Learning materials for your health  Learn

የቆዳ አስም ምንድን ነው? ምልክቶቹስ?

  • September 16, 2021
  • የጤና እክሎች

የቆዳ አስም (የቆዳ አለርጂ) የተለመደ የቆዳ በሽታ ዓይነት ሲሆን፤ ቆዳን በማድረቅ እና በማሳከክ የቆዳን ብግነት ወይም መጉረብረብ (Inflammation)  የሚያመጣ ሕመም ነው። 

ሰዎች በቆዳ አስም በሚጠቁበት ጊዜ 

  • ቆዳቸው የማሳከክ፣ የመድረቅ፣ የመሻከር፣ 

  • ዉሃ የቋጠረ ቀይ ሽፍታ እና የመቆጣት ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። 

ምልክቶቹም ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፉ ሲሆን፤ እየጠፉ ተመልሰው በመምጣትም ረጅም ጊዜ የመቆየት ጠባይ አላቸው።  

የቆዳ አስም ብዙ ጊዜ እንደ ታማሚዎች የዕድሜ ክልል የተለያየ መልክ ይኖረዋል። ለምሳሌ፡- 

  • ዕድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ በእጃቸው፣ በእግራቸው፣ በጉንጭ  ወይም በጭንቅላታችቸው ላይ ይወጣል፡፡ ነገር ግን ዳይፐር (ሽንት ጨርቅ) አካባቢ ያለውን የሰውነት ክፍል ብዙውን ጊዜ አያጠቃም።

  • በትላልቅ ልጆች እና ዐዋቂዎች ላይ ብዙውን ጊዜ የአንገት አካባቢ፣ የክርን መሰንጠቂያዎችን እና የጉልበት ጀርባዎች ላይ የሚወጣ ሲሆን፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ በእጅ፣ በእግር፣ በክንድ እና በፊት ላይ ሊወጣ ይችላል።

  • በትላልቅ ልጆች እና ዐዋቂዎች ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ  ቆዳው እየጠነከረ ሊሄድ እና ከብዙ ማከክ የተነሣ ጠባሳ  ሊፈጥር ይችላል።

 የቆዳ አስምን እንዴት መከላከል እንደምንችል እና ስለተለያዩ የህክምና አማራጮች ለማወቅ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። 

Share the post

scroll top