Fermentation ምንድን ነው?
በሳይንሱ ዓለም መቡካት Fermentation የሚባለው ሂደት እንደ ባክቴሪያ እና እርሾ (Yeast) ያሉ ጥቃቅን ህዋሳት በምግብ ውስጥ ያለውን ካርቦሃይድሬት (ስኳር እና ስታርች) ወደ አልኮል ወይም አሲድ የሚቀይሩበት ጥንታዊ የተፈጥሮ ሂደት ነው፡፡ ይህ ሂደት ምግቡ እንዳይበላሽ ረጅም ጊዜ እንዲቆይ ከማድረጉም በላይ፣ ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቪታሚኖችን እና ባክቴሪያዎችን(probiotics) ያመርታል፡፡
የሆድ ማይክሮባዮም (The Gut Microbiome) እና ጤናችን
በሰውነታችን ውስጥ በተለይም በኮለን (ከትልቁ አንጀት) ውስጥ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች በአንድ ላይ "የሆድ ማይክሮባዮም" ይባላሉ፡፡ የህክምና ሳይንስ እንደሚያረጋግጠው በሆዳችን ውስጥ ያሉ "ጥሩ ባክቴሪያዎች" መጠን ከቀነሰ እና "መጥፎ ባክቴሪያዎች" ከበዙ ለተለያዩ በሽታዎች እንጋለጣለን፡፡ fermented ምግቦች ደግሞ እነዚህን ጥሩ ባክቴሪያዎች (Probiotics) በቀጥታ ለሰውነታችን የሚለግሱ ናቸው፡፡
fermented ምግቦች 6 ዋና ዋና የህክምና ጥቅሞች
የተቦካ ምግቦችን በየቀኑ በአመጋገባችን ውስጥ ማካተት በሰውነታችን ላይ የሚያመጣቸው ሳይንሳዊ ጥቅሞች የሚከተሉት ናቸው፡
1. የምግብ መፈጨት ሥርዓትን ማሻሻል (Digestive Health)
Fermented ምግቦች በውስጣቸው ‘ፕሮባዮቲክስ’ (Probiotics) ወይም ጥሩ ባክቴሪያዎችን ይዘዋል፡፡ እነዚህ ባክቴሪያዎች፡
- የሆድ መነፋትን፣ ጋዝን እና የሆድ ድርቀትን ይቀንሳሉ፡፡
- እንደ አይቢኤስ (IBS - Irritable Bowel Syndrome) ያሉ ከባድ የአንጀት መቆጣት ችግሮችን ያስታግሳሉ፡፡
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ማጠናከር (Immune System Boost)
የሰውነታችን በሽታ የመከላከል ሥርዓት (Immunity) ወደ 70% የሚጠጋው የሚገኘው በአንጀታችን ውስጥ ነው፡፡ fermented ምግቦችን ስንመገብ የአንጀት ጤና ስለሚጠበቅ፣ ሰውነታችን የቫይረስ እና የባክቴሪያ ጥቃቶችን የመከላከል ብቃቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል፡፡
3. የምግብ ንጥረ ነገሮችን አቅምን መጨመር
አንዳንድ ምግቦች በውስጣቸው (Phytic Acid) የተባለ ንጥረ ነገር ይይዛሉ፡፡ ይህ አሲድ ሰውነታችን እንደ ብረት (Iron) እና ዚንክ (Zinc) ያሉ ማዕድናትን እንዳይከማች እንቅፋት ይሆናል፡፡ fermented ምግብ ግን ይህንን ፋይቲክ አሲድ ስለሚሰብረው፣ ሰውነታችን ከምግቡ ማግኘት ያለበትን ጥቅሞች በሙሉ በቀላሉ እንዲያገኝ ይረዳዋል፡፡
4. ለአእምሮ ጤና እና ለስሜት መረጋጋት (The Gut-Brain Axis)
በሆዳችን እና በአእምሯችን መካከል ቀጥተኛ የነርቭ ግንኙነት አለ፡፡ ‘ሴሮቶኒን’ (Serotonin) የተባለው የደስታ እና የስሜት ማረጋጊያ ሆርሞን 90% የሚመረተው በአንጀት ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህ fermented ምግቦችን መመገብ ጭንቀትን (Anxiety) እና ድብርትን (Depression) ለመቀነስ ይረዳል፡፡
5. የልብ ጤናን መጠበቅ
አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የተቦካኩ ምግቦች (በተለይ እርጎ) የደም ግፊትን ለማስተካከል እና መጥፎ የኮሌስትሮል (LDL Cholesterol) መጠንን ለመቀነስ እገዛ ያደርጋሉ፡፡
6. የላክቶስ አለመስማማትን (Lactose Intolerance) መቀነስ
የወተት ተዋጽኦዎች ferment በሚሆኑበት ጊዜ (ለምሳሌ ወደ እርጎ ሲቀየሩ) በውስጣቸው ያለው ‘ላክቶስ’ የተባለው ወተት ስኳር በባክቴሪያዎቹ አማካኝነት ይሰበራል፡፡ በዚህም ምክንያት ወተት መጠጣት የማይችሉ (የሆድ ቁርጠት የሚይዛቸው) ሰዎች እርጎን በቀላሉ መፍጨት ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባህላዊ አማራጮች እና የአጠቃቀም ጥንቃቄ
Fermented ምግቦችን ለማግኘት የግድ ውድ የሆኑ የውጭ አገር ምግቦችን መግዛት አያስፈልግም፡፡ በሀገራችን ባህል ውስጥ እጅግ ምርጥ የሆኑ አማራጮች አሉን፡፡
የሀገር ውስጥ fermented ምግቦች እና መጠጦች
- እንጀራ፦ የጤፍ ሊጥ ለቀናት ሲቦካ (ሲኮመጥጥ) በውስጡ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮባዮቲክስ እና ቢ-ቪታሚኖችን ያመርታል፡፡
- እርጎ እና አይብ፦ ከተፈጥሯዊ ወተት የሚዘጋጁ የሀገር ውስጥ እርጎዎች የአንጀት ጤናን ለመጠበቅ ወደር የላቸውም፡፡
- ቆጮ፦ ከእንሰት ተቆፍሮ ለረጅም ጊዜ ተከድኖ የሚቦካው ቆጮ ለሆድ ጤና እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
- ጠጅ፣ ጠላ እና ከቲራ፦ በባህላዊ መንገድ የሚጠመቁ መጠጦች በመጠኑ (ያለ አልኮል ወይም በአነስተኛ አልኮል) ሲዘጋጁ የመቦካት ጥቅም አላቸው፡፡
fermented ምግቦችን በአመጋገብ ውስጥ ለማካተት ደረጃዎች
1.በአነስተኛ መጠን መጀመር:
fermented ምግቦችን በአንዴ በብዛት መመገብ መጀመሪያ ላይ የሆድ መነፋት ወይም የጋዝ ስሜት ሊፈጥር ስለሚችል፣ በቀን በአንድ ወይም በሁለት ማንኪያ እርጎ መጀመር ይመረጣል፡፡
2.ያልተቀቀሉ/ያልተጠበሱ አማራጮችን መምረጥ:
ከፍተኛ ሙቀት (ማብሰል) ጠቃሚ የሆኑትን ህያው ባክቴሪያዎች ስለሚገድላቸው፣ እንደ እርጎ ያሉ ምግቦችን ሳያሞቁ መመገብ ጥቅሙን ሙሉ ያደርገዋል፡፡
3.ስኳር ያልበዛባቸውን መምረጥ
በሱቅ የሚሸጡ እርጎዎች ውስጥ ከፍተኛ ስኳር ሊኖር ስለሚችል፣ በቤት ውስጥ የተዘጋጀ ወይም "Plain/Natural Yogurt" የሚለውን መምረጥ ይመረጣል፡፡
በአጠቃላይ ferment ምግቦችን የዕለት ተዕለት አመጋገብዎ አካል ማድረግ የሆድዎን ጤና ከመጠበቅ ባለፈ ሙሉ ሰውነትዎ በሃይል እና በጤና እንዲሞላ ያደርጋል፡፡


