Learning materials for your health  Learn

የእንቅርት በሽታ ምልክቶች

  • September 13, 2021
  • የጤና እክሎች

እንቅርት በታችኛው አንገት ውስጥ በፊት ለፊት የሚገኝ  እጢ ነው፡፡ የልብን፣ የጡንቻን  እና የምግብ መፈጨት ሥራን  እንዲሁም የአንጎል እና የአጥንት ዕድገትን የሚቆጣጠር ሆርሞኖችን ያመነጫል።

የእንቅርት ሆርሞን መብዛት የሚያሳያቸው ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው?

አንዳንድ ጊዜ የእንቅርት ዕጢ በጣም ብዙ የእንቅርት ሆርሞን እንዲመረት  ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ ለሚከተሉት ምልክቶች ይዳርጋል፡፡

  • የስሜት መረበሽ ወይም በቀላሉ መናደድ 

  • እንቅልፍ የማጣት ችግር

  • የድካም ስሜት 

  • ያልታሰበ ክብደት መቀነስ ከምግብ ፍላጎት መጨመር ጋር

  • ፈጣን የልብ ምት

  • መንቀጥቀጥ

  • ሙቀት መሰማት፣ ማላብ

  • የወር አበባ መዛባት፣ ልጅ ለመፀነስ መቸገር

  • የዐይን ኳስ ወደፊት መውጣት እና

የእንቅርት ሆርሞን ማነስ የሚያሳያቸው ምልክቶች ምን ምንድን ናቸው?

  • የድካም ስሜት

  • ዐቅም ማነስ

  • ሰውነት መብረድ፣ ቆዳ መድረቅ

  • የምግብ ፍላጎት ሳይጨምር ክብደት መጨመር 

  • ሻካራ ቀጭን ፀጉር ማብቀል፣ ፀጉር መነቃቀል

  • የሆድ ድርቀት

  • የወር አበባ መዛባት እና ለመፀነስ መቸገር ናቸው።

ስለ እንቅርት በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።

 

Share the post

scroll top