የእግር ጡንቻ እስትራፖን እንዴት ማቆም ይቻላል?
እስትራፖ ብዙውን ጊዜ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም በእረፍት ወቅት በድንገት የሚከሰት ኃይለኛ ህመም ሲሆን ከጥቂት ሰከንዶች እስከ ቀናት ሊቆይ ይችላል። ብዙውን ጊዜ ምንም ጉዳት የሌለው ቢሆንም ተደጋጋሚ የእስትራፖየ ህመም እንቅልፍን፣ የእለት ተእለት እንቅስቃሴን እና አጠቃላይ የህይወት ጥራትን ሊረብሽ ይችላል። እስትራፖ በብዝት ከሚከሰትባቸው የሰውነት ክፍሎች ውስጥ የእግር ጡንቻ ሲሆን ህመሙን ለማስቆም እና የሚከሰትበን ድግግሞሽ ለመቀነስ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው ተግባራዊ እርምጃዎች አሉ።
የእግር ጡንቻ እስትራፖ
የእግር ጡንቻ እስትራፖ ድንገተኛ የጡንቻዎች ያለፈቃድ መኮማተር ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ባት፣ ጭን ወይም እግርን ያጠቃል። ይህ ህመም በስፖርታዊ እንቅስቃሴ፣ በእረፍት ወይም በእንቅልፍ ጊዜ ሊከሰት ይችላል።
የእግር ጡንቻ እስትራፖ መንስኤዎች
መንስኤውን መረዳት የመከላከል የመጀመሪያ እርምጃ ስለሆነ የእግር ጡንቻ እስትራፖ ከሚከተሉት ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል:-
- ጡንቻን ከመጠን በላይ መጠቀም ወይም ድካም
- የሰውነት ፈሳሽ ድርቀት
- እንደ ፖታሲየም፣ ማግኒዥየም ወይም ካልሲየም ያሉ ማእደናት ደረጃዎች ዝቅ ማለት
- ደካማ የደም ዝውውር
- ለረጅም ጊዜ መቀመጥ ወይም መቆም
- እርግዝና
- አንዳንድ መድሃኒቶች
- እንደ ስኳር በሽታ፣ የነርቭ መታወክ ወይም የኩላሊት በሽታን ያሉ የሕክምና ሁኔታዎች
የእግር ጡንቻ እስትራፖን እንዴት ማቆም ይቻላል?
እስትራፖ ሲያጋጥሞት ለፈጣን እፎይታ እነዚህን እርምጃዎች ይሞክሩ።
- ጡንቻዎትን በቀስታ በመዘርጋት ያፍታቱ
- እግርዎን ቀና በማድረግ ጣቶችዎን በቀስታ ወደ ራስዎ ይጎትቱ።
- የእስትራፖውን አካባቢውን በቀስታ ማሸት
- የተኮማተረ ጡንቻን ለማዝናናት በእጆችዎ ወይም የማሳጅ መሳሪያዎችን በመጠቀም ይሹት።
- የስትራፖው አካባቢ ላይ ሙቅ ወይም ቀዝቃዛ ነገር ይያዙበት
- ሙቀት የተኮማተሩ ጡንቻዎችን ዘና ለማድረግ ሲረዳ ቅዝቃዜ የህመምን ቆይታ ጊዜ ሊቀንስ ይችላል።
- ይራመዱበት
- ቀላል የእግር ጉዞ የደም ዝውውርን በማሻሻል እስትራፖን ያቃልላል።
- በቂ ፈሳሽን ይውሰዱ
- እያላብዎት ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ ከሆነ በቂ ውሃን ይጠጡ።
- ምቹ ጫማዎችን ይልበሱ
- በተለይም ለረጅም ጊዜ የሚቆሙ ወይም በእግር የሚራመዱ ከሆነ የጡንቻን ጫና ለመቀነስ ጥሩ የቅስት ድጋፍ ያለው ጫማን ይልበሱ።
- የእንቅልፍ አተኛኘትዎን ያሻሽሉ
- በጀርባዎ በመተኛት ጣቶችዎን ወደ ላይ እንዲጠቁሙ እና እግሮችዎ ወደ ታች እንዳያዘነብሉ በንጣፎች ውስጥ በቀላሉ መደበቅ ይችላሉ።
መቼ የጤና ባለሙያን ማማከር ያስፈልጋል?
አብዛኛው እስትራፖ ከባድ አይደለም ነገር ግን፡-
- በተደጋጋሚ የሚከሰት ወይም ከባድ ከሆነ
- በቤት ውስጥ እንክብካቤ የማይሻሻል ከሆነ
- ከእብጠት፣ መቅላት ወይም የጡንቻ ድክመት ጋር የተቆራኘ ከሆነ
- እንቅልፍን ወይም የዕለት ተዕለት ሕይወትን የሚረብሽ ከሆነ
- ከመደንዘዝ ጎን ለጎን የሚከሰት ከሆነ
የጤና ባለሙያ የመድሃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶችን ወይም ሌሎች ጤና ነክ ሁኔታዎችን ሊመረምር ይችላል።
የእግር ጡንቻ እስትራፖ የተለመደ እና እቤት ውስጥ ሊታከም የሚችል ሲሆን ሰውነትዎን በማዳመጥ እና ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በመከተል መፍትሄን ማግኘት ይቻላል።




