Learning materials for your health  Learn

የኮቪድ 19 በሽታ ምንነት እና ምልክቶች

  • September 30, 2021
  • የጤና እክሎች

ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቁ የተለያዩ ቫይረሶች ስብስብ ነው። ኮሮና የተባሉበትም ምክንያት፤ ከእንግሊዘኛው “ክራውን” ከሚለው ቃል በመነሣት በቫይረሶቹ የውጪ ክፍል ላይ ”ዘውድ” የመሰለ ከሰውነት ኅብረ ሕዋስ ጋር የሚጣበቅ ፕሮቲን ስለአላቸው ነው። 

የኮቪድ 19 ሕመምተኞች የሚያሳዩት ብዙ ዓይነት ምልክቶች፣ ከቀላል ምልክቶች እስከ ከባድ ሕመም ድረስ ሪፖርት ተደርገዋል፡፡ በአጠቃላይ ግን ሕመምተኞች በቫይረሱ ​​ከተያዙ ከ 2 - 14 ቀናት በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶችን ያሳያሉ ፡፡  

  • ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት

  • ሳል፣ የመተንፈስ ችግር

  • ድካም፣ የጡንቻ ሕመም፣ ራስ ምታት

  •  መቅመስ እና ማሽተት አለመቻል

  • ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ፣ ተቅማጥ 

በዕድሜ የገፉ፣ እና እንደ የልብ፣ የሳንባ በሽታ፣ የስኳር በሽታ የመሳሰሉ ከባድ መሠረታዊ የጤና እክሎች ያሉባቸው ሰዎች የሚከተሉትን ከባድ ምልክቶች የማሳየት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

  • የመተንፈስ ችግር

  • በደረት ውስጥ የማያቋርጥ ሕመም 

  • ራስን መሳት

  • የጣት ጫፍ እና የከንፈር ቆዳ ቀለም ወደ ግራጫ ወይም ሰማያዊ ቀለም መቀየር

እነዚህን ምልክቶች ከአዩ በፍጥነት ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ ተገቢ ነው፡፡

ስለ ኮቪድ በሽታ ክትባት እና ህክምና መርጃ ማግኘት ከፈለጉ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

Share the post

scroll top