የአስም በሽታ ምንድን ነው? ምልክቶቹስ?
- September 7, 2021
- የጤና እክሎች
የአስም በሽታ እየተደጋገመ የሚመጣ፣ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ፣ የመተንፈሻ ቱቦ እና የሳምባ ሕመም ነው። በሽታው የአየር ቱቦዎችን በማጥበብና በማስቆጣት መተንፈስን ከባድ ያደርገዋል፡፡
የአስም ምልክቶች ቀላል ወይም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ። ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ቢሆንም የአስም ምልክቶች በድንገት ጀምረው እስከ ሞት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡
-
በሚተነፍሱበት ወቅት ሲር ሲር የሚል ድምፅ ማሰማት፤
-
ሳል (በተለይም ምሽት ላይ)
-
በደረት አካባቢ የመጨነቅ ስሜት
-
ትንፋሽ ማጠር
ምልክቶቹ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ወይም ከዚህም ባነሰ ጊዜ ሊከሠቱ ይችላሉ፡፡
የሚከተሉት ምልክቶች ካለዎት እንዲሁም የሚከተሉት አጋላጭ ሁኔታዎች ካሉ ሐኪምዎን ማማከር አይርሱ።
-
በቤተሰብ የአስም ሕመም ከአለ፤
-
በልጆች ላይ የቆዳ ወይም ማንኛውም ዓይነት የመተንፈሻ አካላት አለርጂ ከአለ ፤
-
ታማሚው አዋቂ ከሆነ ደግሞ በልጅነት ጊዜ ማንኛውም ዓይነት የአለርጂ ችግር ከነበረ፤
-
የመተንፈሻ አካላት አለርጂ ከነበረ፤
-
ከመጠን ያለፈ ውፍረት
-
ሲጋራ ማጨስ ወይም ተገብሮ ማጨስ (passive smoking)
-
የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን
ስለ አስም በሽታ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ። በተጨማሪም በሙያው የተካኑ ሐኪሞችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ።