የኮምፕሬሽን (ደጋፊ) ካልሲዎች (Compression Stockings)
የኮምፕሬሽን ስቶኪንጎች (ደጋፊ ካልሲዎች) በመባል የሚታወቁት እነዚህ ልዩ ካልሲዎች ከመደበኛው የተለመዱ ካልሲዎች በላይ አጥብቀው የሚይዙ ካልሲዎች ሲሆኑ እግሮችዎን በቀስታ ጠበቅ አድርገው እና ደግፈው ይይዙታል። እነዚህን ካልሲዎች ማድረግ የደም ፍሰትዎን ለማሻሻል ይረዳል እና በእግርዎ ላይ የሚከሰት ህመም እና እብጠትን ይቀንሳል። እንዲሁም ዲቪቲ (DVT)፣ የደም መርጋት አይነት እና ሌሎች የደም ዝውውር ችግሮች የመያዝ እድሎትን በእጅጉ ይቀንሳሉ።
እነዚህ ካልሲዎች በተለያየ ርዝመት እና ጥብቅት ይገኛሉ። ከዛ በተጨማሪ የእገር ጣትን የማይሸፍኑ የእግር እጀታዎች የሚሸፍኑ ካልሲዎችን እንደ አማራጭ ማግኘት ይችላሉ። በብዙ ፋርማሲዎች እና የመድኃኒት መደብሮች በቀላሉ መግዛት ይችላሉ።
የኮምፕሬሽን ካልሲዎችን መጠቀም ያለበት ማን ነው?
የኮምፕሬሽን ስቶኪንጎች ለአብዛኛዎች ሰዎች ለመልበስ ተስማሚ እና ተመራጭ ናቸው።
የሚከተሉት ነገሮች ካሉቦት እነዚህን ካልሲዎች መልበስ በእጅጉ ሊጠቅም ይችላሉ።
- እንደ ዲቪቲ( DVT) ፣ ቫሪኮስ ቬን (varicose veins ) ወይም የስኳር በሽታ ያሉ የደም ዝውውር ጋር የተገናኙ ችግሮች ካሉ እነዚህን ካልሲዎች መልበስ ተመራጭ ናቸው።
- ከቀዶ ጥገና በኋላ በማገገም ላይ ያሉ ሰዎች ።
- ሊምፍዴማ (ብዙውን ጊዜ በሊንፋቲክ ሲስተምዎ የሚወጣ ፈሳሽ ክምችት) ካለብዎት
- የአልጋ ቁራኛ ከሆኑ ወይም እግሮችዎን ለማንቀሳቀስ የሚቸገሩ ከሆነ።
- ቀኑን ሙሉ በስራ ቦታ የሚቀመጡ ወይም የሚቆሙ ከሆነ
- ስፖርት የሚጫወቱ ከሆነ
- ነፍሰ ጡር ከሆኑ
- ረጅም የአየር ወይንም የየብስ ጉዞ ላይ ጊዜ ሲያሳልፉ
የኮምፕሬሽን ካልሲዎች እንዴት ይሰራሉ?
አዲስ የኮምፕረሺን ስቶኪንጎች በቁርጭምጭሚትዎ አካባቢ በጣም ጥብቅ ናቸው፣ እና ካልሲዎቹ ወደ እግርዎ ሲደርሱ ግፊቱ ይቀንሳል። ተመራማሪዎች ይህ ደምዎ ምን ያህል እና በምን ያህል ፍጥነት ከእግርዎ እንደሚፈስ እና ወደ ልብዎ እንደሚመለስ እንደሚያግዝ ያስባሉ።
በኦክሲጅን የበለጸገ ደም ወደ ጡንቻዎ የሚወስዱት የደም ቧንቧዎች ዘና ስለሚሉ ደምዎ በነፃነት ይፈስሳል። ደም መላሽ ቧንቧዎች ደም ወደ ልብዎ እንዲመለሱ ስለሚያደርግ ደም ከመዋሃድ እና ከመርጋት ይከላከላል። በደም ሥርዎ ውስጥ የረጋ ደም ከተፈጠረ፣ ደምዎ ከኋላው ይመለሳል፣ እና በእግርዎ ላይ ህመም እና እብጠት ያስከትላል። ይባስ ብሎ ደግሞ የረጋ ደም ከደም ስር ውጪ ከለቀቀ በልብዎ ውስጥ ሊዘዋወር እና ወደ ሳንባዎ ውስጥ ሊያርፍ ይችላል, ይህም አደገኛውን የ pulmonary embolism (PE) ያስከትላል።
ነገር ግን የኮምፕረሽን ስቶኪንጎች የደም መርጋትን ለመከላከል እና እብጠትን ለመቀነስ ብቻ አይደሉም። አንዳንድ አትሌቶች፣ የአጭር ሜትር ሯጮች፣ የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ጨምሮ እነዚህን ካልሲዎች ያዘወትራሉ። ከከባድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ ለማገገም እንዲረዳቸው ይለብሷቸዋል እና ጡንቻዎቻቸው ከባድ ህመም እንዳይከሰት ያደርጋል።
ተመራማሪዎች ወደ 1,000 በሚጠጉ ጥናቶች ላይ ባደረጉት ትንተና አንዳንድ አትሌቶች ከጉልበት በታች የኮምፕረሽን ስቶኪንጎችን ለብሰው የተሻለ አፈጻጸም ማሳየታቸውን አሳይተዋል። ነገር ግን ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል።
የኮምፕሬሽን (ደጋፊ) ካልሲዎች ጥቅሞች
የኮምፕሬሽን ካልሲዎች ሰውነትዎን በትክክል ሲሸፍኑ እና በአግባቡ ሲለበሱ በብዙ መንገድ ሊረዱዎት ይችላሉ። ዋና ጥቅማቸው የደም ዝውውርን ማሻሻል ሲሆን ይህም በኦክሲጅን የበለፀገ ደም በሰውነትዎ ውስጥ እንዲዘዋወር ያደርጋል።
የኮምፕሬሽን (ደጋፊ) ካልሲዎች የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ
- በእግርዎ ላይ ህመምን እና ህመምን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያግዛሉ
- በታፋ ፣ በእግሮችዎ እና በቁርጭምጭሚቶችዎ ላይ አላስፈላጊ እብጠትን ይቀሳሉ
- የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደረግበት ጊዜ የጡንቻን ጫና ይቀንሳሉ፣ ይህም በፍጥነት እንዲያገግሙ ይረዳዎታል
- በአጋጣሚ ለረጅም ጊዜ ሲቀመጡ ወይም ሲቆሙ ከደም መርጋት ይከላከልሎዎታል
- የ varicose veins ህመምን ለመከላከል ወይም ለማከም ደም መላሽ ቧንቧዎችን ይደግፉሉ
የኮምፕሬሽን (ደጋፊ) ካልሲዎች የማድረግ የጎንዮሽ ጉዳቶች
የኮምፕሬሽን ካልሲዎች የተለመዱ ባይሆንም አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፣ በተለይ በትክክል ካልተለበሱ ወይም የተሳሳተ መጠን ከለበሱ።
በጣም የተለመዱ የጎንዮሽ ጉዳቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ;-
- ማሳከክ
- የእግር ቅዝቃዜ
- የቆዳ መቆጣት/ መቅላት
- ህመም ወይም ምቾት ማጣት
- የባክቴሪያ ወይም የፈንገስ ኢንፌክሽን
- የቆዳ እና የለስላሳ ጡንቻዎች ጉዳት
የጎንዮሽ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ የሚከሰቱት የምንጠቀማቸውን የኮምፕሬሽን ካልሲዎች ትክክለኛ መጠን ባለማወቅ ወይም በተሳሳተ መንገድ ሲለብሱ ነው። በእግር ወይም እግር ታፋ የላይኛው ክፍል በጣም ጥብቅ ከሆነ የደምዎን ፍሰት ያግዳል ወይም ይቀንሳል። ከእሱ ጋር ተያይዞም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ይታያሉ ማለት ነው።
አስተውሉ !
ከባድ የደም ቧንቧ በሽታ ካለብዎ የኮምፕሬሽን ካልሲዎችን መልበስ የለብዎትም ምክንያቱም በእግሮችዎ ውስጥ ያሉ የደም ሥሮች ጠባብ ስለሚያደርጉ እናም የደም ፍሰትዎን ስለሚቀንሱት።




