በቤት ውስጥ ሊኖር የሚገባ የመጀመሪያ ዕርዳታ ሳጥን (First Aid Kit)

Betelhem Kenea
Jul 7, 2026
undefined

የመጀመሪያ ዕርዳታ ሳጥን በማንኛውም ቤት ውስጥ ሊኖር የሚገባ መሠረታዊ መሣሪያ ነው።  ልጅዎ ሲጫወት ወድቆ ጉልበቱን ተጎድቶ ሆነ በሌሊት ላይ ትኩሳት ቢኖረው ፣ ወይም እርስዎ ራስ ምታት ወይም የሚያቃጥል ምግብ ተመግበው ጨጓራዎትን ቢያቃጥሎት ፤ የመጀመሪያ የእርዳታ ሳጥን በቤትዎ ውስጥ መያዝ ፈጣን እፎይታ እንዲያገኙ እንዲሁም ለቀላል ምልክቶች ወደ ፋርማሲ መሄድዎትን ያስቀርልዎታል። 

 

ለቁስል እና ለቃጠሎ እንክብካቤ 

ለሚፈጠሩ ትናንሽ ቁስሎች የመጀመሪያ እርዳታ ሳጥን ውስጥ እነዚህን መያዝ አስፈላጊ ነው። 

  • የቁስል ፕላስተር (Band-aid)
  • የሚለጠጥ ፋሻ (Elastic bandage)
  • ንጹህ ጎውዝ እና የጎውዝ ጥቅሎች (Sterile Gauze & Gauze roll)
  • የሕክምና ፕላስተር (Medical tape)
  • እንደ ፖቪዲን አዮዲን (Povidone Iodine) ወይም ክሎርሄክሲዲን (Chlorhexidine) ያሉ የቁስል ማጽጃ ፈሳሾች 
  • ቁስልን ለማጠቢያ የሚያገለግል ሳላይን (Normal saline) ወይም ንጹህ ውሃ 
  • ንጹህ ፎጣ ወይም ጨርቅ 

መሠረታዊ መድሃኒቶች 

  • ለቀላል ራስ ምታት እና ለትኩሳት የሚሰጥ ፓራሲታሞል (Paracetamol)
  • ለሌሎች ህመሞች ማስታገሻ አይቡፕሮፌን (Ibuprofen)
  • ለቀላል አለጂ የሚሰጡ አንታይ ሒስታሚን (Antihistamine)
  • ለተቅማጥ እና ድርቀት የሚበጠበጥ ጨው (ORS)
  • ለጨጓራ ህመም የሚሰጥ አንቲ አሲድ (Antacid) 

ከላይ የተገለጹትን መድሃኒቶች ለጊዜያዊ ህመም ማስታገሻ ቢያገለግሉም ምልክቶቹ የማይጠፉ ወይም የሚብሱ ከሆነ ወደ ሐኪም ቤት በመሄድ የሕክምና እርዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው። 

የንጽህና እቃዎች 

  • የፀረ ባክቴሪያ መጥረጊያዎች (Antiseptic Wipes)
  • ሳሙና 
  • የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር (Hand Sanitizer)
  • የፊት መሸፈኛ (Face mask) 

ተጨማሪ የደህንነት መጠበቂያዎች እና ተጨማሪ መሳሪያዎች 

  • ሙቀት መለኪያ (Thermometer)
  • ላቴክስ ያልሆኑ ጓንቶች (Non-Latex Gloves)
  • መቀስ (Medical scissors)
  • ትዊዘር (Tweezers)
  • ደም መፍሰስ ማቆሚያ ማሰሪያ (Tourniquet) 

ማስታወሻ 

የመጀመሪያ እርዳታ መድኃኒቶችን ሲገዙ እንዲሁም ከመጠቀምዎ በፊት መድኃኒቶቹ የሚያበቁበትን ቀን (Expiry date) በየጊዜው መመልከት አይዘንጉ። የመጀመሪያ ዕርዳታ ሳጥኑንም ሕፃናት በማይደርሱበት ሥፈራ ማስቀመጥ እና የሚዋጡ መድኃኒቶችን አወሳሰድ  ያለ ሕክምና ባለሙያ ምክር በራስዎ አይውሰዱ።

 

የመጀመሪያ ዕርዳታ ሳጥን መኖሩ አስፈላጊ ቢሆንም አጠቃቀሙን ማወቅ ግን ይበልጥ አስፈላጊ ነው። የደም መፍሰስን መቆጣጠር ፣ ቁስልን በአግባቡ ማጽዳት እና መሸፈን ፣ ቃጠሎን በቀዝቃዛ ውሃ ማቀዝቀዝ እና አደገኛ ምልክቶችን ለይቶ ወደ ሐኪም ቤት መሄድ ከሁሉም የቤተሰብ አባላት የሚጠበቅ መሰረታዊ ክህሎት ነው። 

Comments (0)