ኮንታክት ደርማታይተስ (Contact Dermatitis) ምንድነው?

Tsion Girma
Nov 8, 2025
undefined

ኮንታክት ደርማታይተስ (Contact Dermatitis) ምንድነው?

ቆዳ የውስጥ አካላትን ከውጭ ባእድ ነገሮች የሚጠብቅ አስፈላጊ ክፍል ነው። ነገር ግን ከአንዳንድ ነገሮች ጋር ሲነካካ የቆዳ እብጠት ወይም መቅላት ሊፈጠር ይችላል። ይህንን ሁኔታ “ኮንታክት ደርማታይተስ” (Contact Dermatitis) ብለን እንጠራዋለን። የኮንታክት ደርማቲቲስ በአጠቃላይ ሁለት ዓይነት ነው፦ የኢራቲታንት እና የአለርጂ ደርማታቲስ።

 

 1. የኢሪቲታንት ኮንታክት ደርማታይተስ

 

ይህ ዓይነት  የቆዳ መቆጣት  በቀጥታ የኬሚካል ንክኪ ሊከሰት ይችላል ። በምሳሌ፣ ከውሃ፣ ሳሙና፣ እቃ ማጠቢያ ኬሚካሎች፣ መድሀኒቶች ጋር ንክኪ ሲኖር ይነሳል።  ምሳሌ፣ በቀን ብዙ ጊዜ እጆችን በመታጠብ ወይም አዘውትሮ ኬሚካል መጠቀም የቆዳ መቆጣት ሊያስከትል ይችላል።

 

 2. የአለርጂ ኮንታክት ደርማታይተስ

 

 የአለርጂ ኮንታክት ደርማታይተስ ከአንድ ነገር ጋር በመጀመሪያ ስንነካ ወዲያውኑ አይታይም፤ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ አካልዎ በዚያ ነገር ላይ መቆጣት ሊያመጣ ይችላል።

ምክንያቶቹ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፦

  • የብረት ጌጣጌጦች (እንደ ወርቅ ወይም ናይክል)
     
  •  የቀለም ንጥረ ነገሮች
     
  • ሽቶ 
     
  • አንዳንድ እፅዋቶች
     
  • የአንዳንድ መድሀኒቶች ክሬሞች
     

 የኮንታክት ደርማታይተስ የሚታዩ ምልክቶች

የኮንታክት ደርማታይተስ ምልክቶች  በአብዛኛው የሚታዩት፦

  • ቆዳ መቅላት  እና ቦታው ላይ የመሞቅ ስሚት
     
  • ቆዳን ማሳከክ
     
  • ቆዳ እብጠት 
     
  • አንዳንድ ጊዜ የእብጠት ቦታ መሰንጠቅ
     

 የሚደረጉ ምርመራዎች

የቆዳ ሐኪም (Dermatologist) የታካሚውን ታሪክ በመጠየቅ እና ቆዳውን በመመርመር ይጀምራል።
ከዚያ በኋላ እንደ Patch Test ያሉ ፈተናዎችን በመጠቀም የበሽታው መንስኤ ሊያስታውቅ ይችላል።
ይህ ፈተና የተለያዩ ንጥረ ነገሮችን በትንሽ መጠን በቆዳ ላይ በመተግበር የመለየት ሂደት ነው።

 

 ሕክምና እና መከላከያ መንገዶች

ሕክምና

  1. ከሚያባብሰው  ነገር መቆጠብ:
    ቆዳ መቆጣት  የሚያስከትለውን ነገር ካወቁ ከእርሱ መራቅ።
     
  2. የቆዳ ክሬሞች  መጠቀም:
    በተለይ እጅ እና ፊት የሚታይ ቆዳ መቆጣት ሲኖር  ቆዳ መድረቅ እንዳይኖር ክሬም መጠቀም አስፈላጊ ነው።
     
  3. የአለርጂ ክሬሞች :
    ሐኪም እብጠቱን ለመቀነስ የኮርቲዞን ክሬም ወይም በአፍ ሚወስድ መድሀኒት ሊያዝ ይችላል።
     
  4. የአለርጂይ መድሀኒቶች:
    የእብጠት እና መቅላት ስሜትን ለመቀነስ ይረዳሉ።
     

🔸 መከላከያ መንገዶች

  •  አንዳንድ ኬሚካል ሲነኩ እጅ ጓንት ይጠቀሙ ።
     
  • የእጅ መታጠቢያን ሳሙና ከመጠን በላይ አይጠቀሙ።
     
  • ቆዳን ሚያለሰልሱ ክሬሞችን በየቀኑ ይጠቀሙ ።
     
  • ከኬሚካል ንጥረ ነገሮች ይልቅ የተፈጥሮ ነገሮችን ይምረጡ።

     

Comments (0)