ጤና ይስጥልኝ
ድምፅ አልባው ገዳይ "ስትሮክ" (Stroke) ምንድን ነው?
ወደ አእምሯችን ክፍል በተለያየ ምክንያት የደም አቅርቦት ሲስተጓጎል ወደ አእምሮ የሚደርሰው ኦክስጅን ይቋረጣል። አንድ መኪና ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ጭንቅላታችንም ያልተቆራረጠ ኦክስጅን የያዘ የደም አቅርቦት ያስፈልገዋል። ያለ ኦክስጅን አእምሮ ውስጥ ያሉ ሴሎች ይጎዳሉ፣ ይሞታሉም። ስለዚህ በተለያየ ምክንያት የሚፈጠረው አእምሯችን በቂ ደም ሳያገኝ ሲቀር "ስትሮክ" እንለዋለን።
1. የስትሮክ ዓይነቶች እና መንስኤዎች
ስትሮክ በዋናነት በሁለት ይከፈላል፦
- 🟢 Ischemic Stroke (በደም ስር መደፈን ወይም መዘጋት የሚመጣ):
- Thrombotic: አእምሯችን ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች በረጋ ደም ወይም በAtherosclerosis ሲዘጉ።
- Embolic: ከአእምሮ ውጪ ከሌላ የሰውነታችን አካል (በተለይ ከልብ ወይም ከአንገት አካባቢ) በደም ቧንቧ አማካኝነት ወደ አእምሮ በመሄድ የደም ዝውውርን ሲያስተጓጎል የሚፈጠር።
- 🔴 Hemorrhagic Stroke (በመድማት ምክንያት የሚመጣ):
- አእምሮ ውስጥ የደም ስር በተለያየ ምክንያት ሲፈነዳ እና ደም ወደ ጭንቅላታችን ሲፈስ ነው። የሚፈሰው ደም ተጠራቅሞ አእምሮ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት, ጫናው የደረሰበት የአእምሮ ክፍል ኦክስጅን እንዳያገኝ ሲሆን የሚከሰት ነው።
2. ለስትሮክ የሚያጋልጡ ዋና ዋና ምክንያቶች
- ⚠️ እድሜ እየገፋ ሲሄድ
- ⚠️ የጤና ሁኔታዎች: ስኳር፣ የደም ግፊት፣ የኮሌስትሮል ክምችት፣ የደም መርጋት ችግር
- ⚠️ የኑሮ ዘይቤዎች: ከመጠን በላይ የሰውነት ውፍረት፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል መጠጥ፣ አደንዛዥ እጾች
- ⚠️ ልዩ ሁኔታዎች: እርግዝና፣ የወሊድ መቆጣጠሪያ በተደጋጋሚ የሚጠቀሙ ሴቶች፣ ደም ለማቅጠን የሚረዱ መድኃኒቶች፣ በፊት የነበረ ያልታከመ ስትሮክ፣ የአእምሮ እጢዎች
3. የስትሮክ ምልክቶች (ድንገተኛ ምልክቶች)
- ⚡ ድንገተኛ እና ኃይለኛ ራስ ምታት
- ⚡ ራስን መሳት፣ ትውከት፣ የማጅራት መገተር
- ⚡ ሚዛንን ለመቆጣጠር መቸገር
- ⚡ የፊት በአንድ በኩል ማዘንበል
- ⚡ የእጅ እና የእግር ሰንፈት ወይም አለመታዘዝ (በተለይ በአንድ በኩል)
- ⚡ መናገር ማጣት፣ መንተባተብ፣ ግራ መጋባት
4. የሚያስከትላቸው የጤና ችግሮች (Complications)
- 🔹 የአእምሮ እብጠት፣ የሳንባ ምች፣ የልብ ድካም
- 🔹 የሚጥል በሽታ፣ ሽባነት (Paralysis)
- 🔹 ሽንት ያለመቆጣጠር ችግር፣ ለመዋጥ መቸገር
- 🔹 የአልጋ ቁስል፣ የህመም ስሜት፣ ጭንቀት፣ የመግባባት ችግር
- 🔹 ሞትን ማስከትል
5. በምን ማረጋገጥ ይቻላል?
- ⏱️ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት ከማገገማችን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ቶሎ መታከም እጅግ ወሳኝ ነው።
- 🩺 የህክምና ምርመራዎች: የጤና ባለሙያው ጥርጣሬ ካለው አካላዊ ምርመራ አድርጎ፦
- የደም ስኳር መጠን እና ሙሉ የደም ምርመራ
- የደም መርጋት እና የልብ ምርመራ
- CT scan ወይም እንደ አስፈላጊነቱ MRI በማዘዝ ትክክለኛው የስትሮክ ዓይነት ይረጋገጣል።
6. የሕክምና መንገዶች
- ⭐ ፈጣን እርዳታ: ከምንም በላይ በፍጥነት የህክምና እርዳታ ማግኘት እጅግ ወሳኝ ነው።
- 💊 የመድኃኒት ሕክምና: እንደየስትሮክ ዓይነቱ የደም ግፊት መቀነሻ፣ የረጋ ደም መቀነሻ፣ የኮሌስትሮል መቀነሻዎች ይሰጣሉ። አልፎ አልፎ በደም መፍሰስ ምክንያት ከሆነ የተከማቸ ደምን ለማውጣት ቀዶ ጥገና ሊያስፈልግ ይችላል።
- 🧠 Rehabilitation:
- የመናገር እና የመግባባት ሕክምና (Speech therapy)
- ፊዚዮቴራፒ (Physical & Occupational therapy)
- የሐኪም ተከታታይ ክትትል ማድረግ
💪 ስለዚህ በየቀኑ ያሉ የጤና መሻሻሎችን በትዕግስት መከታተል ተገቢ ነው።
ጤናችን_ሐብታችን !
በዶ/ር ኢዮብ ባየህ (ጠቅላላ ሀኪም )




