የጉበት በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?

Eyob Bayeh
Jun 24, 2025
undefined

‎የጉበት በሽታን መቼ እንጠርጥር?ምልክቶች ምንድን ናቸው?!
 

‎Clues for liver diseases ?
 


 

‎የጉበት በሽታ:- መርዛማ ንጥረ-ነገሮችን ማስወገድ፣ ፕሮቲንን ማዘጋጀት እና ሃሞት ማምረትን ላሉ የተለያዩ ወሳኝ ተግባሮችን የሚወጣውን ጉበትን የሚነኩ ወይም ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የተለያዩ ሁኔታዎችን ያጠቃልላል። 
 


 

‎ጉበት በሚጎዳበት ጊዜ ሰውነታችን ህመም ላይ መሆኑን ለማሳወቅ የተለያዩ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል። 
 


 

‎እነዚህን ምልክቶች ቀደም ብሎ ማወቅ ውጤታማ የሆነ ምርመራ እና ሕክምና ለማግኘትና ለማድረግ ወሳኝ ነው። 
 


 

‎የጉበት በሽታ ምልክቶች 
 

‎የጉበት በሽታ በተለያዩ መንገዶች ሊገለጥ ይችላል። አሥር የተለመዱ የጉበት በሽታ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው:-
 

‎1.  ጃውንዲስ | Jaundice
 

‎ቢሊሩቢን በመከማቸቱ ምክንያት የቆዳ እና የዓይን ቀለም ቢጫ መሆን። 
 

‎2. ድካም 
 

‎የማያቋርጥ የድካም ወይም የመዛል ስሜት መሰማት። 
 

‎3.  የሽንት መጥቆር 
 

‎ሽንት ከወትሮው የበለጠ ጠቆር ያለ ቀለም ይኖረዋል፣ አብዛኛውን ጊዜ አምበር (ብሩህ ቢጫ) (Amber) ወይም ቡናማ የሆነ ሽንት።
 

‎4.  የገረጣ ወይም የሸክላ ቀለም ያለው ሰገራ 
 

‎በሃሞት እጥረት ምክንያት ሰገራ ከተለመደው ነጣ ያለ መልክ ወይም ቀለም እንዲኖረው ያደርጋል።
 

‎5. የሆድ ህመም እና የሆድ እብጠት 
 

‎በሆድ የላይኛው ቀኝ በኩል ህመም ወይም የምቾት ማጣት ስሜት መሰማት፣ በፈሳሽ ክምችት ወይም ፈሳሽ በመከማቸቱ ምክንያት የሚከሰት እብጠት ወይም አሳይቲስ (Ascites)።
 

‎6. ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ 
 

‎7. የምግብ ፍላጎት ማጣት 
 

‎የመብላት ፍላጎት መቀነስ፤ ይህ ሁኔታ አንዳንድ ጊዜ የሰውነት ክብደት መቀነስ ያስከትላል። 
 

‎8. የቆዳ መቅላት እና መድማት | Easy Bruising and Bleeding
 

‎የጉበት ተግባር በመዳከሙ ምክንያት ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች መበጠስ እና የቆዳ መልክ መቀየር (መቅላት) ወይም መድማት (ደም መፍሰስ)።
 

‎9. የቆዳ ማሳከክ 
 

‎ከቆዳ በታች የሃሞት ጨው (Bile Salt) በመከማቸቱ ምክንያት የሚከሰት የማያቋርጥ የቆዳ ማሳከክ።
 

‎10. የእግር እና ቁርጭምጭሚት እብጠት 
 

‎በተለይም በታችኛው የሰውነት ክፍሎች ላይ ኤድማ (Edema) ወይም የፈሳሽ መቋጠር። 
 

‎እነዚህ ምልክቶች እንዳለብዎት የጉበት በሽታ ዓይነት እና ክብደት ወይም አስከፊነት ሊለያዩ ይችላሉ። የጉበት በሽታን እንዳለብዎት ከጠረጠሩ ተገቢውን ምርመራ እና ህክምና ለማግኘት ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው። 
 

‎ጤናችን ሐብታችን! ለጤናችን ራሳችን!!
 

‎ዶ/ር ኢዮብ ባየህ (ጠቅላላ ሀኪም)
 

Comments (0)