Pediatric GERD (መደበኛ ያልሆነ ቅርሻት) ምንድን ነው?
GERD ወይም ቅርሻት ማለት ለረጅም ጊዜ የሚቆይ (ስር የሰደደ) የጨጓራና የምግብ ቧንቧ ችግር ነው። ምግብ ወይም ፈሳሽ ከጨጓራ ወደ ላይ ተመልሶ ወደ ምግብ ቧንቧ (esophagus) ሲፈስ የሚከሰት ችግር ነው።GERD የበለጠ ከባድ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ የቅርሻት አይነት ነው።
መደበኛ የሆነ ቅርሻት(GER) ከ 2 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የተለመደ ነው።መደበኛ ቅርሻት በህፃናት ላይ ምንም አይነት ችግር አይፈጥርም::በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ከ12 እስከ 14 ወራት ዕድሜ ላይ ሲደርሱ በራሱ ይጠፋል።
ከ 2 እስከ 19 አመት ለሆኑ ህጻናት እና ታዳጊዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጨምር ቅርሻት (GER) መኖሩ የተለመደ ነው።ይህ ማለት ሁልጊዜ መደበኛ ያልሆነ ቅርሻት(GERD) አለባቸው ማለት አይደለም።
መደበኛ ቅርሻት (GER) መደበኛ ያልሆነ ቅርሻት (GERD) በሚሆንበት ጊዜ መቼ ነው?
ህፃናት ወይም ታዳጊዎች በሚከተሉት ሁኔታዎች GERD ሊኖራቸው ይችላል፡-
• ምልክቶቹ ከመመገብ የሚከለክሉ ከሆነ። እነዚህም ምልክቶች ማስመለስ፣ ማሳል እና የመተንፈስ ችግርን ሊያካትቱ ይችላሉ።
• ከ12 እስከ 14 ወራት በላይ ከቀጠለ ወይም በሳምንት ከ 2 ጊዜ በላይ ለወራት ከቆየ።
- የጨጓራ ይዘት ወደ ጉሮሮ መመለስ (GER): ይህ ማለት በውስጣችን ያለው የጨጓራ ይዘት (የተዋሃደ ምግብ እና አሲድ) ያለፍላጎታችን ወደ ጉሮሮ (esophagus) መመለሱ ነው።
- በተለይም በጨቅላ ህፃናት ላይ ምግብ ከተመገቡ በኋላ ትንሽ መጠን ያለው ወተት የመመለስ ሁኔታ የተለመደ ስለሆነ እንደ ጤናማና ተፈጥሯዊ ሂደት (ፊዚዮሎጂያዊ ክስተት) ይቆጠራል።
- የጨጓራና ትራክት ሪፍሌክስ በሽታ (GERD): ይህ የሚፈጠረው የጨጓራ ይዘት ወደ ጉሮሮ መመለስ (GER) በየጊዜው ሲከሰት እና የሚያስቸግሩ ምልክቶችን ወይም የጤና ችግሮችን/ውስብስቦችን ሲያስከትል ነው።
- ለምሳሌ የልብ መቃጠል (Heartburn - ቃር የሚባለው) ወይም የጉሮሮ መቆጣት (esophagitis) ሊያስከትል ይችላል።
- ይህ በሽታ በሁሉም የህፃናት የዕድሜ ክልሎች በጣም ከተለመዱት የሆድና የጉሮሮ ምልክቶች ዋና ምክንያቶች አንዱ ነው።
GERD (መደበኛ ያልሆነ ቅርሻት) በምን ይከሰታል?
-ብዙውን ጊዜ በታችኛው የምግብ ቧንቧ (esophagus) ላይ የሚገኘው ጡንቻ(Lower esophageal Sphincte) ችግር ይከሰታል::ይህ ጡንቻ ከምግብ ቧንቧ (esophagus) በታች ያለ ጡንቻ ነው። ይህም ምግብ ወደ ሆድ (ጨጓራ) እንዲገባ ይከፈታል። ምግብን በሆድ ውስጥ ለማቆየት እና ወደ ምግብ ቧንቧ እንዳይመለስ ይዘጋል።ይህ ጡንቻ በጣም ለብዙ ጊዜ ሲላላ የሆድ አሲድ ወይም ምግብ ወደ ጉሮሮ ይመለሳል። ይህም ማስታወክ ወይም ቅርሻን ያስከትላል።
ጨቅላ ሕፃናት የሆድ ይዘትን የመመለስ ወይም "የማስመለስ" (Regurgitation) ሁኔታ በተለይ የተለመደ ነው።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህ ክስተት ያለባቸው የሕፃናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፦
- በመጀመሪያው ወር የእድሜ ዘመን አካባቢ 80% ያህሉ ሕፃናት የማስመለስ ክስተት ያጋጥማቸዋል።
- ይህ ቁጥር በአንድ ዓመት ዕድሜ ላይ ደግሞ ከ10% በታች ይሆናል።
ይህ ቅነሳ አብዛኛው ጊዜ የሚከሰተው ሕፃናቱ እያደጉ ሲሄዱ የሆድ እና የጉሮሮ መሀል ያለው ጡንቻ (Lower Esophageal Sphincter) እየጠነከረ በመምጣቱ ነው።
ሁሉም ሰው አልፎ አልፎም ቢሆን ይህ ችግር ሊኖረው ይችላል።አፍ ውስጥ የሚመር እና የአሲድ ጣዕም ከተሰማዎ ይህ ችግር (Reflux) አጋጥሞዎታል ማለት ነው።አንዳንድ ጊዜ ይህ ጡንቻ በተሳሳተ ጊዜ ሊላላ ይችላል። ብዙውን ጊዜ ህፃናት በአፋቸው ውስጥ መጥፎ ጣዕም ይኖራል ወይም ልጆች አጭር እና መለስተኛ የሆነ የልብ ህመም (heartburn) ስሜት ሊኖረው ይችላል።
-ጨቅላ ህጻናት ለደካማ ጡንቻ የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው። ይህም ተዘግቶ መቆየት ሲገባው እንዲላላ ያደርገዋል። ምግብ ወይም ወተት እየተዋሃዱ ሲሄዱ የታችኛው ጉሮሮ ይከፈታል። የሆድ ዕቃው ወተት ወደ ጉሮሮው ተመልሶ እንዲሄድ ያስችለዋል። አንዳንድ ጊዜ የሆድ ዕቃው ወተት እስከ ጉሮሮው ድረስ አልፎ ይወጣል። ከዚያም ሕፃኑ ትውከት ይኖረዋል። በሌሎች ሁኔታዎች የሆድ ዕቃው ፈሳሽ ወደ ጉሮሮ ግማሽ ድረስ ብቻ የሚወጣው ከሆነ የልብ ህመም (heartburn) ወይም የመተንፈስ ችግር ያስከትላል። በአንዳንድ ሁኔታዎች ምንም ምልክቶች ላይታዩ ይችላሉ።
-አንዳንድ ምግቦች በጡንቻዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። እነዚህም ምግቦች እንደ ቼኮሌት ፤ ከፍተኛ ቅባት ያላቸው ምግቦች ሲሆኑ ሌሎች ምግቦችም ጨጓራ ብዙ አሲድ እንዲፈጠር ያደርጉታል። ይህም ሊያባብስ ይችላል።
-ለዚህ ችግር ተጋላጭ የሚያደርጉ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
•በሕፃን የመጀመሪያ አመት በጣም የተለመደ ነው። ብዙውን ጊዜ በራሱ ይጠፋል።
•ህፃናት የሚከተሉት ችግሮች ካሉባቸው የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።
•ዳውን ሲንድሮም : የነርቭ እና የጡንቻ ችግር(neuromuscular disorders) ያለባቸው ህፃናት (ለምሳሌ muscular dystrophy, cerebral palsy) ተጋላጭ ናቸው።
የGERD ምልክቶች ምንድን ናቸው?
•ቃር ወይም የምግብ አለመፈጨት በጣም የተለመደው የGERD ምልክት ነው።የሚያቃጥል የልብ ህመም (heartburn) እንደ የሚያቃጥል የደረት ሕመም ይገለጻል። ከደረት አጥንት ጀርባ ይጀምርና ወደ አንገት ይሰማል። እስከ 2 ሰዓት ድረስ ሊቆይ ይችላል። ከተመገባችሁ በኋላ ብዙ ጊዜ የከፋ ነው። ከምግብ በኋላ ወዲያው መተኛት ወይም መታጠፍ እንዲሁ ወደ ቃር ሊያመራ ይችላል።
ከ12 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ብዙ ጊዜ የተለያዩ የGERD ምልክቶች ይኖራቸዋል። ደረቅ ሳል፣ የአስም ምልክቶች፣ ወይም የመዋጥ ችግር ይኖርባቸዋል። የልብ ህመም(heartburn) ብዙውን ጊዜ አይኖራቸውም።እያንዳንዱ ልጅ የተለያዩ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል።
•የተለመዱ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
• ሆድ መንፋት : አለመብላት : የሆድ ህመም መኖር : በምግብ ሰዓት አካባቢ መበሳጨት : ብዙ ጊዜ ማስታወክ : ህቅታ መኖር : ትንታ : ብዙ ጊዜ ማሳል በተለይ በምሽት ሰዓት ላይ የተለመዱ ምልክቶች ናቸዉ::
•ሌሎች ምልክቶችም የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ-
• የአስም ምልክት(wheezing) : ብዙ ጊዜ ጉንፋን መያዝ : ብዙ ጊዜ የጆሮ ኢንፌክሽኖች : ጠዋት ላይ የጉሮሮ መቁሰል : በአፍ ውስጥ መራራ ጣዕም መኖር : መጥፎ የአፍ ጠረን መኖር : የጥርስ ሽፋን መበላሸት ወይም መበስበስ ሊታዩ ይችላሉ::
•የGERD ምልክቶች እንደ ሌሎች የጤና ችግሮች ሊመስሉ ይችላሉ። ስለዚህ ለምርመራ ልጅዎን ወደ ጤና ተቋም ወስደው በማሳየት ማረጋገጥ መልካም ነው።
እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ልዩ ባህሪ የሌላቸው (non-specific) ሲሆኑ፣ ከሌሎች በጨቅላነት ዕድሜ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች ጋር ሊመሳሰሉ ወይም በእነሱ ምክንያት ሊመጡ ይችላሉ።
ሊመሳሰሉ ወይም ሊከሰቱባቸው ከሚችሉት የጨቅላነት ችግሮች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፦
- የላም ወተት ፕሮቲን አለርጂ (Cow's milk protein allergy)
- ፓይሎሪክ ስቴኖሲስ (Pyloric stenosis) - በጨጓራ መውጫ ላይ የሚከሰት መጥበብ
- ማልሮቴሽን (Malrotation) - የአንጀት ትክክለኛ አቀማመጥ መዛባት
- ከመጠን በላይ መመገብ (Overfeeding)
- ትራኪዮ-ኢሶፋጂያል ፊስቱላ (Tracheo-esophageal fistula) - በንፋስ ቧንቧ እና በጉሮሮ መካከል ያለ ያልተለመደ ግንኙነት
- ሆድ ድርቀት (Constipation)
ስለዚህ፣ ትክክለኛውን ምርመራ (diagnosis) እና ሕክምና ለመወሰን ጥልቅ የሆነ የሕክምና ታሪክ (thorough medical history) መውሰድ እና አጠቃላይ የሕክምና ምርመራ (examination) ማድረግ ወሳኝ ነው።
እንዴት ነው የሚመረመረው?
•የልጅዎ ሐኪም የአካል ምርመራ ያደርጋል እና የጤና ታሪክ ይወስዳል። ሌሎች ምርመራዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ-
-የደረት ራጅ(CXR) : የላይኛው የአንጀት ክፍል ባሪየም ምርመራ (Upper GI series or Barium Swallow) ኢንዶስኮፒ(Endoscopy) : የምግብ ቱቦ የጡንቻ ምርመራ(Esophageal manometry) : ፒኤች ክትትል (PH monitoring) ሊያስፈልጉ ይችላሉ::
•GERD እንዴት ይታከማል?
-ሕክምናው የሚወሰነው በልጅዎ ምልክቶች፣ ዕድሜ እና አጠቃላይ ጤና ላይ ነው::እንዲሁም በሽታው ምን ያህል ከባድ እንደሆን ታይቶ ይወሰናል።
-የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች የመጀመሪያዉ እና ዋነኛዉ ነዉ::በብዙ አጋጣሚዎች የአመጋገብ እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች GERDን ለማቃለል ይረዳሉ።
•የGERD ምልክቶችን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር አንዳንድ ምክሮች አሉ።
-ለአራስ ሕፃናት:
°ከተመገቡ በኋላ ልጅዎን ለ30 ደቂቃዎች ቀጥ ባለ ቦታ ይያዙት : በጡጦ የሚመገብ ከሆነ የጡጦውን ጫፉ በወተት እንዲሞላ ያድርጉት። በዚህ መንገድ ልጅዎ በሚመገብበት ጊዜ ብዙ አየር አይውጥም። የተለያዩ የጡጦ ጫፎችን ይሞክሩ። በሚመገብ ወቅት የልጅዎ አፍ ከጡጦ ጫፍ ጋር በጥሩ ሁኔታ እንዲዘጋ የሚያደርገውን አንዱን ይምረጡ።ጡጦ በማጥባት ወይም ጡት በማጥባት ጊዜ ልጅዎን ያስገሱት ወይም አያወዛውዙት። የሞላ ጨጓራ ሲወዛወዝ ልጅዎ ብዙ ጊዜ እንደገና ሊያስመልስ ይችላል።
-ለትላልቅ ልጆች:
•የልጅዎን አመጋገብ ያስተካክሉ። የተጠበሱ እና የሰቡ ምግቦችን፣ ፔፐርሚንት፣ ቸኮሌት፣ እንደ ሶዳ እና ሻይ ያሉ ካፌይን ያላቸውን መጠጦች፣ ቆምጣጣ ፍራፍሬዎች እና ጭማቂዎችን እና የቲማቲም ምርቶችን ይገድቡ።


