Learning materials for your health  Learn

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች ምንድናቸው?

  • September 22, 2021
  • የጤና እክሎች

አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ማለት፤ ኩላሊት በድንገት ሥራውን እየቀነሰ ሲሄድ ወይም  በፍጥነት ሥራውን ሲያቆም  ማለት ነው፡፡ ይህም በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ጨው፣ ውሃ እና የማያስፈልጉ ንጥረ ነገሮች እንዲጠራቀሙ ያደርጋል።

የአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡

  • የሽንት መጠን ማነስ ፣ ወይም በጭራሽ አለመሽናት፡፡ ማለትም በ 24 ሰዓት ውስጥ ከ 400 ሚሊ ሊትር ያነሰ መሽናት፡፡

  • ደም የቀላቀለ ሽንት፣ ቀይ ወይም ቡናማ የሆነ ሽንት፤

  • ሰውነት ማበጥ፤ 

  • ማስታወክ፣ የምግብ ፍላጎት አለመኖር፤

  • በቀላሉ የመድከም ስሜት፣ የማዞር ስሜት፤

  • የደረት ሕመም ወይም ግፊት

  • ያልተስተካከለ የልብ ምት

  • የትንፋሽ እጥረት

ከላይ የተጠቀሱት  ምልክቶች  ከአጋጠመዎ በቶሎ ወደ ሕክምና ተቋም  መሄድ ይኖርብዎታል። 

ስለበሽታው ሙሉ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

Share the post

scroll top