Learning materials for your health  Learn

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ 

  • April 15, 2022
  • የጤና እክሎች

ኤች.አይ.ቪ ፓዘቲቭ  ከሆነች እናት የሚወለዱ ሕፃናት እንክብካቤ 

(HIV exposed neonate)

- ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ (በደሟ ውስጥ) የአለባት አንዲት እናት በእርግዝናዋ ወቅት፣ በምጥና በወሊድ ጊዜ እንዲሁም ጡት በምታጠባበት ጊዜ ልጇ ለኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ኢንፌክሽን የተጋለጠ ይሆናል።  

  - ስለዚህም ሕፃኑ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ በጤና ተቋም ውስጥ ክትትል ይደረግለታል። 

  • ለመጀመሪያዎቹ 6 ወራት በየወሩ ከዚያም በየ3 ወሩ ይቀጥላል፡፡ የሚደረጉት የሕክምና ክትትሎች የሚከተሉት ናቸው ::

- አጠቃላይ የጤና ምርመራ 

- አካላዊና ሥነ እእምሯዊ ዕድገት ክትትል 

- የአመጋገብ ትምህርት፣ ክትባት መስጠት 

- የተጓዳኝ በሽታ መከላከያ መድኃኒት( cotrimoxazole Preventive therapy) ማስጀመር 

- የሳንባ ነቀርሳ ተጋላጭነት ክትትል 

- የኤች.አይ.ቪ ምርመራ 

 - ቋሚ ክትትል ማስጀመር።

ለሕፃኑ የሚሰጠው የኤች.አይ.ቪ መድኃኒት ዓይነቱና ለምን ያህል ጊዜ ይወሰዳል? 

ለሕፃኑ ሁለት ዓይነት መድኃኒት ይጀመርለታል:: እነዚህም፤

        ኤዚቲ (AZT) ለ ስድስት ሳምንታት

         ኔቬራፒን ( NVP) ለ ዓሥራ ሁለት ሳምንታት

  • ሕፃኑ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ መቼ ያድርግ? 

      - ከተወለደ 6 ሳምንት ሲሞላው (HIV virologic testing) 

      - ሕፃኑ ከ9 - 12 ወር ከሆነ (HIV antibody &/or HIV virologic test) 

      ልብ ይበሉ ! ሕፃኑ ጡት መጥባት በአቆመ በ 3 ወሩ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ቢያደርግ ይመከራል። 

በአጠቃላይ ቫይረሱ የአለባት እናት ለልጅዋ ምን ዓይነት ጥንቃቄ ታድርግ? 

    - ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ልጇን ጤና ተቋም በመውሰድ ክትትልና ምርመራ ማድረግ 

    - እስከ 6 ወር ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻ መስጠት ከዚያ በኋላ ተጨማሪ ምግብ መጀመር 

    - የልጁን መድኃኒት በአግባቡ መስጠት 

     - እናትየው የፀረ ኤች. አይ.ቪ መድኃኒቷን በአግባቡ መውሰድ ይኖርባታል።


 

Share the post

scroll top