የውሃ መጠጫ ኮዳዎን በየስንት ጊዜው መቀየር እንዳለብዎ ያውቃሉ?

Elsabet Azezew
Nov 22, 2025
undefined

                      የውሃ መጠጫ ኮዳዎን በየስንት ጊዜው መቀየር እንዳለብዎ ያውቃሉ?

       የውኃ መጠጫ ኮዳ በእለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ስፖርት በምንሰራበት ጊዜ፣ ለስራ፣ለትምህርት ቤት እንዲሁም ለጉዞ አስፈላጊ የሆነ ብዙዎቻችን አዘውትርዎ የምንጠቀምበት እቃ ነው። ነገር ግን ብዙዎቻችን የውኃ መጠጫ ኮዳዎቻችንን በየስንት ጊዜ መቀየር እንዳለብን አናውቅም። 

      ምንም እንኳን ብዙ የውኃ ኮዳዎች ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ታስበው የተሰሩ ቢሆንም ንፅህናቸውን እና ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ተገቢውን እንክብካቤ መደረግ እና በየጊዜው መቀየር ያስፈልጋል። 

       የውኃ ኮዳዎን በምን ያህል ጊዜ መቀየር እንዳለብዎ የሚወስኑ የተለያዩ ነገሮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኮዳዎ አይነት፣ የአጠቃቀሞ መጠን እና የአያያዞ ሁኔታ ይጠቀሳሉ። 

                     የኮዳዎ አይነት ወይም የተሰራበት እቃ 

የፕላስቲክ ኮዳ 

     የፕላስቲክ ኮዳ ከሆነ የሚጠቀሙት እንደ የተሰራበት ፕላስቲክ ጥራት እና እንደ አጠቃቀሞ መጠን በየ6 እስከ 12 ወሩ ቢቀየር ይመረጣል። በጊዜው ካልተቀየረ ከጊዜ በኋላ ፕላስቲኩ እየተበላሸ በመሄድ ባክቴሪያዎች ሊራቡበት የሚችሉ ስንጥቆችን ሊፈጠር ይችላል።

የጠርሙስ ኮዳ 

     የሚጠቀሙት የጠርሙስ ኮዳ ከሆነ ደግሞ ምንም አይነት ጎጂ ባክቴሪያዎች እንዳይራቡበት  ለማረጋገጥ በየ2 እስከ 3 ዓመቱ መለወጥ ይኖርቦታል። 

ከማይዝግ ብረት የተሰራ የውኃ ኮዳ 

     ጥራት ካለው የማይዝግ ብረት የተሰራ የውኃ ኮዳ በአግባቡ ከተያዘ ለዓመታት ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። ሆኖም ግን ዝገት፣ መጠርመስ ወይም ከጽዳት በኋላም የማይጠፋ መጥፎ ሽታ እና ጣዕም ካመጣ ኮዳውን መቀየር ተገቢ ነው። 

                  የውሃ መያዣዎን ለመለወጥ ጊዜው እንደደረሰ የሚያሳዩ ምልክቶች

   የተሰራበት እቃ ምንም ይሁን ምን አዲስ ኮዳ መቀየር እንዳለብዎ የሚጠቁሙ ምልክቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ

  • ከታጠበ በኋላም የማይጠፋ መጥፎ ሽታ እና ጣዕም  
  • የሚታይ መሰንጠቅ ካለ 

         ትንሿ መሰንጠቅ እንኳን ባክቴሪያዎችን ደብቆ በመያዝ ለማፅዳት የሚያደርጉትን ጥረት ከንቱ ያደርገዋል።

  • በኮዳው ወይም በክዳኑ ላይ ሻጋታ ካስተዋሉ
  •  የሚያፈስ ወይም በትክክል የማይዘጋ ክዳን ካለው የውሃ መጠጫ ኮዳዎን ቶሎ መቀየር ይኖርቦታል። 

                የውኃ መጠጫ ኮዳዎን ዕድሜ ለማርዘም የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮች

   የውኃ መጠጫ ኮዳዎን በተቻለ መጠን ለረጅም ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ለማቆየት የሚከተሉትን ምክሮች ይከተሉ

  • የውኃ መጠጫ ኮዳዎን በየቀኑ ይጠቡ

         ሁልጊዜ ኮዳዎን ከተጠቀሙበት በኋላ ለብ ባለ ውሃ እና በእቃ ሳሙና ይጠቡት።

  • በየሳምንቱ ጥልቅ ጽዳት ያድርጉለት

         ባክቴሪያዎችን እና የተከማቸውን ቆሻሻ ለማስወገድ በየሳምንቱ ኮምጣጤ (vinegar) እና ቤኪንግ ሶዳ (baking soda) በመጠቀም በደንብ ያፅዱት።

  • ኮዳዎን ከከፍተኛ ሙቀት ይጠብቁ

         በተለይም ከፕላስቲክ የተሰሩ ኮዳዎች ከልክ ላለፈ ሙቀት ሲጋለጡ ሊበላሹ ስለሚችሉ ከከፍተኛ ሙቀት ይጠብቋቸው።

  • ኮዳዎን ሲያጥቡ የጠርሙስ ብሩሽ (Bottle Brush) ይጠቀሙ  

         የጠርሙስ ብሩሽ በተለይ ጠባብ አፍ ያላችውን ኮዳዎች በደንብ ውስጣቸውን ለማፅዳት ይረዳል ።

Comments (0)