የእንቅርት ሆርሞን መብዛት የሕክምና አማራጮች ምን ምንድን ናቸው?
- September 14, 2021
- የጤና እክሎች
ሕክምናው መድኃኒቶችን፣ ቀዶ ጥገናን እና ሬዲዮአክቲቭ አዮዲንን ሊያጠቃልል ይችላል።
-
ዕጢው የሚያመርተውን ሆርሞን የሚቀንሱ ( anti-thyroid)
-
ምልክቶችን ለመቀነስ የሚረዱ (Beta blockers)
እነዚህም የእንቅርት ሆርሞን ሚዛን እስኪስተካከል ድረስ ምልክቶችን በመቀነስ የበለጠ ምቾት እንዲኖር ያደርጋሉ።
-
ሬዲዮአክቲቭ አዮዲን
መድኃኒቱ የሚወሰደው በሚዋጥ ክኒን ወይም ፈሳሽ መልክ ሲሆን ዕጢው እንዲጠፋ ያደርጋል። ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች ይህንን ሕክምና መጠቀም የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም የሕፃኑን የእንቅርት ዕጢ ሊጎዳ ይችላል። ሕክምናውን የወሰዱ ሴቶችም ለማርገዝ ከመሞከራቸው በፊት ቢያንስ 6 ወር መጠበቅ አለባቸው።
-
ቀዶ ጥገና
ሌሎች የሕክምና ምርጫዎች ካልተሳኩ በቀዶ ጥገና ዕጢው እንዲወጣ ይደረጋል። ነገር ግን በአብዛኛውን ጊዜ ቀዶ ጥገናው ከመደረጉ በፊት የሆርሞኑን መጠን ለማስተካከል እና ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚያግዙ በአፍ የሚወሰዱ እንክብሎች ይታዘዛሉ።
የመድኃኒቶቹ መጠን የሚስተካከለው ተከታታይ የደም ምርመራዎችን በማድረግ ስለሆነ ታማሚዎች በመደበኛነት በጤና ተቋም ክትትል ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛውን ጊዜ በሬዲዮአክቲቭ አዮዲን ወይም በቀዶ ጥገና ሕክምና የተደረገላቸው ሰዎች ከሕክምና በኋላ በጣም ትንሽ የእንቅርት ሆርሞን ሊቀራቸው ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት በቀሪው ሕይወታቸው የእንቅርት ሆርሞን ክኒኖች መውሰድ ሊኖርባቸው ይችላል።
ስለ እንቅርት በሽታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።