ሂቢስከስ(ከርከዴ ሻይ)

Rediet Tadesse
Dec 12, 2025
undefined

ሂቢስከስ(ከርከዴ) ምንድነው?

አሁን አሁን ተፈጥሮ የሆኑ መድሃኒቶችን ፍለጋ እና ጤናን የሚያሻሽሉ ነገሮችን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተወዳጅነት አግኝቷል። ለብዙ የጤና ጥቅሞቹ ከፍተኛ ተቀባይነት ካገኘ ከእነዚህ ጤናን ከሚያሻሽሉ መካከል አንዱ ሂቢስከስ ነው። የሂቢስከስ ተክል ደማቅ የአበባ ቅጠሎች ቀለም ያለው ሲሆን ለእይታ ማራኪ ብቻ ሳይሆን ለጤናም ጠቃሚ በሆኑ ነገሮች የተሞላ ነው። አንቲኦክሲዳንት (Antioxidants) የበለፀገ ሲሆን ብዙ ጠቃሚ ጥቅሞችን ይሰጣል። በተለይም ክብደትን ለመቀነስ፣ የባክቴሪያ እና የካንሰር ሕዋሳትን እድገት ለመቀነስ እንዲሁም የልብ እና የጉበት ጤናን ለመጠበቅ ይረዳል።

 

የሂቢስከስ ሻይ የሚከትሉትን ንጥረ ነገሮች ይዟል፦

የሂቢስከስ ሻይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የኃይል ምንጭ ነው። በአንቲኦክሲዳንት ፣ ቪታሚኖች እና ማዕድናት የበለፀገ ሲሆን እነዚህም፡-

  • ቫይታሚን ሲ፦ ቫይታሚን ሲ በሽታ የመከላከል ስርዓትን ለማጠናከር ይረዳል።
  • ብረት፦ ለቀይ የደም ሴሎች ፤ ለአእምሮ እና የደም ማነስን ለመከላከል አስፈላጊ ነው።
  • ካልሲየም፦ ለአጥንት ጤና እና ለጡንቻዎች ተግባር አስፈላጊ።
  • ማግኒዥየም፦ ጡንቻዎችን ዘና ለማለት እና ለአጠቃላይ የነርቭ ጤንነትን 
  • ፖሊፊኖልስ፦ እነዚህ ፀረ-ንጥረ-ምግቦች ኦክሳይድን ለመዋጋት ይረዳሉ ወጥረት እና እብጠትን ይቀንሳል።

1.አንቲኦክሲደንት ባህርያት

በሂቢስከስ ውስጥ ያለው ከፍተኛ አንቲኦክሲዳንት ይዘት በተለይም አንቶሲያኒን በሰውነት ውስጥ ያሉትን ነፃ radicals በማጥፋት ይረዳል። ፍሪ radicals በሴሉላር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ያልተረጋጉ ሞለኪውሎች ናቸው ሥር የሰደዱ በሽታዎች እና ያለጊዜው እርጅናን ያመጣሉ። በመሆኑም ሂቢስከስ በኃይለኛ አንቲኦክሲደንትስ የበለፀገ በመሆኑ የፍሪ radicals መከማቸትን ጉዳት እና በሽታን ለመከላከል ይረዳል። እንዲሁም ውጥረትን በመቀነስ እና በደም ውስጥ ያለው የፀረ-ኦክሳይድ መጠን ይጨምራል።

 

2. የደም ግፊትን ለመቀነስ 

የሂቢስከስ በጣም አስደናቂ እና ታዋቂ ከሆኑት ጥቅሞች አንዱ የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳል።

ከጊዜ በኋላ ከፍተኛ የደም ግፊት በልብ ላይ ተጨማሪ ጫና ስለሚፈጥር እንዲዳከም ያደርጋል። የሂቢስከስ ሻይ ሲስቶሊክ እና ዲያስቶሊክ የደም ግፊትን በመቀነስ ከፍተኛ የደም ግፊትን እና በግፊት ምክንያት ለሚመጣ የልብ ሕመም የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።

የሂቢስከስ የደም ግፊትን ለመቀነስ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተፈጥሯዊ መንገድ ሊሆን ቢችልም ከደም ነገር ግን ከግፊት መድሃኒቶች ጋር መውሰድ አይመከርም። 

 

 3. በደም ውስጥ የሚገኝ የስብ መጠንን ለማሻሻል 

የደም ግፊትን ከመቀነሱ በተጨማሪ የሂቢስከስ በደም ውስጥ ስብን ለመቀነስ ይረዳል። ሂቢስከስ የ LDL (መጥፎ) የኮሌስትሮል መጠን እንዲቀንስ እና HDL (ጥሩ) የኮሌስትሮል መጠንን ከፍ በማድረግ የልብ ጤናን ለመጠበቅ እና አተሮስስክሌሮሲስ በሽታን ለመከላከል ወሳኝ ነው። በተጨማርም ለሜታቦሊክ

እና ትራይግሊሰርራይድ መጠን ሊቀንስ ይችላል

 

4. የጉበት ጤናን ይጨምራል

ጉበት ብዙ ተግባራት አሉት እንደ ፕሮቲኖች ማምረት ፣ ሐሞትን ማውጣት እና ስብን መሰባበር ሂቢስከስ ለአጠቃላይ ለጉበት ጤና አስፈላጊ ናቸው።ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሂቢስከስ የጉበት ጤናን እንደሚያበረታታ እና ጉበት በብቃት እንዲሠራ ሊረዳ ይችላል። እንዲሁም የጉበትን ጉዳት በመቀነስ እና በጉበት ውስጥ የሚፈጠርን ስብ በመከላከል ሊጠቅም ይችላል።

 

5. ክብደት ለመቀነስ

ክብደትን ለመቆጣጠር የሂቢስከስ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ዝቅተኛ የካሎሪ ይዘት ያለው እና ለስኳር መጠጦች ሌላ ጤናማ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ለሜታቦሊዝም፦ ሂቢስከስ ሻይ ሜታቦሊዝምን ከፍ የሚያደርግ እና ካሎሪን በማቃጠል ክብደት ለመቀነስ እና ጤናማ ክብደትን ለመጠበቅ ይረዳል።

የምግብ ፍላጎት ቁጥጥር፦ የምግብ ፍላጎትን ለመቀነስ የሚረዱ ውህዶችን ይዟል, ይህም ከተመጣጣኝ አመጋገብ ጋር ይያያዛል።

 

6. ካንሰርን ለመከላከል የሚረዱ ውህዶችን ይዟል

ሂቢስከስ በpolyphenols ከፍተኛ ነው፣ እነዚህም ውህዶች ፀረ-ነቀርሳ ባህሪያት እንዳላቸው የተረጋገጠ ነው።

  • የአፍ እና የፕላዝማ ሕዋስ ካንሰር ወራሪነት ቀንሷል።
  • የፕሮስቴት ካንሰር ሕዋሳት እንዳይሰራጭ ይከላከላል።
  • የጡት ፣ የሆድ እና የቆዳ ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች የካንሰር ሴሎችን እድገትን ይገታል። እንዲሁም የበርካታ የካንሰር ሕዋሳት እድገትን እና ስርጭትን ይቀንሳል። 

7. የባክቴሪያዎችን እድገት ለመቀነስ

ባክቴሪያዎች ለጤናዎ ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥሩ ባክቴሪያዎች ልክ እንደ አንጀት ውስጥ እንደሚገኙ ለምግብ መፈጨት እና የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያጠናክራሉ።  ጎጂ ባክቴሪያዎች እንደ ኢንፌክሽኖች እና እንደ ብሮንካይተስ እና ዩቲአይ(uti) ያሉ ብዙ የጤና ችግሮችን ያስከትላሉ።

የሂቢስከስ መጠጣት ሰውነትን ከነዚህ ጎጂ ባክቴሪያዎች ለመጠበቅ ይረዳል። በፀረ-ባክቴሪያዎች የበለፀገ ባህሪ ስላለው በአጠቃላይ ጤናን ለመጠበቅ እና ኢንፌክሽኖችን እንደባክቴሪያዎች እንደ ብሮንካይተስ፣ የሳምባ ምች እና የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽኖች ያሉ የተለያዩ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ይረዳል።

 

8. ሂቢስከስ ሻይ ለምግብ መፈጨት ጤና

የምግብ መፈጨት ችግር አጠቃላይ ጤናን እና ደህንነትን በእጅጉ ሊጎዳ ይችላል። ሂቢስከስ ሻይ ጤናማ የምግብ መፍጫ ሥርዓትን ለመጠበቅ ይረዳል።

ተፈጥሯዊ ዳይሪቲክ(Diuretics) ሂቢስከስ ሻይ እንደ ተፈጥሯዊ ዳይሬቲክ ሆኖ ይሠራል ፣ ይህም ከመጠን በላይ ፈሳሾችን እና መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ያስወግዳል። ይህም የሆድ እብጠትን ይከላከላል እና የተሻለ የኩላሊት ተግባርን ያበረታታል።

የምግብ መፈጨት እርዳታ፦ የምግብ መፈጨትን ለማሻሻል እና የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል። እንዲሁም ለጤናማ የምግብ መፍጫ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑትን ጠቃሚ የአንጀት ባክቴሪያ እድገትን ያበረታታል።

 

 9. ለቆዳ ጤና

የሂቢስከስ ጥቅሞች ከውስጥ ጤና በዘለለለ ለቆዳ የፀረ-ባክቴሪያ ይዘት ስላለው ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣል። እንዲሁም 

የፀረ-እርጅና፦  በሂቢስከስ ውስጥ የሚገኙት አንቲኦክሲዳንቶች የቆዳ መሸብሸብን እና ፊት ላይ የሚወጡ መስመሮችን በመቀነስ ከእርጅና ጋር ተያይዞ የሚመጣን የፊት መጨማደድን ለመቀነስ እና ቆዳ  አንጸባራቂ እና ውጥር ያለ እንዲሆን ይረዳል። 

ብጉር ለመከላከል፦ ተፈጥሯዊ ፀረ-ባክቴሪያ ስላለው እና እንዲሁም በብዛት የብጉር መንስኤ የሆነውን ከልክ ያለፈ የፊት ወዝ ምርትን ለመቆጣጠር ይረዳል።

 

10. ለኩላሊት ጤና

ኩላሊት ከደም ውስጥ ቆሻሻን የማጣራት ተግባራት ሲኖረው ሂቢስከስ ጤናማ የኩላሊት ስራን ያሻሽላል። የሂቢስከስ ከኩላሊት ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ፤ የኩላሊት ጠጠርን እና የኩላሊት ጠጠር ዋነኛ መንስኤ የሆነውን የካልሲየም ኦክሳሌት ክሪስታሎች እንዳይፈጠር ይከላከላል። ኩላሊትን በጥሩ ሁኔታ ማቆየት ለአጠቃላይ ጤና አስፈላጊ ነው። የሰውነት ፈሳሾችን በማመጣጠን ቆሻሻን ለማስወገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። 

 

11. የደም ስኳርን ለመቆጣጠር 

የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር በተለይም ለስኳር ህመምተኞች ወሳኝ ነው። ሂቢስከስ ሻይ በደም ውስጥ ያለውን ስኳር መጠን ዝቅ ለማድረግ ይረዳል።

በሂቢስከስ ውስጥ ያሉት ውህዶች ሰውነታችን ለኢንሱሊን የተሻለ ምላሽ እንዲሰጡ ስለሚረዱ ሰውነት ግሉኮስን ለመጠቀም ቀላል ያደርገዋል። በተለይ ዓይነት 2 የስኳር በሽታ ላለባቸው ሰዎች ጠቃሚ ነው። የተረጋጋ የደም ስኳር መጠን እንዲኖር እና ከስኳር በሽታ ጋር የተዛመዱ ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል ። የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ይህ ተፈጥሯዊ ተክል በጣም ጠቃሚ ነው።

Comments (0)