Learning materials for your health  Learn

የጥርስ መቦርቦር

  • May 24, 2023
  • የጤና እክሎች

የጥርስ መቦርቦር  (Dental caries)

 

የጥርስ መቦርቦር (Dental caries) ስኳርን ወደ አሲድ መቀየር የሚችሉ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን (bacteria) የጥርስን ንጣፍን ሲያጠቁ የሚፈጠር የጥርስ በሽታ ነው፡፡ 

  •  ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቀስ በቀስ የጥርስ ህመም ፣ ቁስለት አልፎ ተርፎም የጥርስ መበስበስ ያስከትላል ፡፡
  • ይህ በሽታ በሁሉም ዕድሜ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከሌላው እድሜ በተለየ ህፃናት ለጥርስ መቦርቦር የተጋለጡ ናቸው

 

የጥርስ መቦርቦር በምን ምክንያት ይፈጠራል?

  •  የጥርስ መቦርቦርን የሚያስከትሉ ባክቴሪያዎች በምግብ እና መጠጥ ውስጥ ካለው ስኳር ጋር ሲገናኙ አሲድ ይፈጥራሉ ፡፡ 
  •  ይህ አሲድ የጥርስን ሽፋን (Enamel) በማጥቃት ቅስ በቀስ ማዕድናትን ያሳጣል፡፡
  •  አስፈላጊውን እንክብካቤ ካላገኘ ከጊዜ በኋላ የጥርስን ሽፋን ተዳክሞ መቦርቦር ይጀምራል፡፡

 

የጥርስ መቦርቦር ምን ምን ምልክቶችን ያሳያል? 

  •  መጀመሪያ አካባቢ ብዙም ምልክቶች አይታይም ፡፡ 
  •  የጥርስ መቦርቦሩ እየገፋ ሲሄድ ግን ጥርስ ለጣፋጭ ፣ ለሞቃት ወይም ለቅዝቃዛ ነገሮች የበለጠ ስስ እየሆነ ይመጣል፡፡ 
  •  በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ ደግሞ ከባድ የሆነ የጥርስ ህመም ፣ የፊት እብጠት እና ትኩሳት ሊያስከትል ይችላል ፡፡

 

ህክምናውስ ምን ይመስላል?

የጥርስ መቦርቦርን ለማከም የሚረዱ ብዙ አማራጭ መንገዶች አሉ። ከነዚህ ውስጥ የተለመዱት የሚከተሉት ናቸው።

 

  •   የተቦረቦሩ የጥርስ ቀዳዳዎችን መሙላት፦ የጥርስ ሐኪሞች ቀዳዳዎችን በመሙላት ህክምና ያደርጋሉ ፡፡ ይህም የሚሆነው የበሰበሰውን ህዋስ ከተወገደ እና ጥርሱ ከተጰዳ በውሃላ ነው። 

 

  •   ጥርሱ በጣም ከተጎዳ እና ማዳን ካልተቻለ ጥርሱን ማስወገድ ሊያስፈልግ ይችላል።

 

የጥርስ መቦርቦርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የጥርስ መበስበስን ለመከላከል ማድረግ የሚችሏቸው አንዳንድ ነገሮችን እነሆ፦

  •  የጥርስ መበስበስ ለመከላከል ወይም ባለበት ለማቆም የሚያስችል ፍሎራይድ የተባለ ማዕድን ይጠቀሙ ፡፡ 

ፍሎራይድ ከምን ከምን ማግኘት እችላለሁ?

  •  ፍሎራይድ የያዘ የጥርስ ሳሙና / የአፍን ማጠቢያን በመጠቀም
  •  በፍሎራይድ የበለዕገ ውሃ  በመጠጣት
  •  ፍሎራይድ በያዘ የጥርስ ሳሙና ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ለ ሁለት ደቂቃ ይቦርሹ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከድድ ጀምሮ ወደ ታች በሆን ይመረጣል፡፡እንዲሁም በመደበኛነት በጥርስ መካከል ያለ ቆሻሻን የሚያጰዳ የክር ማጽጃን ይጠቀሙ፡፡
  •  በስኳር የበዛባቸውን ምግቦችን ይቀንሱ
  •  ጭስ አልባ ትንባሆን ጨምሮ የትምባሆ ምርቶችን አይጠቀሙ
  • ከዚህ በተጨማሪ የጥርስ ሀኪምዎ ጋር በመደበኛነት ክትትል ማድረግዎን አይርሱ። 

❗️ከላይ የተጠቀሱትን ምክሮችና ጥቆማዎች በመተግበር የጥርስዎን ጤንነት መጠበቅ ይችላሉ ❗️

Share the post

scroll top