ቫይታሚን ዲ ጠብታ (ማሟያ)

Biruh Tesfaye
Sep 2, 2025
undefined

ቫይታሚን ዲ ለሁሉም ሕፃናት ለእድገት እና ለጤናማ የአጥንት መጎልበት አስፈላጊ ቪታሚን ነው። በእርግዝና ወቅት ሕፃናት ቪታሚን ዲን ከእናታቸው ያገኛሉ። ከተወለዱ በኋላ በሕፃናት ውስጥ ያለው የቪታሚን ዲ ክምችት ስለሚቀንስ፣ ሕፃናት የቪታሚን ዲ መጠናቸው ዝቅተኛ የመሆን ዕድል ይኖራቸዋል። 

ልጅዎ የቫይታሚን ዲ ማሟያ ለምን ያስፈልገዋል?

ቫይታሚን ዲ ለሚከተሉት ነገሮች አስፈላጊ ነው፦

  • ለጤናማ አጥንቶች እና ጥርሶች ካልሲየም እንዲዋሃድ   
  • የአጥንት መሳሳት ስጋትን ለመቀነስ   
  • የጡንቻን ጥንካሬን ለማሻሻል
  • ለእድገት 
  • የበሽታ መከላከልን ለመጨመር

በክረምት ወራት የፀሐይ ብርሃን በቂ ላይሆን ስለሚችል፣ የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ ምግብ/ማሟያ መስጠት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል።

የቫይታሚን ዲ ማሟያ መቼ ይሰጣል?

የጡት ወተት (Breast Milk) ለሚጠቀም ልጅ

የጡት ወተት ብዙውን ጊዜ ሕፃን የሚያስፈልገውን የቫይታሚን ዲ መጠን በሙሉ አይሰጥም። የጡት ወተት ብቻ የሚጠጡ ሕፃናት ወይም የጡት ወተትና ፎርሙላ የሚመገቡ ሕፃናት በየቀኑ የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ ጥብታ መውሰድ አለባቸው። መጠኑም፦ 

  • ከ12 ወር በታች የሆኑ ሕፃናት በየቀኑ 400 IU (International Units) ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል።
  • ከ12 እስከ 24 ወር የሆኑ ሕፃናት ደግሞ በየቀኑ 600 IU ቫይታሚን ዲ ያስፈልጋቸዋል።

የሕፃን ፎርሙላ ወተት (Infant Formula) ለሚጠቀም ልጅ

ፎርሙላ ብቻ የሚመገቡ ሕፃናት የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ ምግብ ላያስፈልጋቸው ይችላል። ምክንያቱም በቫይታሚን ዲ ተሞልቶ የሚዘጋጁ የሕፃናት ፎርሙላ ወተቶች ስላሉ ነው። እነሱ ወትቶች ካልተገኙ ግን የቫይታሚን ዲ ተጨማሪ ጥብታ መውሰድ አለባቸው።

ምግብ መብላት የጀመሩ ልጆች

ጠንካራ ምግብ መብላት ለጀመሩ ሕፃናት፣ ምግባቸው ቫይታሚን ዲ ያላቸውን ምግቦች መያዙን ያረጋግጡ። ቫይታሚን ዲ ያላቸው ምግቦች ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • እንደ ሳልሞን ወይም ቱና ያሉ አንዳንድ ዓሳዎች
  • እንቁላል
  • ከ12 ወር እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕፃናት የላም ወተት እና እርጎ
  • ጥራጥሬዎች (Cereals)   
  • አንዳንድ ጭማቂዎች   

Comments (0)