አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)
- March 3, 2023
- የጤና እክሎች
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) በሽታ ህመም ያለው በቆዳ ላይ የሚወጣ ሕመም ያለው ሽፍታ ነው፡፡ሲሆን ቫሪሴላ -ዞስተር (Varicella zoster) በሚባል ቫይረስ አማካኝነት ይከሠሰታል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ 20 በመቶ የሚሆነው የዓአለማችን ሕህዝብ በዚህ በሽታ ይጠቃል፡፡ ይህ ሕህመም የሚከሠሰተው አስቀድሞ ጉድፍ (Chickenpox) በተያዙ ሰዎች ላይ ነው፡፡ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች በጉድፍ በሽታ ተይዘው እንደነበረ ላያውቁ ወይም ላያስታውሱ ይችላሉ።
-
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) እንዴት ይከሠሰታል?
ቫሪሴላ -ዞስተር ሰዎች በጉድፍ እንዲታመሙ የሚያደርግ ቫይረስ ሲሆን፤ ሕህመሙ ከአካለፈ በኋላ ይህ ቫይረስ በአከርካሪ እና በአንጎል አቅራቢያ በሚገኙ ነርቮች ውስጥ ይቀመጣል። አመቺ ሁኔታን ሲያገኝ ይህ ቫይረስ በነርቮች ውስጥ በመጓዝ በቆዳችን ላይ አልማዝ ባለጭራ በሽታ እንዲከሠሰት ያደርጋል።
-
ለአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) መከሠሰት አመቺ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
በሽታ የመከላከል ዐዓቅም የሚቀንሱ ሁኔታዎች።
-
ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ ህመም
-
የካንሰር በሽታ ወይም የኬሞቴራፒ ሕክምና
-
አንዳንድ መድኃኒቶች (Steroids)
-
ከፍተኛ ውጥረት ወይም ጭንቀት
-
ዕድሜ በተለይም ከ 50 ዓመት በላይ
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምልክቶች
-
አልማዝ ባለጭራ ማንኛውንም የሰውነት ክፍል ሊያጠቃ ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን በአንድ ጎን በኩል በደረት፣ በሆድ ወይም በጀርባ ላይ ሲወጣ ይስተዋላል።
-
ይህ ህመም ቆዳ ላይ ሽፍታ ከማሳየቱ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ የመደንዘዝ፣ የማቃጠል እና የማሳከክ ስሜት ይኖረዋል። ይህ ስሜት ከታየ 1 ወይም- 2 ቀናት በኋላ በአንድ የሰውነት ጎን ብቻ የቆዳ መቆጣት እና የቀበቶ ቅርፅ የመሰለ ዉሃ የቋጠረ፣ ሕህመም ያለው ሽፍታ መታየት ይጀምራል። ብዙ ጊዜ ሽፍታው ከጥቂት ቀናት በኋላ መድረቅ እና መክሰም ይጀምራል፡፡ ከዚያም በአንድ1 ወይም ሁለት2 ሳምንት ውስጥ ይጠፋል።
-
በተጨማሪ ትኩሳት ፣ ድካም፣ ራስ ምታት እና ህመሙ በተከሰተበት አካባቢ ንፍፊት (Lymphadenopathy) መውጣት ሊኖር ይችላል።
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ተላላፊ ነውን?
ታማሚዎች በቀጥታ አልማዝ ባለጭራን ማስተላለፍ አይችሉም። ነገር ግን የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጉድፍ ታሞ የማያውቅ ሰው በታማሚው አካባቢ በሚሆንበት ጊዜ በጉድፍ በሽታ ሊጠቃ ይችላል።
ቫይረሱ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ ቀጥታ የቆዳ ንክኪ ወይም በትንፋሽ አማካኝነት ይተላለፋል። ስለዚህ የጉድፍ ክትባት ያልወሰደ ወይም ጭራሽ ታሞ የማያውቅ ሰው ከታማሚው ጋር የቅርብ ንክኪ ባያደርግ ይመረጣል።
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምን ዓይነት ከባድ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል?
አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ችግሮች የሚከሠሰቱት ዕድሜያቸው በገፋ ሰዎች ወይም በሽታ የመከላከል ዐአቅማቸው በቀነሰ (Immunocompromised) ሰዎች ላይ ነው።
እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
ከአልማዝ ባለጭራ በኋላ የሚከሠሰት የነርቭ ሕህመም (Postherpetic neuralgia)
-
ይህ ሽፍታው ከተከሠሰተበት ጊዜ ጀምሮ በተመሳሳይ የሰውነት ክፍል ላይ ቢያንስ ለ 3 ወራት የሚቆይ ሕመም እና ማቃጠል ሲኖር ነው። ሕመሙ ከቀላል እስከ ኑሮን ሊያውክ የሚችል ከባድ ማቃጠል እና ውጋት ሊደርስ ይችላል።
-
አብዛኛውን ጊዜ ህመሙ ከጊዜ በኋላ እየቀነሰ ቢሔድም አንዳንድ ጊዜ ግን እየተመላለሰ ለወራት ወይም ለዓመታት ሊዘልቅ ይችላል። ስለዚህ ሕመሙን ለማስታገስ የጤና ባለሙያዎች የተለያዩ መድኃኒቶችን ሊያዝዙ ይችላሉ።
የዐይን ችግር
-
ይህ የአልማዝ ባለጭራ ሽፍታ ዐይን፣ ግንባር እና አፍንጫ አካባቢ ሲከሠሰት ሊያጋጥም የሚችል ከባድ የዐይን ችግር ነው።
-
ይህ ሕመም በአግባቡ ካልታከመ ዕይታን ሊያሳጣ ስለሚችል፤ በእነዚህ አካባቢዎች ላይ ሽፍታ ሲከሠሰት በፍጥነት የጤና እርዳታ ማግኘት ያስፈልጋል።
የቆዳ ኢንፌክሽን
-
አንዳንድ ጊዜ ሽፍታው ሊቆስል እና ቆዳችን በሽታ አምጪ በሆኑ ተዋሕዋስያን ሊበከል ይችላል። ይህም በቆዳችን ላይ ጠባሳ ሊፈጥር ይችላል። ስለዚህ ከፍተኛ ትኩሳት ወይም መግል በሚኖርበት ጊዜ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ያስፈልጋል።
የጆሮ ብግነት ወይም መቆጣት
-
በተጎዳው ጆሮ በኩል የፊት ጡንቻ መስነፍ (የፊት መጣመም)፣ የጆሮ ሕህመም እና በጆሮ ውስጥ ሽፍታ መውጣት ምልክቶቹ ናቸው። ብዙውን ጊዜ በፀረ -ቫይረስ መድኃኒት እና ብግነትን በሚቀንሱ መድኃኒቶች (Steroids) ይታከማል።
ያልተለመደ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ አልማዝ ባለጭራ በሳንባ ፣ በአንጎል እና በጉበት ላይ ለሞት የሚዳርግ ውስብስብ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል።
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ምርመራዎች ምንድን ናቸው?
የጤና ባለሙያዎች ሽፍታውን በማየት እና ስለምልክቶቹ በመጠየቅ ስለበሽታው መረዳት ይችላሉ። እንዲሁም ከሽፍታው ላይ ናሙና በመውሰድ ምርመራ ሊደረግ ይችላል።
የአልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) ሕክምና
-
በቤት ውስጥ የሚደረግ ሕክምና
-
ሽፍታው የአለበትን አካባቢ ንጽሕፅህና መጠበቅ፣ በተጨማሪም እርጥበት እንዳይኖር በጥንቃቄ ማድረቅ
-
ቆዳን የበለጠ ሊጎዱት ስለሚችሉል እርጥበት ያላቸውን ቅባቶች እና ክሬሞችን ማስወገድ
-
የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ በቂ ዕረፍት ማድረግ
-
ሰፋ ያሉ እና ምቾትን የሚሰጡ ልብሶችን መልበስ
-
የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማድረግ፣ ውጥረትን መቀነስ
-
በሕክምና ተቋማት ውስጥ የሚደረጉ ሕክምናዎች
-
የፀረ -ቫይረስ መድኃኒቶች፤ ፣ እነዚህ መድኃኒቶች የቫይረሱን መራባት ለማገድ፣ የሕመሙን ክብደት እና ቆይታ ለመቀነስ እና ሽፍታው በፍጥነት እንዲድን ለማድረግ ያግዛሉ። በተለይም ሽፍታው በተከሠሰተ በ72 ሰዓአታት ውስጥ መወሰድ ከተጀመሩ ውጤታቸው ጥሩ ይሆናል።
-
የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች፤፣ አንዳንድ ጊዜ ሕመሙ ከባድ ሊሆን እና የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶች ሊታዘዙ ይችላሉ።
-
የ ፀረ ተሕዋስያን መድኃኒቶች፤ ፣ ቆዳ በበሽታ አምጪ ተሕዋስያን ከተበከለ እና ኢንፌክሽን ከተፈጠረ አንቲባዮቲክስ መድኃኒቶች ይታዘዛሉ።
አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster) መከላከያ መንገዶች
-
ሕፃናት የጉድፍ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ማድረግ
-
በአደጉት አገራት ዕድሜያቸው ከ 50 በላይ ለሆኑ ሰዎች የአልማዝ ባለጭራ መከላከያ ክትባትን እንዲወስዱ ይደረጋል።
-
የአልማዝ ባለጭራ ታማሚ እስኪያገግምሙ ድረስ ርቀትን መጠበቅ ያስፈልጋል። በተለይም የጉድፍ ክትባትን ከአልወሰዱ ወይም በጉድፍ ተይዘው የማያውቁ ከሆነ ይህን ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል።