በስልክ ስክሪን ላይ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ በዲጂታል መሣሪያዎች ምክንያት የሚመጣ የዓይን ድካም የሚያስከትል ሲሆን ፤ ለአጭርና ለረጅም ጊዜ የዓይን ችግሮችም ያጋልጣል። ሆኖም ግን ዘላቂ ዓይነ ስውርነትን ወይም በዓይን ሬቲና ላይ ቋሚ ጉዳትን አያመጣም።
ኮምፒውተር ቪዥን ሲንድረም (CVS ወይም በዲጂታል መሣሪያዎች ምክንያት የሚከሰት የዓይን መድከም) ማለት ያለ እረፍት ለበርካታ ሰዓታት የዲጂታል መሣሪያዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ ሊያጋጥሙዎት የሚችሉ ችግሮችን የሚያመለክት ነው። ኮምፒውተሮች፣ ታብሌቶች፣ የኤሌክትሮኒክስ ማንበቢያዎች (e-readers) እና ስማርት ስልኮች ሁሉም ለእነዚህ መሣሪያዎች ምሳሌዎች ናቸው።
ያለማቋረጥ ለሰዓታት ስክሪን መመልከት ከሌሎች ምልክቶች በተጨማሪ የዓይን መቆጥቆጥ፣ የእይታ ብዥታ እና ራስ ምታት ሊያስከትል ይችላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የዲጂታል መሣሪያዎችን በምሽት መጠቀም እንቅልፍዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
ኮምፒውተር ቪዥን ሲንድረም ከባድ የሕክምና ችግር አይደለም። ነገር ግን ምልክቶቹ በጣም ምቾት የሚነሱ ከመሆናቸው የተነሳ ሥራዎን ወይም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎን ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ።
የዲጂታል ዓይን ድካም ምልክቶቹ
•የዓይን መድረቅ እና መቆጣት (Dry Eyes & Irritation)
•የዓይን መድከም እና ሕመም (Eye Fatigue & Aches)
•የእይታ መደብዘዝ (Blurred Vision)
•ራስ ምታት(Headache)
•የአንገት ህመም(Neck pain)
•የብርሃን ፍርሃት(Photophobia)
•ትኩረት ማጣት(loss of concentration)
የሚወሰዱ የህመም ማስታገሻዎች እና መከላከያው
• ሰው ሠራሽ የዓይን ዕንባ (የዓይን ጠብታ) ይጠቀሙ
• ዓይንዎን ደጋግመው ያርገብግቡ
• የአካባቢዎን ብርሃን በማመጣጠን ነፀብራቅን ያስወግዱ
• ልዩ የዓይን መነጽሮችን መጠቀም
• የ20-20-20 ሕግ ትኩረትዎን በቅርብ ርቀት ላይ ከሚገኙ ስክሪኖች በማንሳት በዲጂታል መሣሪያዎች ምክንያት የሚከሰት የዓይን መድከምን (ኮምፒውተር ቪዥን ሲንድረምን) ለመቀነስ ይረዳል።
ስክሪን በተመለከቱ በየ 20 ደቂቃው፣ የዓይን ጡንቻዎትን ለማሳረፍ ቢያንስ 20 ጫማ ርቆ የሚገኝን ነገር ቢያንስ ለ 20 ሰከንድ በትኩረት ይመልከቱ።
ስክሪን በተመለከቱ በየ20 ደቂቃው ቢያንስ 20 ጫማ (6 ሜትር ገደማ) ርቀት ላይ የሚገኝን ነገር ቢያንስ ለ20 ሰከንድ ያህል ይመልከቱ።

እያንዳንዱ "20" እንዴት ነው የሚሠራው
- በየ20 ደቂቃው ማረፍዎ፦ ዓይኖችዎ በአንድ ቋሚ ርቀት ላይ እያዩ እንዳይቆዩ ለረጅም ጊዜ በቅርብ ርቀት ላይ የሚደረግ ትኩረትን ያቋርጣል።
- 20 ጫማ ርቀት ላይ ማየትዎ፦ የዓይን የማተኮር ጡንቻ የሆነው ሲሊያሪ ቦዲ (በቅርብ ርቀት ላይ ለማተኮር የሌንሱን ቅርጽ የሚያስተካክል ክብ ልስልስ ጡንቻ) ዘና እንዲል ያስችላል።
- ለ20 ሰከንድ ያህል ሌላ ማየትዎ፦ የማተኮር ጡንቻዎች ውጥረታቸውን እንዲለቁ በቂ ጊዜ ይሰጣል፤ እንዲሁም የእንባ ንብርብርን (የዓይንን የፊት ክፍል የሚሸፍነውን ስስ ፈሳሽ ሽፋን) ለማደስ ዓይንን ሙሉ በሙሉ መርገብገብን ያበረታታል።




