ለመዋቢያነት አገልግሎት የሚጠቅም ቦቶክስ መርፌ(የቦቱሊነም መርዝ) (Botox injection)

Elsabet Azezew
Aug 4, 2025
undefined

                ለመዋቢያነት አገልግሎት የሚጠቅም ቦቶክስ መርፌ(የቦቱሊነም መርዝ) 

        ቦቶክስ የቆዳ መሸብሸብን ለመቀነስ የሚረዳ ጡንቻን ዘና የሚያደርግ የመዋቢያ ህክምና አይነት ነው። ይህ ህክምና ቦቱሊነም ታይፕ 1 የተባለ መርዝ የሚጠቀም ሲሆን ይህም ጡንቻዎችን ለጊዜው ሽባ በማድረግ የፊት መሸብሸብን ይቀንሳል። 

        የቦቶክስ መርፌ በአንፃሩ ቀላል የህክምና አይነት ሲሆን በአይን አካባቢ እና ግንባር ላይ የሚከሰት መሸብሸብን ለመቀነስ ውጤታማ እና ከደህንነት አንፃር የማያሰጋ የህክምና ሂደት ነው። 

        ቦቶክስ በመጀመሪያ በ1989 ዓ.ም እ.ኤ.አ. በምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር (FDA) የተፈቀደው የአይን ጡንቻ ችግሮችን ለማከም ሲሆን ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ግን ለመዋቢያ ህክምና እንዲውል ተደርጓል። 

          ቦቶክስ መርፌ የመዋቢያ ህክምና ሂደት

          ቦቶክስ መርፌ የመዋቢያ ህክምና ከቀዶ ህክምና ውጪ የሆነ በሐኪሞ ቢሮ ውስጥ የሚሰጥ ብዙም ዝግጅት የማያስፈልገው ህክምና ነው። ይህን ህክምና በሐኪሞ ከመሰጠቶ በፊት የህክምና ታሪኮን ፣ ስላለቦት ማንኛውም አለርጂዎች ወይም የጤና እክሎች ማሳወቅ ይኖርቦታል።

          ከህክምና ሂደቱ በፊት ሜካፕ ተቀብተው ከሆነ ሜካፕዎን ማስወገድ እና ፊቶን መታጠብ ይስፈልጋል። እንዲሁም ከህክምናው በኋላ የፊት መበለዝ አደጋን ለመቀነስ እንደ አስፕሪን ያሉ የደም ማቅጠኛ መድኃኒቶችን ማቆም ሊኖርቦትም ይችላል።

            በህክምናው ሂደት ወቅት ሐኪሞ ቀጭን መርፌ በመጠቀም ከ3-5 የሚደርሱ የቦቱሊነም ታይፕ 1 መርዝ የያዙ መርፌዎችን የተሸበሸበው ቆዳ ላይ ይወጋዎታል።ጠቅላላ የህክምናው ሂደት በጣም ቀላል እና ከ10 ደቂቃ ያነሰ ጊዜን የሚወስድ ነው። 

 

         በቦቶክስ መርፌ የመዋቢያ ህክምና መታከም የሚችሉ የሰውነት ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?

        ቦቶክስ መርፌ ለመዋቢያነት በሚተሉት የሰውነት ክፍሎች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል

 

  • በሁለቱ ቅንድቦች መካከል ያለ ቦታ ላይ ያለን የቆዳ መሸብሸብ እእና 
  • አይኖች ዙሪያ ያለን መሸብሸብ ለመቀነስ ይጠቅማል 

     ቦቶክስ የሚከተሉትን የተለያዩ የህክምና ችግሮች ለማከምም በምግብ እና መድኃኒት አስተዳደር ፈቃድ አግኝቷል

 

  • ከመጠን በላይ ንቁ የሽንት ፊኛ ችግር  (overactive bladder)
  • ከመጠን በላይ የብብት ማላብ ችግር
  • የእግር ጡንቻ መኮማተር (lower limb spasticity)
  • ስር የሰደደ የማይግሬን ራስ ምታት 

                   ቦቶክስ እንዴት ይሰራል

           ቦቶክስ ወደ ጡንቻ የሚሄደውን የነርቭ መልዕክት ለጊዜው በመከልከል የጡንቻ መኮማተርን ያስቆማል። ይህም በአይን አካባቢ እና በቅንድቦች መካከል የሚፈጠረውን የቆዳ መሸብሸብ ያሻሽላል። እንዲሁም ይህ የፊት ጡንቻ መኮማተር ማቆም አዲስ የቆዳ መሸብሸብ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳል። 

     የቦቶክስ መርፌ የመዋቢያ ህክምና የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉት ?

            ከቦቶክስ መርፌ ጋር ተያይዞ መርፌው የተሰጠበት  ቦታ ላይ መበለዝ እና ትንሽ ህመም ሊኖር የሚችል ሲሆን ይህም ከጥቂት ቀናት በኋላ ይጠፋል ። ከቦቶክስ ጋር ተያይዘው ከሚመጡ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ 

                                                                                  

  •  የአይን ሽፋን ማበጥ ወይም መውደቅ 
  • ድካም
  • ራስ ምታት 
  • የአንገት ህመም
  • አይን ብዝታ ወይም ድርብ እይዳ  
  • የአይን መድረቅ 
  • እንደ ሽፍታ ፣ ማሳከክ ወይም የአስም ምልክቶች ያሉ የአለርጂ ምላሾች

ከእነዚህ  የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዱ ከአጋጠሞት ወዲያውኑ ሐኪሞን ማማከር ይኖርቦታል።                                                                                           

                             

       የቦቶክስ መርፌ የመዋቢያ ህክምና በኋላ ምን ይጠበቃል 

        ከቦቶክስ ህክምና በኋላ መርፌ የተወጉበትን ቦታ ከማሻሸት ወይም ከመጫን መቆጠብ ይኖርቦታል። ምክንያቱም እነዚህ ድርጊቶች የተሰጡት ቦቶክስ ወደ ሌሎች የሰውነት ክፍሎች እንዲሰራጭ በማድረግ የህክምናው ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል። 

        የቦቶክስ መርፌውን የተወጉት በቅንድቦ መካከል ከሆነ ለ3-4 ሰአታት መጎንበስም ሆነ መተኛት የለቦትም።ይህን ማድረግ ቦቶክሱ ወደ አይኖ አጥንት ጠርዝ (ኦርቢታል ሪም) እንዲገባ በማድረግ የአይን ሽፋን መውደቅን ያስከትላል። ከዚህ ውጪ ግን የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎን ከህክምናው በኋላ ወዲያውኑ መጀመር ይችላሉ።                                    

         የህክምናውን ውጤት ከ1-2 ቀናት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ማየት የሚጀምሩ ሲሆን ሙሉ ውጤቱም አብዛኛውን ጊዜ እስከ 4 ወራት ድረስ ይቆያል።                                                                                                             

Comments (0)