Learning materials for your health  Learn

የእከክ በሽታ ምንድን ነው? ምልክቶቹስ?

  • September 15, 2021
  • የጤና እክሎች

የእከክ በሽታ (Scabies) ሳርኮፕተስ እስኬቢ (Sarcoptes scabiei) ተብሎ በሚጠራው ተባይ አማካኝነት የሚመጣ የቆዳ በሽታ ነው፡፡  

ይህ በሽታ የተለያዩ ምልክቶች አሉት። በብዛት የሚታዩት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው።

  • እከክ  

ከስሙ መረዳት እንደምንችለው የበሽታው ዋና ምልክት እከክ ነው። ብዙውን ጊዜ ምሽት ላይ ወይም ደግሞ ከሙቅ ሻወር በኋላ ይባባሳል፡፡ የሚከተሉት የሰውነት ክፍሎች ከሌሎቹ በበለጠ በበሽታው የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።

  • በጣቶች መካከል

  • በክርን እና በጉልበቶች ዙሪያ መተጣጠፊያ ላይ

  • በብብት ቆዳ

  • በጡት ጫፍ ዙሪያ አካባቢ

  • በወገብ ዙሪያ

  • በመቀመጫ መሃል እና በላይኛው ጭኖች አካባቢ

ብዙውን ጊዜ የጀርባ እና የጭንቅላት ቆዳን አያጠቃም።

  • ቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታ (ቁስሎች) 

  • በቆዳ ላይ የሚወጣ ቀጭን የመስመር ምልክት 

  • ክረስትድ እስኬቢስ (crusted scabis) - በሽታ የመከላከል ዐቅማቸው የተዳከመ ሰዎች (ኤች አይ ቪ በሽተኞች፣ ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች እና ሌሎች ሁኔታዎችን ጨምሮ) ከባድ ምልክት ሊኖራቸው ይችላል። ይህም “ክረስትድ እከክ” ተብሎም ይጠራል ፡፡ ክረስትድ እስኬቢስ (crusted scabis) ከተለመደው እከክ በተለየ ሁኔታ በሙሉ ሰውነት ላይ የሚሰራጭ እና ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በሽታ ነው።

ስለ እከክ በሽታ ሙሉ መረጃ ለማንኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። 

Share the post

scroll top