ ይገልብጡ። በማስከተል continue እና እና confirm ብለው ይጨርሱ።