Learning materials for your health  Learn

የሐሞት ጠጠር ምንድንነው? ምልክቶቹስ?

  • September 20, 2021
  • የጤና እክሎች

የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠሩ ትናንሽ ጠጠሮች ናቸው::

የሐሞት ጠጠር ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የሐሞት ጠጠር የአለባቸው አብዛኛዎቹ ሕመምተኞች ምንም ምልክቶች የላቸውም፡፡ 

ነገር ግን ምልክት ከአላቸው፤ የተለመዱት ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው። 

  • ከደረት ዝቅ ብሎ ጨጓራ አካባቢ ያለ ሕመም ስለሆነ፤ በብዛት በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ለብዙ ዓመታት ለጨጓራ በሽታ ሲታከሙ የኖሩ ናቸው፡፡ 

  • በተጨማሪም በቀኝ በኩል የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ሕመም ሊኖር ይችላል፡፡ ይህም ከ 30 ደቂቃ እስከ 6 ሰዓታት የሚቆይ የማያቋርጥ እና ከባድ የሚባል ሕመም ሲሆን ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሕመሙ ይጨምራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ ወደ ጀርባ እና ትከሻ ሊሰራጭ ይችላል፡፡  

  • ከዚህ በተጨማሪ የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ሊኖር ይችላል፡፡ 

  • እንደ ትኩሳት፣ የቆዳ እና የዐይን ቢጫ መሆን ከሐሞት ጠጠር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮችን ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡ 

አልፎ አልፎ ሌሎች ያልተለመዱ ምልክቶችም ሊታዪ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፦

  • የደረት ሕመም

  • የሆድ መነፋት

  • ቶሎ መጥገብ 

  • ቃር እና የመሳሰሉት ምልክቶች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ስለ በሽታው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

Share the post

scroll top