የዊፕዎርም (whipworm) ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል?

Eyerusalem Tadese
Sep 2, 2026
image 2026 09 02 101234641

ትሪኩሪስ ትሪኪዩራ (Trichuris trichiura) 'ዊፕዎርም' (whipworm)

 በመባል የሚታወቅ ጥገኛ የሆነ ክብ ትል ነው። ይህ ትል በሰው ልጅ አንጀት (በተለይም በትልቁ አንጀት) ላይ ኢንፌክሽን በመፍጠር 'ትሪኩሪያሲስ' (trichuriasis) የተባለ በሽታ ያስከትላል፤ ይህ በሽታ ደግሞ የንጽህና አጠባበቅ ደካማ በሆነባቸው ሞቃታማና እርጥበት አዘል አካባቢዎች በብዛት ይከሰታል።

የዊፕዎርም (Whipworm) ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?

የዊፕዎርም (whipworm) ኢንፌክሽን ከቀላል እስከ ከባድ የሚደርሱ የተለያዩ ምልክቶችን ሊያስከትል ይችላል። እነዚህም የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

  • ደም የተቀላቀለበት ተቅማጥ

  • የሆድ ህመም

  • ማቅለሽለሽ

  • ማስታወክ

  • ራስ ምታት

  • ድንገተኛ እና ያልተጠበቀ የክብደት መቀነስ

  • ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል

የዊፕዎርም (Whipworm) ኢንፌክሽን መንስኤው ምንድን ነው?

አንድ ሰው ሳያውቅ የዊፕዎርም (whipworm) ጥገኛ ተህዋሲያንን ወይም እንቁላሎቻቸውን ወደ ሰውነቱ ሊያስገባ የሚችለው በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፦

  • አፈር ከነካ በኋላ እጁን ወይም ጣቶቹን ወደ አፉ ሲያስገባ ወይም ከአፉ አጠገብ ሲያደርግ

  • በደንብ ያልታጠቡ፣ ያልበሰሉ ወይም ያልተላጡ ፍራፍሬዎችን ወይም አትክልቶችን ሲመገብ ነው።

የዊፕዎርም (Whipworm) ኢንፌክሽን ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

የዊፕዎርም (whipworm) ኢንፌክሽን በማንኛውም ሰው ላይ ሊከሰት ይችላል። ሆኖም፣ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ሰዎች ለዚህ ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል፦

  • በሞቃታማና እርጥበት አዘል የአየር ንብረት ባለበት አካባቢ መኖር

  • ደካማ የንፅህና አጠባበቅ ሁኔታዎች ባሉበት አካባቢ መኖር

  • ከእንስሳት ፍግ ጋር በተቀላቀለ አፈር የመገናኘት እድል በሚፈጥር የስራ መስክ ላይ መሰማራት

  • በእንስሳት ፍግ በተዳቀለ አፈር ውስጥ የለሙ ጥሬ አትክልቶችን መመገብ

  • ህጻናት በዊፕዎርም (whipworm) የመያዝ ዕድላቸውም ከፍተኛ ነው። ብዙውን ጊዜ ከቤት ውጭ ስለሚጫወቱ፣ ምግብ ከመብላታቸው በፊት እጃቸውን በደንብ ላያጠቡ ይችላሉ።

               የዊፕዎርም (Whipworm) ኢንፌክሽን እንዴት ይታወቃል?

  • Stool Test(የሰገራ ምርመራ) 

  • የካቶ-ካትዝ (Kato-Katz) ዘዴ፡- በላቦራቶሪዎች ውስጥ ጥገኛ ተህዋሲያን የሚያስቀምጧቸውን እንቁላሎች ለመቁጠር እና የኢንፌክሽኑን ክብደት ለመለካት የሚያገለግል መጠናዊ ዘዴ።

  • ኢንዶስኮፒ ወይም ኮሎኖስኮፒ፡ አልፎ አልፎ፣ ዶክተሮች በካሜራ በሚደረግ ምርመራ ወቅት በትልቁ አንጀት (colon) ወይም በፊንጢጣ (rectum) ውስጠኛ ሽፋን ላይ ተሰግስገው የሚገኙ እንደ ክር የሚመስሉ አዋቂ ትሎችን ሊያዩ ይችላሉ።

                የዊፕዎርም (whipworm) ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል?

ለዊፕዎርም ኢንፌክሽን በጣም የተለመደውና ውጤታማው ህክምና እንደ (albendazole) እና(mebendazole) ያሉ ጥገኛ ተህዋሲያንን የሚገድሉ መድኃኒቶችን መጠቀም ነው። እነዚህ መድኃኒቶች በሰውነት ውስጥ የሚገኙትን ዊፕዎርሞች እና እንቁላሎቻቸውን ያስወግዳሉ።ምልክቶቹ አንዴ ከቀነሱ በኋላ፣ ኢንፌክሽኑ መጥፋቱን ለማረጋገጥ ሐኪምዎ ሌላ የሰገራ ምርመራ ማድረግ ሊፈልግ ይችላል።

                          በዊፕዎርም (whipworm) የመያዝ አደጋን እንዴት መከላከል ይቻላል?

  • በዊፕዎርም የመያዝ አደጋን ለመቀነስ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦

  • እጅዎን በደንብ ይታጠቡ፤ በተለይም ምግብ ከማዘጋጀትዎ ወይም ከመመገብዎ በፊት።

  • ምግቦችን ከመመገብዎ በፊት በደንብ ይጥቧቸው፣

  • ጥራት ያለው ውሃ መጠቀም ወይም አፍልቶ መጠቀም

Comments (0)