ወንዶች ለምን በራሰ በራነት ይጠቃሉ? እርስዎስ ምን ማድረግ ይችላሉ?

Asteraye Belay
Jan 5, 2026
undefined

የጸጉር መመለጥ/መሳሳት በ አለማቀፍ ደረጃ በወንዶች ዘንድ የተለመደ የውበት እንዲሁም ስነልቦናዊ ጫና የሚያሳድር ተፈጥሮአዊ ክስተት እንደሆነ ይታወቃል። በተለይም ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑ ወንዶች በ50ኛ አመታቸው ከጸጉር መሳሳት አይነቶች በአንደኛው እንደሚጠቁ ጥናቶች ያሳያሉ። ይሄ ደግሞ የተለያየ ቅርጽ፤ መልክ እና ደረጃ ሊሆን ይችላል። 

በአብዛኛው ጊዜ በሁለት አይነት መልኩ የሚጀምር ሲሆን ይህም ከፊት ለፊት መሸሽ (receding hairline) ወይም ደግሞ የዘውድ መሳሳት (thinning crown); በመነሳት ይስፋፋል። 

በአብዛኛው የጸጉር መመለጥ መነሻ ምክንያት androgenic alopecia (male pattern baldness) ሲሆን ራሰ በራነት በመባል ይታወቃል። ይህ ሁኔታ በዘር የሚወረስ ሲሆን ፤ በጽጉር ስሮች የቴስቴስትሮን ተጋላጭነት የሚወሰን ነው። ዳይሃይድሮ ቴስቴስትሮን በመባል የሚታወቀው ሆርሞን በተጋላጭ ወንዶች ላይ የጸጉር ስር መቀጨጭ ያስከትላል። ይሄ ደግሞ ቀስ በቀስ ቀጫጫ እና አጫጫር ጸጉሮች (baby hair) እንዲበቅሉ በመቀጥል ደግሞ ሙሉ በሙሉ የጽጉር እድገት እንዲቆም ያደርጋል። 

ነገር ግን ይሄ ችግር በዘር ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ፤ እንደ ጭንቀት፤ ድንገተኛ ክብደት መቀነስ፤ ደካማ አመጋገብ፤ ስር የሰደዱ ህመሞች ፤ የሆርሞኖች መዛባት እንዲሁም አንዳንድ መድኃኒቶች ራሰ በራነትን ሊያፋጥኑ ይችላሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች የጸጉር መመለጥ አነሳሹ ወይም አባባሹ ምክንያት እስከተወገደ ድረስ ጊዜያዊ ሊሆን ይችላል።  

 

 

እርስዎ ምን ማድረግ ይችላሉ? 

  • የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል፡ ጭንቀትን በአግባቡ ማስወገድ ፤ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ በተለይም በፕሮቲን እና አይረን የበለጽጉ ምግቦችን መመገብ፤ ለጸጉርዎ እንክብካቤ ማድረግ አሁን ያለውን ጸጉር ለመጠበቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል። 
  • የመድኃኒት እገዛ፡ የሚቀቡ መድሃኒቶች እንድ ሚኖክሲዲል እና የሚዋጡ እንደ ፊናስተራይድ ፊናስተራይድ የጸጉር መሳሳትን ለማዘግየት ጥቅም ላይ ይውላሉ። 
  • የጽጉር ንቅለ ተከላ እና በፕላትሌት የበለጸገ ፕላዝማ ህክምና ደግሞ ከፍተኛ ደረጃ ለደረሰ ራሰ በራነት ጥሩ ውጤት አስገኚ አማራጭ ነው። 

ቀደሞ ህክምና ማድረግ ለተሻለ ውጤት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤ ራሰበራነት ሁልጊዜ እንደበፊቱ ለመመለስ ባይቻል እንኳን በትክክለኛው የህክምና አማራጭ ፍጥነቱን መቀነስ እና መቆጣጠር ይቻላል። 

Comments (0)