የስኳር ሕመምተኛ ሆነው የደም ስኳርዎን ለመቆጣጠር የሚሞክሩ ይሁኑ ወይም በቀንዎ ውስጥ የስኳር መጠን መጨመርን ለመከላከል እና የህይወት ጥራትዎን ለማሻሻል ፈልገው ይሁን ፤ እነዚህ 5 ምግቦች የደም ስኳር መጠንዎን በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር ፣ ከምግብ በኋላ የሚከሰተውን የስኳር መጠን መጨመር (Sugar spike) ለመከላከል እና ውጤታማ ቀን እንዲኖርዎት ይረዱዎታል። የደም ስኳርን በጥሩ ሁኔታ መቆጣጠር የዓይን፣ የኩላሊት፣ የነርቭና የልብ ጉዳትን ይቀንሳል፤ እንዲሁም ቁስል በፍጥነት እንዲድንና የሕይወት ጥራት እንዲሻሻል ይረዳል።
1 ብሮኮሊ(Broccoli)
ብሮኮሊ ሰልፎራፌን (Sulforaphane) በተባለ ንጥረ ነገር የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ሰውነትዎ ለኢንሱሊን (Insulin) ያለውን ምላሽ በማሻሻል እና የኦክሲዳንት ውጥረትን (Oxidative stress) በመቀነስ የስኳር መጠንዎን ለመቆጣጠር ይጠቅማል።
2 ቀረፋ (Cinnamon)
ሰውነታችን ለኢንሱሊን ተቀባይነቱን የሚያሻሽሉ እና ከምግብ በፊት የደም ስኳር መጠንን የሚቀንሱ ውህዶችን በመያዙ በሻይ ፣ አጃ ፣ እና ሌሎች ምግቦች ውስጥ በማካተት ቀረፋን ይጠቀሙ።
3 አቮካዶ (Avocado)
በጤናማ ስብ እና ፋይበር የበለፀገ ነው ። አቮካዶ ከምግብ በኋላ የሚከሰተውን የስኳር መጠን መጨመር ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስኳር ቁጥጥርን (glycemic control) ለማሻሻል ይረዳል።
4 አጃ (Oatmeal)
አጃ ፋይበር በተለይም ቤታ-ግሉካን (beta-glucan) የያዘ ሲሆን፣ ይህም ሰውነታችን ስኳር ወደ ደም ስር የሚያስገባበትን ሂደን ቀስ በማድረግ ከፍተኛ የስኳር መጨምረን ይቀንሳል። ስለዚህም ቀኑን ሙሉ የደም የስኳር መጠን የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል።
5 ተልባ (Flaxseeds)
በፋይበር እና በጤናማ ስብ የበለጸገ በመሆኑ፣ ተልባ የሄሞግሎቢን ኤ ዋን ሲ (HbA1c) መጠንን ያሻሽላል እና ከምግብ በኋላ የሚከሰተውን የደም ስኳር መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል።
ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት 5 ምግቦች በተጨማሪ፣ የደም ስኳርን ለመቆጣጠር የሚረዱ እንደ ስፒናች እና ሌሎች ቅጠላማ አትክልቶች፣ ቤሪዎች፣ የዱባ ፍሬዎች እና እንቁላል ያሉ ምግቦችን መጥቀስ ተገቢ ነው።


