ፔድረስ ደርማታይተስ/ናይሮቢ ፍላይ/ምንድነው?

Al Amin Worku
Jul 19, 2025
undefined

    ፔድረስ ደርማታይተስ/ናይሮቢ ፍላይ/ምንድነው?

ፔድረስ ደርመታይቲስ ህመም መንስኤዋ ነፍሳት ክረምትና ቀዝቃዛ አየርን ተከትላ በምትራባ ነፍሳት ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም ነው። በተለምዶው ናይሮቢ ፍላይ በመባል የምትታወቀው ነፍሳት ብርሐን አቅራቢያ ብዙውን ጊዜ የጣራ ኮርኒስ ላይ ትገኛለች። በሀረጋችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ይህ የቆዳ ህመም ሪፖርት ተደርጓል።

 

              እንዴት ነው የቆዳ ህመም የምታስከትለው?

ናይሮቢ ፍላይ አትናከስም አትናደፍም። በውስጧም ፔድሪን የሚባል ለቆዳ መርዛማ የሆነ ኬሚካል ይዛለች። ቆዳችን ላይ እያለች በእጃችን ጣቶች፣ በልብሳችን ወይም በማንኛውም ነገር መጨፍለቅ ሲገጥማት ከሰውነቷ ሚያመልጠው ፔድሪን የተሰኘው ኬሚካል ነው የቆዳ ህመሙን ሚያስከትለው።

 

             የህመሙ ምልክቶች?

የቆዳ መቅላት፣ የተለያዩ የቆዳ ሽፍታ አይነቶች፣ እብጠት፣ የማሳከክ ስሜት እንዲሁም ካልታከመና የግለሰቡ የበሽታ መከላከል አቅም ደካማ ከሆነ የተለያዩ የቆዳ ህመሞችን ልታስከትል ትችላለች። እነዚህ ምልክቶች ያሉት ሰው በሚያድርበት አካባቢ ይህችን ነፍሳት መኖርዋን ማረጋገጥና ማራቅ ለቆዳ ህመሙ ሐኪም ማማከር ይኖርብናል።

 

 

           እንዴት ከሌሎች መፍሳት መለየት ይቻላል?

ናይሮቢ ፍላይ በመባል ምትታወቀው ነፍሳት ቁመቷ ከ7_10 ሚሊሜትር ሲደርስ በቅደም ተከተል የተደረደሩት ቀይና ጥቁር ቀለማት በቀላሉ ከሌሎች ነፍሳት መለየት ያስችሉናል

Paederus sabaeus(Nairobi or narrow bee fly . aka. rove beetles)

ይህች ነፍሳት በተደጋጋሚ በምኖርነት አሶሳ አካባቢ ትስተዋላለች ቁጥራቸውን መናገር ባይቻልም ብዙ ሰዎችንም አጥቅታለች። ህመሙ ከ5 _10 ቀናት በሚቆይ የቆዳ ቁስል ሊወሰን ቢችልም ለበርካታ የቆዳ ህመሞች ስለሚያጋልጥ ችላ ሊባል አይገባም።

 

           መከላከያ መንገዶች

ይህንን ህምም ያለ ምንም ወጪ መከላከል እንችላለን። ቁልፍ ከላይ ያለውን ምስል በመመልከት ነፍሳቷን መለየትና የምንተኛበትን፣ የምንቀመጥበትን ቦታዎች በማራቃ ነፍሳቷንም ከስፍራው ቆዳችንን ሳትነካን ማሶገድ ያስፈልጋል። የአልጋ አጎበር መጠቀምም ጠቃሚ ይሆናል። 

1. የህመሙ መንስኤ የሆነችውን ነፍሳት መለየት መቻል።

2. ወደ ማረፊያ ቦታዎቻችን እንዳትገባ በርና መስኮት መዝጋት።

3. የአልጋ አጎበር መጠቀም።

4. ሰውነታችን ላይ ካየናት በርጋታ ቀስ ብሎ ማንሳት።

5. የቤት ውስጥ ብርሀን ነፍሳቶቹን ስለሚስብ ከመተኛታችን በፊት አላስፈላጊ የሆኑ መብራቶችን ማጥፋትና ፀረ ተባይ ስፕሬይ መጠቀም ያስፈልጋል።

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ ሰዎችንም ያስገንዝቡ።

Comments (1)

Abraham Tesfaye
Jul 24, 2025

🙏 Thanks Dr

Al Amin undefined
Jul 25, 2025

👌👌👌