የኩላሊት እጥበት (dialysis)

Eyasu Yebeltal
Feb 12, 2026
undefined

                   የኩላሊት እጥበት (dialysis)

በሰውነታችን ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑትን ንጥረነገሮች እና ከመጠን በላይ የሆነን ፈሳሽ በኩላሊት  አማካኝነት ከሰውነታችን በሽንት መልክ እንዲወገድ ይደረጋል። ነገር ግን በተለያየ ምክንያት ኩላሊት ላይ ህመም ሲኖር እና ኩላሊት ከ80 እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የማጣራት አቅም ሲያጣ የኩላሊት እጥበት የሚባለው የህክምና ሂደት ይከናወናል።

የኩላሊት እጥበት ከመሰራቱ በፊት መደረግ ያለባቸው ነገሮች አሉ ለምሳሌ

·         ክብደት መለካት

·         ደም ግፊት መለካት

·         የፖታሺየም፣ካልሺየም እና ፎስፈረስ መጠንን ጨምሮ  የተለያዩ የደም ምርመራዎችን ማድረግ

በህክምናው ሁለት አይነት የኩላሊት እጥበት መንገዶች አሉ። እነዚህም ሄሞዳያሊሲስ(Hemodialysis) እና ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ(Peritoneal dialysis) የምንላቸው ናቸው።

ሄሞዳያሊሲስ(Hemodialysis) የምንለው የሚጣራውን ደም ከሰውነት አውጥቶ ማሽን ውስጥ አጣርቶ መልሶ ወደ ሰውነት የሚልክ ሂደት ነው። ይህም በአነስተኛ ቀዶ ጥገና የደምስር ውስጥ ቱቦ በማስቀመጥ ይከናወናል።

ከ ሄሞዳያሊሲስ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ የተለያዩ ችግሮች አሉ ለምሳሌ

·         የደም ግፊት መቀነስ

·         ደም ማነስ

·         የጡንቻ ህመም

·         እንቅልፍ ለመተኛት መቸገር

·         ማሳከክ

·         በደም ውስጥ የፖታሲየም መጠን መጨመር ና

·         ኢንፌክሽን ይጠቀሳሉ

በአንፃሩ ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ የምንለው ደግሞ እንደ ሄሞዳያሊሲስ በውጪ ሳይሆን የሆድ ክፍል ውስጥ ቀላል በሚባል ቀዶ ጥገና ቀጭን ቱቦ በማስገባት አላስፈላጊ የሰውነታችን ቆሻሻ እንዲጣራ እና ከመጠን በላይ የሆነውን ፈሳሽ ከደም ውስጥ እንዲወጣ ያረጋል።

 ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮች የሚከተሉት ናቸው። 

·         የሆድ ውስጥ ኢንፌክሽን

·         ትኩሳት

·         የሆድ ህመም

·         ክብደት መጨመር

·         የስኳር መጠን ከፍ ማለት

ከዲያሊሲስ ጋር በተያያዙ በብዛት የሚጠየቅ ጥያቄ አለ ይህም ለምን ያህል ጊዜ ይሰጣል የሚለው ነው፡ ፡

አንዳንዴ ቀላል የሚባል የኩላሊት ህመም በሚያጋጥምበት ጊዜ እና ህክምና ከተጀመረ በኋላ ኩላሊት ማገገም ከጀመረ የኩላሊት እጥበት ለ አጭር ጊዜ (ከቀናት እስከ ሳምንታት ጊዜ ብቻ ሊሰጥ ይችላል። 

ነገር ግን የኩላሊት ህመም የከፋ ደረጃ ላይ ከደረሰ እና ማገገም ካልቻለ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ካልተደረገ በቀር የኩላሊት እጥበት ለእድሜ ልክ ይቀጥላል።

የኩላሊት እጥበት ላይ ያለ ሰው ምን አይነት አመጋገብ ይመገብ

ፎስፈረስ፣ሶዲየም እንዲሁም ፖታሲየም በብዛት የያዙ ምግቦችን ማስወገድ እነዚህም እንደ ሙዝ፣አቮካዶ፣ድንች፣አሳ፣ኦቾሎኒ፣የወተት ግብአቶች፣ቸኮሌት እና የመሳሰሉት ናቸው። እነዚህን ምግቦች ማስወገድ የሚያስፈልገው በደም ውስጥ የሚጣሩ ንጥረነገሮችን ስለሚጨምር የኩላሊት ስራ ላይ ጫና ይፈጥራል። በተጨማሪም የሚወስዱትን የፈሳሽ መጠን መቀነስ ያስፈልጋል ይህም የሰውነት እብጠትን ለመከላከል ፣ልብ ላይ ያለውን የስራ ጫና ለመቀነስ እና ሳንባ ላይ ፈሳሽ እንዳይጠራቀም ለመርዳት ነው።

ሌላው የፕሮቲን መጠናቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን እንደ ስጋ እና እንቁላል መመገብ በኩላሊት በኩል የሚወገደውን ቆሻሻ ስለሚቀንስ የኩላሊትን ስራ ለማገዝ ይረዳል።

የኩላሊት እጥበት እየተደረገላቸው ያሉ ሰዎች ላይ  የደም ማነስ፣ የአጥንት መሳሳት፣ የቆዳ ማሳከክ፣ የእግር ህመም እና የመሳሰሉት ችግሮች ስለሚኖሩ እንደ ቫይታሚን ዲ፣ ቫይታሚን ኢ፣ አይረን እና የተለያዩ ክሬሞች ይታዘዛሉ

ከዚህ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ጥያቄዎች ካሏችሁ ከመንት ላይ ግፏልን ቸር እንሰንብት። 

Comments (0)