የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምንድነው? ምን ላድርግ።
.
♠የሰው ልጅ አጥንት የሚገባውን ያክል የካልሲየም ክምችት ሳይኖረው ሲቀር እና ደካማ ሲሆን የአጥንት መሳሳት(Osteoporosis) ይባላል። በዚህ ጊዜ አጥንት በቀላሉ ተሰባሪ ይሆናል።
♠ሁሉንም የሰው ዘሮች እና ሁለቱንም ጾታዎች የሚያጠቃ ሲሆን በተለዬ ተጠቂ የሆኑ አካላት አሉ፦
-አፍሪካዊያን
-ኤሲያዊያን
-እና ሴቶች የበለጠ ተጠቂ ናቸው።
♠መንስዔዎቹ፦
-እርጅና
-ሴት መሆን
-ከቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ መኖር
-በጣም ቀጭን መሆን
-የሆርሞን መዛባት(የመራቢያ ሆርሞን፣የጎይተር ሆርሞን)
-የአመጋገብ ሥርአት መዛባት(በጣም ቀጭን ለመሆን ራስን ማስራብ፣ካልሲዬም ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ
ምን ላድርግ?
♠መቼ ወደ ህክምና ልሂድ?
-ከቤተሰብ ውስጥ በአጥንት መሳሳት ምክንያት የዳሌ ስብራት ተከስቶ ከነበር
-የወር አበባ ከ45 እድሜ በፊት ከቀረ
-እድሜ ሲገፋ ወንድ ከ70 ዓመት ሴት ከ50 ዓመት እድሜ በላይ
-የአጥንት መሳሳት ሊያመጡ የሚችሉ መድሐኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ።
♠ምን ችግርን ያስከትላል?
-በቀላሉ የመሰበር እድል ከሌሎች ከፍ ያለ ይሆናል።
-የጀርባ አጥንት(Vertebral bone #)፣የዳሌ አጥንት ሥብራት፣የመዳፍና የክርን አጥንት ሥብራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
-የዳሌ የአጥንት ሥብራትን ተከትሎ በሽተኛውን ለተጨማሪ እንገልትና ስቃይ ብሎም ቶሎ ካለረታከመ ለሞት ይዳርጋል።
♠እንዴት መከላከል ይቻላል?
-በሐኪም የሚሰጥን የቅድመ መከላከል ምክር ተግባራዊ ማድረግ
-የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
-የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል። በካልሲየምና በቫይታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
አልኮል በጤናችን ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖ
ጤናችን ውድ ሀብታችን ነው። አልኮል በሰውነታችን ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት በጥበብ በመገንዘብ የምንወስዳቸውን ውሳኔዎች ማስተካከል ለረጅም እና ጤናማ ህይወት ወሳኝ ነው። ዛሬውኑ ለጤናዎ አወንታዊ እርምጃ ይውሰዱ!


