ዋና መዋኘት ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል?
ዋና መዋኘት ከፍተኛ መጠን ያለው ካሎሪ በማቃጠል፣ መገጣጠሚያዎችን ሳይጎዱ መላውን የሰውነት ክፍል በማንቀሳቀስ እና ጡንቻዎችን በመገንባት ክብደትን ለመቀነስ እጅግ በጣም ከፍተኛ አጋዥ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው።
መዋኘት ክብደት ለመቀነስ ሆነ ለመዝናናት አስደሳች የሆነ እንቅስቃሴ ሲሆን መንፈስን የሚያድስ እና በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት። በሞቃታማ ሁኔታዎች ውስጥ እንቅስቃሴ ለመስራት የምንቸገርል፣የመገጣጠሚያ፤ ጀርባ፣ጉልበታት ወይም ቁርጭምጭሚት ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወይንም ህመም ላላቸው ሰዎች መዋኘት የአካል ብቃት ደረጃን ለመጨመር እና ለማማሻሻል ጥሩ መንገድ ነው።
ዋና መዋኘት ክብደትን ለመቀነስ የሚረዳዎት እንዴት ነው?
የውሃ ዋና መዋኘት ክብደትን ለመቀነስ ካሎሪዎችን እንዴት ያቃጥላል?
- ከፍተኛ የካሎሪ ማቃጠል (Calorie Burn): በመዋኘት ሂደት ውስጥ ሰውነት ከፍተኛ ጉልበት ስለሚፈልግ በሰዓት ከ 400 እስከ 700 ካሎሪዎችን ማቃጠል ይቻላል (ይህም እንደዋናው ዓይነትና እንደ ሰውየው ክብደት ይወሰናል)። ስለዚህ እነዚህን ፈጣን እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የምናደርገው ዋና ከፍተኛ ጉልበት ስለሚያስፈልግ በዛን ጊዜ የሰውነታችን ካሎሪዎችን በማቃጠል ለክብደት መቀነስ ምክንያት ሊሆን ይችላል።
- መላውን ሰውነት ማንቀሳቀስ (Full Body Workout): ውሃ ዋና እጅን፣ እግርን፣ ደረትን፣ እና የሆድ ጡንቻዎችን በአንድ ጊዜ ስለሚያሠራ የሰውነትን ቅርጽ ለማሳመርና ጡንቻን ለማጠንከር ይረዳል። መዋኘት በጠቅላላ የሰውነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተብሎ የሚመደብ በመሆኑ የላይኛው አካልዎ እና የታችኛው አካልዎ ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ እና ዋና ከሚሰጠው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር እንዲዋሃዱ ሲያደርግ ፣ የልብ ምትዎን ከፍ ለማድረግ እና ካሎሪዎችን እንዲያቃጥሉ ያስችልዎታል።
- ለመገጣጠሚያዎች (Joints) ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፡ የውሃው ግፊት የሰውነትን ክብደት ስለሚሸከመው እንደ መሮጥ ያሉ ስፖርቶች በጉልበትና አጥንት ላይ የሚያደርሱትን ጫና ይቀንሳል። ይህም ከመጠን በላይ ውፍረት ላላቸው ሰዎች ተስማሚ ያደርገዋል። እንደ መራመድ ወይም መሮጥ ካሉ ልምምዶች ይልቅ ዋናን ጥሩ አማራጭ የሚያደርገው ዋና በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚያደርሰው ተፅዕኖው ዝቅተኛ በመሆኑ ነው። ዝቅተኛ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የሰውነት ክብደቶት ከፍተኛ ከሆነ ፣ እድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ወይም በአንዳንድ የሰውነትዎ ክፍሎች ላይ እንደ መገጣጠሚያዎ ወይም የጀርባ ህመሞች ካሉ ጠቃሚ ናቸው።
- ሜታቦሊዝምን ያፋጥናል፡ እንደ ዋና ያሉ አዘውትረው የሚሰሩ ኤሮቢክ ስፖርቶች የሰውነትን የኃይል ማቀነባበር (Metabolism) አቅም በመጨመር በቀን ውስጥም እንኳ ሰውነት ብዙ ካሎሪዎችን እንዲያቃጥል ይረዳሉ። ከፍ ያለ ሜታቦሊዝም ማለት የኃይል መጠን ይጨምራል እናም በእረፍት እና በእንቅስቃሴ ጊዜ ብዙ ካሎሪዎችን ያቃጥላሉ ማለት ነው።
በመዋኘት ምን ያህል ክብደት መቀነስ ይቻላል?
የሚቃጠሉት ካሎሪዎች እና የሚቀነሱት የሰውነት ክብደት መጠን በተለያዩ ምክንያቶች ይወሰናል፡-
- የአሁኑ ክብደትዎ
- የእርስዎ የሰውነት ሜታቦሊዝም መጠን
- የሚመገቡት የካሎሪዎች መጠን
- የሰውነቶ የአካል ብቃት ወይንም ጥንካሬ
ለክብደት መቀነስ የሚደረግ ዋና ውጤታማ እንዲሆን ዋና ነጥቦች፡
ተከታታይነት፡ በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ ያህል መጠነኛ ወይም ከፍተኛ የዋና እንቅስቃሴ ማድረግ ይመረጣል።
የአመጋገብ ስርዓት፡ ከስፖርት ጎን ለጎን ጤናማ እና በንጥረ-ምግብ የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ለፈጣንና አስተማማኝ ለውጥ ወሳኝ ነው።
የዋና አይነቶች፡ እንደ ፍላጎትዎ እና አቅምዎ የቢራቢሮ፣ የጀርባ፣ የደረት ወይም የፍሪስታይል ዋና ዓይነቶችን በመቀያየር የሰውነትን እንቅስቃሴ ማጠናከር ይቻላል።
ክብደትን ለመቀነስ የውሃ ዋና እንቅስቃሴዎች እየሰሩ ከሆነ ጥሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ያስፈልግዎታል። ምንም እንኳን ጥሩ የሰውነት ብቃት ቢኖርዎትም ፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ክብደትን ለመቀነስ የሚያደርጉት ጉዞ እንዲሳካ ሊያደርግ እንደሚችል ልብ ሊባል ይገባል ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ክብደትን ለመቀነስ ወሳኝ ቢሆንም ጤናማ እና ከመጠን ያላለፈ ወይንም ካሎሪ ዴፊሲት ያለው አመጋገብም በእጅጉ ወሳኝ ነው።
ዋና መዋኘት መላ ሰውነትዎ ከውሃ ውጭ ከሚሰራው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በላይ ጠንክሮ እንዲሰራ ስለሚያስችል በመዋኛ ገንዳ ውስጥ ለ30 ደቂቃ መዋኘት ከገንዳው ውጭ ከሚደረግ የ45 ደቂቃ እንቅስቃሴ ጋር እኩል ነው።
መዋኘት ካሎሪዎችን ለማቃጠል ውጤታማ መንገድ ነው።
አንድ የ 70 ኪሎ ሰው በየ 30 ደቂቃው በመጠነኛ ፍጥነት ቢዋኝ 223 ካሎሪዎችን ያቃጥላል። ያው ግለሰብ በየ 30 ደቂቃው በከፍተኛ ፍጥነት ቢዋኝ እስከ 372 ካሎሪ ያቃጥላል።




