Learning materials for your health  Learn

ልጆቻችንን መቼ እናስከትብ?

  • November 3, 2021
  • የጤና እክሎች

ክትባት በተለይም ለሕፃናት ምን ጠቀሜታ አለው?

ሕፃናት እንደተወለዱ ለአካባቢያቸው አዲስ ስለሚሆኑ ለብዙ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን የተጋለጡ ናቸው።

በሽታ እንዳይበረታባቸውም የሰውነታቸውን የመከላከል ዐቅም ማሳደግ ይገባል፡፡ ስለዚህ  ክትባት ለልጆች በጣም አስፈላጊ ይሆናል።

ክትባት በሽታ አምጪ የሚባሉ ተሕዋስያንን በማዳከም ወይም በመግደል አለያም መርዙን በመውሰድና ፕሮቲኑን በማዳቀል የሚሠራ ነው። የክትባት ዋና ሥራው በሽታ ከመከሠቱ በፊት አስቀድሞ መከላከል ነው።

የሕፃናት ክትባት አሰጣጥ ፕሮግራም በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ የራሱ የሆነ የተዘጋጀ መመሪያ አለው። በዚህም መሠረት በጤና ተቋማት ውስጥ የሚከተሉት የክትባት ዓይነቶች ለልጆች ይሰጣሉ።

  • ሕፃናት እንደተወለዱ ቢሲጂ (BCG)

  • በ 6 ሳምንት (45 ቀን)   ፖሊዮ፣ ፔንታቫለንት፣ ፒሲቪ እና ሮታ ( OPV,PCV,Penta,Rota)

  • በ 10 ሳምንት ፡ በ6 ሳምንት ከሚሰጠው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

  • በ14 ሳምንት ከ 6 ፡ ሳምንት ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ነገር ግን ሮታ አይሰጥም፡፡

  • በ 9 ወሩ ፡ የኩፍኝ ክትባት፣ ቪታሚን ኤ

  • ቪታሚን ኤ በየ 6 ወሩ እስከ አምስት ዓመታቸው ድረስ ክትባቱን ቢወስዱ ይመረጣል።

በተለያዩ ጊዜያት ወረርሽኞች ሲከሠቱ ለምሳሌ እንደ ማጅራት ገትር፣ ፖሊዮ፣ ኩፍኝ እና ትክትክ፤ በዓለምና በሀገር አቀፍ ደረጃ  እነዚህን በሽታዎች ለመቆጣጠር ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ በጅምላ ለሕፃናት ክትባት ይሰጣል።

ስለ ክትባት ተጨማሪ መርጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።

Share the post

scroll top