Epilepsy(የሚጥል በሽታ) ምንድን ነው?

Al Amin Worku
Oct 27, 2025
undefined

Epilepsy(የሚጥል በሽታ) ምንድን ነው?  
 

Epilepsy(የሚጥል በሽታ) ማለት አዕምሮ ወስጥ የሚከሰት ከመጠን ያለፈ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ሲሆንየባህርይ ለውጥ ወይም ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የሰውነትመንዘፍዘፍ ዋና መገለጫው ነው።

 

አንድ ሕጻን የሚጥል በሽታ አለበት የምንልበት ምክንያት፡ 
2 ጊዜ የእንፍርፍሪት በሽታ (seizure) ካሳየ : እንዲሁም ያለ ምንም የጤና ጉድለት ምክንያት ማለትም እንደ ትኩሳት ወይም ሌላ ዓይነት ሕመም (የቀሰቀሰው ነገር የሌለ) የተከሰቱ ሲሆን ነው። 
በተጨማሪም ልጅዎ 1 የሚጥል በሽታ ካጋጠመው እና እንደገና እንዲከሰት በከፍተኛ አደጋ ላይ ከሆነ የሚጥል በሽታ አለበት ለማለት እንችላለን።
 

የሚጥል በሽታ (Epilepsy) የምንለው አንጎልን ከሚያጠቃ የአእምሮ በሽታዎች ፣ተላላፊ ያልሆነ በአለም ላይ ተንሰራፍተው ከሚገኙ በሽታዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው።
አእምሯችን የነርቭ ሴል ውህድ ሲሆን ከ 100 ቢሊየን በላይ የነርቭ ሴሎች አሉት። እነዚህ የነርቭ ሴሎች አንዱ ከሌላው ጋር እየተናበበ የሚሰራበት የራሱ የሆነ መንገድ (neural network) አለው።
እነዚህ የነርቭ ክፍሎች በተለያየ ምክንያት እክል ይገጥማቸዋል። ይህ ሲሆነ የነርቭ ስርአቱ ይዛባል። በዚህ ሰአት በአንጎል ውስጥ በሚገኙ ሴሎች ውስጥ ከመጠን በላይ በሆነ ኤሌክትሪካዊ ንዝረት (electrical discharge) ጊዚያዊ መረበሽ ምክንያት የአእምሮ ትግበራ በድንገት መታወክ ሲኖር ምልክት ለተወሰኑ ደቂቃዎች በሚያሳይ ጊዜ አንድ ሰው ሲዝ አደረገ ፣ (seizure) ተከሰተ እንላለን።
በነርቭ መታወክ የተነሳ ተደጋጋሚ የሆነ በሰዉነት ላይ ማንቀጥቀጥን፣ የጡንቻ መገታተርን እና ማርገፍገፍን የሚያስከትል በሽታ ነዉ።የትኛውንም የእድሜ ክልል የሚያጠቃ እክል ነው፤ በአለማችን ከ70 ሚሊዮን ሰዎች በላይ የዚህ ህመም ተጠቂ ናቸው::
 

የሚጥል በሽታ ያለባቸዉን ሰዎች መርዳት እና ድጋፍ መስጠት በኑሮአቸዉ ላይ አወንታዊ ለዉጥ ሊያመጣ ይችላል።
• የሚጥል ህመም ለብዙ ሺ ዘመናት የቆየ ቢሆንም ሰዎች ስለ ህመሙ ያላቸው የተዛባና የተሳሳተ እይታ ህመሙ አሁንም ብዙዎችን የሰቀቀን ህይወት እየደገፉ እያደረገ ነው። ያረጀና ያፈጀ አመለካከት የሚጎዳው እኛኑ ነው።
የአሜባ ህመም በዘመኑ የእርኩስ መንፈስ ዉጤት ተደርጎ ይታመን ነበር።አሁን ያ'እሳቤ በሜትሮኒዳዞል ተሽሯል።በዘመን ሒደት የኤሊ ጉዞ እያደረገ ከሚገኙት አካላዊ ህመሞች አንዱ "epilepsy " ነው 
 

የሚጥል በሽታ አይነቶች
አንደኛው ዓይነት: መላው ሰውነትን የሚያንዘፈዝፍና ራስን የሚያስት ሲሆን
ሁለተኛው ዓይነት: ደግሞ የተወሰነ የሰውነት ክፍልን የሚያንዘፈዝፍ ሆኖ ራስ መሳት ያለው ወይም የሌለው ነው።


መንስኤዎቹ በዋናነት ለ5 ክፍሎች ይመደባሉ። 
 

1. መዋቅራዊ(structural)- ለምሳሌ በየራስ ላይ የደረሰ አደጋ(head injury)፣ የደም ስር ችግር (vascular problems)፣ የአንጎል ካንሰር (Brain neoplasms)፣የጨቅላነት ሕፃናት መታፈን (HIE) ወዘተርፈ... 
2. የዘር ውርስ( genetic/hereditary) በጣም ብዙ አይነት አወቃቀር ችግሮች (Genetic alterations) ያሉ ሲሆን የሚጥል በሽታ ሲንድሮምስ (genetic syndromes) የሚባሉትን በርከት አድርገው ያጠቃልላሉ። 
3. በጭንቅላት በኢንፌክሽን (infectious) ምክንያት:-ለምሳሌ ያክል እንደ ማጅራ ገትር (meningitis)፣ የአንጎልብግነት (inflammation) ለምሳሌም ያክል እንደ encephalitis ፣ brain abscess) የመሳሰሉትን ምክንያቶች ያሉት ሲኾን እነኚህም በተለያዩ ደቂቅ ዘአካላት (microorganisms) የሚመጡ ናቸው:: 
4. ሜታቦሊክ(metabolic)- የሰውነታችን ያሉ ቅመሞች ያለመመጣጠን ሳቢያ የሚከሰቱ ሲኾን ይኸውም ለምሳሌ ያክል በደም ውስጥ የስኳር መጠን ማነስ (hypoglycemia)

5 . የማይታወቅ (Idiopathic/Unknown):-ለዚህ በሽታ እንደመንስኤነት ብዙ ነገሮችን እንዳየነው ቢኖሩትም በአመዛኙ ለሚኾነው ግን እንደምክንያትነት የሚጠቀሱለት እስካሁን ድረስ አይታወቅም::

 

የሚጥል በሽታ ቀስቃሽ ምክንያቶች
ከፍተኛ የሆነ ስሜታዊነት:ከባድ ስፓርት :ከፍተኛ ድምፅ ወይም ብርሃን:ትኩሳት:የወር አበባ:ዕንቅልፍ ማጣት:ጭንቀት እና ሌሎችሂም ይጠቀሳሉ፡፡

 

የሚጥል በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው?  
የሰውነት ማንቀጥቀጥ ወይም መንዘፍዘፍ፡ተከታታይ የእጅና የእግር መወራጨት፡የሰውነት ድርቅ ማለት፡ዓይንን ወደላይ መገልበጥ፡ራስን መሳት፡አረፋ መድፈቅ፡ሽንት ማምለጥ፡ከነቁ በኋላ ግራ መጋባት፡ምላስ መንከስ፡በተድጋጋሚ የሚመጣ እራስን መሳት ከታማሚዉ ቁጥጥር ዉጪ የሆነ የእግርና የእጅ መወራጨት እና ማንቀጥቀጥ፡በአፍ አረፋ መድፈቅ፡አንድ ቦታ ላይ አይንን ተክሎ ለ ተወሰነ ደቂቃ ፈዞ መቅረት፡አይንን ወደ ላይ መገልበጥ፡የባህሪ መቀየር እንደ ፍርሃትና ጭንቀት ያሉ ስሜታዊ ምልክቶች መታየት፡፡

 

የሚታዘዙ ምርመራዎች 
1 አዕምሮ ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መለኪያ ("EEG")
ኤሌክትሮኢንሴፋሎግራፊ (EEG)- በአንጎል ውስጥ ያለውን የኤሌክትሪካዊ ሞገድና እንቅስቃሴን ይለካል። በዚህ መሳሪያ በመታገዝ ያለብዎትን የየሚጥል በሽታ አይነት ለማወቅ ሊረዳ ይችላል::

2 የጭንቅላት "CT Scan" ወይም "MRI"
ሲቲ ስካን(CT-Scan) ወይም ኤምአርአይ(MRI)ስካን -እነዚህ ምርመራዎች ደግሞ የአንጎል ውስጥን ምስሎችን በማንሳት ምናልባትም ይኽ ችግር የሚታዩ የመዋቅራዊ(structural) ምክንያቶች ያሉት መኾኑን መኖራቸውን ለማየት ይረዳሉ።

3 የአንጎል ወይም የሰረሰር ፈሳሽ ምርመራ
በተጨማሪም ለሴሬብሮስፒናል ፈሳሾች (CSF)  የአከርካሪ አንጓን በመበሳት ተቀድቶ የሚታይ ሲኾን የማጅራት ገትር፣ የኢንሰፍላይትስና ወይም የሰባራክኖይድ ደም መፍሰስ(SAH) በሚጠረጠርባቸው ታካሚዎች ላይ ሚና አለው። 
4 የተለያዩ የደም ምርመራዎች:- በደም ናሙና ተወስዶ የሚሰሩ የምርመራ አይነቶች እንደኹኔታው ታይቶ ሊታዘዙ ይችላሉ።
 

እንዴት መርዳት እንደሚችሉ/የመጀመሪያ እርዳታ 
1. ከግለሰቡ/ቧ ጋር አብረው ይቆዩ። ለማስቆም አይሞክሩ፣ እስከሚጨርስ ይጠብቁ። ግለሰቡ/ቧ ምን እያደረገ/ች እንደሆነ አያውቅም/አታውቅም 
2. አደገኛ ዕቃዎችን ከመንገድ ያስወግዱ። 
3. ወደጎን በማድረግ አንገታቸውን እና ወገባቸውን መደገፍ ከዚያም ጉልበታቸውን ማጠፍ አለብን 
4. ምላሳቸው ወደላይ ሊታጠፍ ስለሚችል የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ ከአገጭ ቀና ከአናት ዝቅ ማድረግ/head tilt chin lift/

5. ግራ ተጋብቶ/ተጋብታ ሊሆን ስለሚችል ሙሉ ግንዛቤው/ዋ እስከሚመለስ ድረስ አብረውት/ዋት ይቆዩ። በመጨረሻም መንቀጥቀጡ ሲቆም ወደ ህክምና ተቋም ማምራት አለብን፡፡
የሚጥል ህመም መደረግ ያለባቸው 
የመጀመሪያ እርዳታዎች 
ከጭንቅላት ስር ለስላሳ ልብስ ማድረግ : ሲንፈራገጥ ራሱን እንዳይጎዳ በዙሪያው ያሉ ሊጎዱት የሚችሉ ነገሮችን (እሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ ስለታማ ነገሮችን፣ድንጋይ፣ ውሀ) ማስወገድ : እንዳይንፈራገጥ በኃይል ለመያዝ አለመሞከር (የአጥንት ወይም የጡንቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላልና) : አንገት አካባቢ ያሉ የልብስ ቁልፎችን ማላላት : መንቀጥቀጡ ጀምሮ እስኪነቃ ድረስ በጎኑ ማስተኛት( የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ ለማድረግ) : አፍ ውስጥ እንጨት ወይም ሌላ ባዕድ ነገር አለመጨመር ክብሪት አለማሽተት (የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው ወድቆ ሲንፈራገጥ የመተንፈሻ አካሉ በምራቅ አረፋና በምላስ ሊዘጋ ይችላል ፤ የክብሪት ጪስ ሲጨመርበት ይባሱን ይዘጋል ፤ ጪሱ በራሱም አንጎልን የሚጎዱ ኬሚካሎች አሉት) : ህመምተኛው ከነቃ በኋላ ማረጋጋት : መንቀጥቀጡ ከ 5 ደቂቃ በላይ ከቆየ ወይንም የታማሚዉ ከንፈሩ ወደ ሰማያዊነት ወይም መጥቆር ካለ በአስቸኳይ አምቡላንስ መጥራት ቶሎ ሆስፒታል መወሰድ ተገቢ ነው::

የሚጥል በሽታ ህክምና ምክንያቱን መለየትና ማከም : ፀረ-ኢፕለፕሲ መድሃኒቶች : ከላይ የተዘረዘሩትን ቀስቃሽ ነገሮች ማስወገድ ወይም መታከም : የአዕምሮ ቀዶ ጥገና (በሚከታተል ሃኪም የሚወሰን እና ለጥቂት ህሙማን ብቻ የሚሰጥ)
የሚጥል በሽታ በተለያዩ አማራጮች አማካኝነት ይታከማል።እነዚህም በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች ዋነኛዎቹ ሲኾኑ የሚጥል ሕመም ባለባቸው ታማሚዎች ላይ የሚደረግ ሕክምና ዋና ግብ ከምልክቶች ነፃ የሆነ ሁኔታን ያለ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳካት መቻል ነው።
ታካሚው መድኃኒቶችን ሲወስድ በአንድ ጊዜ በአንድ የመድኃኒት አይነት(ሞኖቴራፒ/monotherapy) ወይንም ደግሞ ከአንድ አይነት በላይ መድኃኒቶች (ፖሊቴራፒ/polytherapy/polypharmacy)ን እንደየኹኔታው ታይቶ ሊታዘዝለት ይችላል። 
-ሞኖቴራፒ ውጤታማ ከኾነ እና ችግሩን መቆጣጠር ከቻሉ በዚህ መንገድ እንዲታከሙ ይመከራል፤ ምክንያቱም ደግሞ አሉታዊ ተፅእኖዎችን የመቀነስ እድልን ስላለውና እና የመድኃኒት መስተጋብርን ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ስለሚያቃልል ነው።
እነዚህ መድኃኒቶች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ስለዚህ ስላለብዎት የጎንዮሽ ጉዳቶች ለሐኪምዎ ያሳውቁ። በዚህ መንገድም አንድ ላይ ኾነው ምርጡን መድኃኒት እና መጠን ለእርስዎ ማግኘት ይችላሉ። 
•በጣም ከባድ ሊሆኑ የሚችሉ 2 ያልተለመዱ 
የጎንዮሽ ጉዳቶች አሉ። አዲስ ሽፍታ (rash) ካጋጠመ ወይም ራስን የመጉዳት ስሜት(suicidal attempt)  ከተሰማዎት ወዲያውኑ ለሐኪምዎ ያሳውቁ።

እነኚህ መድኃኒቶች ሌሎች የሚወስዷቸውን መድኃኒቶች በተለያየ መንገድ ሊያውኩ ይችላሉ። በተጨማሪም ሌሎች መድኃኒቶችም ለየሚጥል ሕመምዎ ተብሎ የሚወሰዱ መድኃኒትዎን ኹሉ በደንብ እንዳይሰራ ሊያደርጉት ኹሉ ይችላሉ።ስለዚህ ማንኛውንም አዲስ ማዘዣ ወይም በሐኪም ያልታዘዙ መድኃኒቶችን ከመጠቀምዎ አስቀድሞ በደንብ ለሐኪምዎ ያሳውቁ። 
ለምሳሌም እነኚሁ መድኃኒቶች የወሊድ መከላከያ ክኒኖችን በደንብ እንዳይሰሩ ያደርጋሉና ይህም ወደ ያልተጠበቀ እርግዝና ሊያመራ ይችላል፤ በጽንሱ ላይ ደግሞ የአፈጣጠር ችግርን ጨምሮ ጠንከር ያሉ ጉዳቶችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን በሚጠጉ ሰዎች ላይ የኢፕሊፕሲ (የሚጥል በሽታ) ተጠቂዎች ናቸው።
ከእነዚህ መካከል ህክምናውን የሚያኙት ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡
•በኢፕሊፕሲ ከሚቸገሩት መካከልም 70 በመቶው በአግባቡ ምርመራ ተደርጎላቸው ሕክምናውን ቢያገኙ በዚህ የጤና እክል ምክንያት የሚያጋጥነው ማንቀጥቀጥ ሊወገድላቸው እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ ህክምናው ረዘም ያለ ጊዜን የሚወስድ ሲሆን የጭንቃላትን ኤሌክትሪክ ንዝረት በሚለኩ መሳሪያዎች(EEG) በመለካት ህመሙ ያለበትን ሁኔታ በማወቅ ለረጅም ጊዜ የሚወሰድ መዳሃኒት ይታዘዛል :: 
•ታማሚው መድሃኒቱን በአግባቡ እንዲወስድና ከህመሙ ቢያንስ ለሁለት ዓመት ነፃ በሚሆን ጊዜ መድሃኒቱን ቀስ በቀስ መጠኑ እየተቀነሰ ሊቆምለት ይቺላል::

Comments (0)