በኬታሚን የታገዘ ሳይኮቴራፒን መረዳት
በኬታሚን የታገዘ የሳይኮቴራፒ ህክምና የስነ-አእምሮ ህክምና ክፍለ ጊዜዎችን ኬታሚን ከተሰኘ መድሃኒት ጋር አጣምሮ ብቅ ያለ አዲስ የአእምሮ ጤና ህክምና ነው። እንደ ድብርት፣ ጭንቀት እና ድህረ-አሰቃቂ አደጋ ጭንቀት(PTSD) ያሉ የአእምሮ ጤና እክሎች ጋር የሚታገሉ ሰዎችን ለመርዳት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል።
ኬታሚን ምንድን ነው?
ኬታሚን በዋነኝነት የማደንዘዣ መድሃኒት ሆኖ ለብዙ አሥርተ ዓመታት በሕክምና ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ መድኃኒት ሲሆን በዝቅተኛ መጠን እና በጥንቃቄ ክትትል እየተደረገ ሲሰጥ በቴራፒ ሕክምና ጊዜ ስሜትን ለማሻሻል፣ የድብርት ምልክቶችን ለመቀነስ እና ለህክምናው የሚኖረውን ተቀባይነት ለመጨመር ይረዳል። ለማከም ብዙ ሳምንታት ከሚወስዱ የፀረ-ጭንቀት ህክምናዎች በተቃራኒ ኬታሚን ለአንዳንድ ሕመምተኞች በሰዓታት ወይም በቀናት ውስጥ የሚታይ ውጤትን ሊያመጣ ይችላል።
በኬታሚን የታገዘ የሳይኮቴራፒ ህክምና እንዴት ይደረጋል?
በኬታሚን የታገዘ ሳየይኮቴራፒ ህክምና ላይ ኬታሚን የተሰኘው መድሃኒት በሰለጠኑ ባለሙያዎች በጥንቃቄ ይሰጣል። መድሀኒቱ በሚሰጥበት ወቅት ወይም ከተሰጠ በኋላ የአይምሮ ህክምና ባለሙያው በታካሚው የሚነሱ ሀሳቦችን፣ ስሜቶችን እና የበፊት ታሪኮችን እንዲያብሰለስል እና እንዲረዳ ታካሚውን ይመራል።
የሕክምናው ሂደት ብዙውን ጊዜ ሦስት ዋና ዋና ደረጃዎችን ያካትታል።
- ዝግጅት- የአይምሮ ህክምና ባለሙያዎ በህክምናው ግቦች፣ ተጠባቂ ነገሮች እና ደህንነት ዙሪያ ከእርስዎ ጋር ይወያያል።
- ኬታሚንን መውሰድ- ታካሚው በተረጋጋ፣ ጥንቃቄ በተሞላ ባለሙያ በታገዘ ሁኔታ ውስጥ ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት ኬታሚንን ይወስዳል።
- የውህደት ቴራፒ- ታካሚዎች በሕክምናው ወቅት ያገኙትን ግንዛቤ በአግባቡ እንዲረዱ እና እንዲተገበሩ ክትትል የሚደረግበት ሕክምና ነው።
በኬታሚን የታገዘ የሳየይኮቴራፒ ህክምና ውጤቶች ከሰው ወደ ሰው ሊለያዩ ይችላሉ። አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ትርጉም ያለው የአይምሮ ጤና መሻሻልን ሲያገኙ ቀጣይነት ያለው ሕክምና እና ድጋፍ የማገገም አስፈላጊ ክፍሎች ሆነው ይቆያሉ። በሕክምናው ወቅት ሊያጋትሙ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ጊዜያዊ ማዞር፣ ማቅለሽለሽ ወይም የአመለካከት ለውጥን ሊያጠቃልሉ ሲችሉ፣ እነዚህ ተፅዕኖዎች አብዛኛውን ጊዜ ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ እና በክሊኒኮች ውስጥ ቅርብ ክትትል የሚደረግባቸው ናቸው።
በዚህ ህክምና ዙሪያ ያለው ምርምር ማደጉን እየቀጠለ ሲሆን በኬታሚን የታገዘ የሳየይኮቴራፒ ህክምና ከአስቸጋሪ የአእምሮ ጤና ሁኔታዎች እፎይታ እና ጥልቅ የፈውስ መንገድን ለሚፈልጉ ሰዎች አዲስ ተስፋ እየሰጠ ይገኛል።
በኬታሚን የታገዘ የስነ-ልቦና ሕክምና በተገቢው የሕክምና ሁኔታ ውስጥ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ብቻ መሰጠት ስላለበት ይህን ለማድረግ እያሰቡ ከሆነ፣ ለእርስዎ የአይምሮ ጤና ሁኔታ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን ፈቃድ ካለው የጤና እንክብካቤ አቅራቢ ጋር ይነጋገሩ።




