ሃይድሮሴፋለስ | Hydrocephalus
ሃይድሮሴፋለስ:- የአንጎል እና ህብለሰረሰር ፈሳሽ ኡደት መዛባትን ተከትሎ የሚመጣ የፈሳሽ መከማቸት ሲሆን ይህም በአንጎል ላይ ግፊት አና ጫና በማምጣት ብዙዎችን ለሞት የዳረገ ህመም ነው::
በህፃናት አና በአዋቂዎች አመጣጡ እና የሚያሳየው ባህሪ ይለያያል:: የህፃናት የራስ ቅል በቶሎ ስለማይገጥም ግፊቱ ሲጨምር በማደግ ትልቅ ጭንቅላት ይኖራቸዋል::
የፈሳሹ መከማቸት አንጎሉን ከራስ ቅል ጋር ስለሚጫነው እድገታቸው ዘገምተኛ ይሆናል:: ይህም ማለት ራሳቸዉን ችለው መቀመጥ በሚገባቸው ሰዓት ያንን ማድረግ ያዳግታቸዋል:: መናገር የሚገባቸዉን ያክል መናገር ይቸገራሉ:: ቀስበቀስ እይታቸው ሊጠፋ ይችላል:: አለፍ ሲል ደግሞ ለሞት ይዳርጋል ::
የራስ ቅል ከገጠመ በኋላ (በመሃል አናት ትር ትር የሚለው ሲጠፋ) የፈሳሹ ግፊት በቶሎ ስለሚጨምር በጣም ድንገተኛ እና ካልታከመ ለሞት ይዳርጋል::
በአብዛኛው በህፃናት ላይ የሚከሰትበት ምክንያት በተፈጥሮ ሲሆን ተያያዥ የነርቭ ዘንግ ክፍተት ችግር ሊኖራቸው ይችላል:: የጨቅላ ሕፃን ኢንፌክሽን ተከትሎ ሊመጣ ይችላል:: ሌላኛው እና በቶሎ መታከም የሚገባው የህፃናት አንጎል እጢ(Brain tumor) ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን ነው::
ሕክምናዉም የፈሳሹን መስመር ማስተካከል ሲሆን…
1: በቱቦ (shunt catheter ) ከአንጎል ወደ ሆድ (Peritoneal space)ወይም ወደ ሌላ ክፍል (pleura or atrium) እንዲፈስ ይደረጋል:: ቱቦው ከቆዳ ስር የሚያልፍ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ እድሜ ሙሉ የሚቆይ ነው::
2: በ ኢንዶስኮፕ (Endoscopic ventriculostomy) የፈሳሹን መስመር መክፈት
3: መስመሩን የዘጋዉን ዕጢ በቀዶ ጥገና ማስወገድ
4: ጊዜያዊ ማስታገሻ መድኃኒቶችን መጠቀም
5: አንዳንዴ ፈሳሹ ወደ ዉጭ በተዘጋጀለት ማጠራቀሚያ እንዲፈስ ማድረግ እና ሌሎችም..
ይህ መታከም የሚችል ችግር ነው።


