የአጥንት መሳሳት

Eyob Bayeh
May 17, 2025
undefined

የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምንድነው? ምን ላድርግ።
.
♠የሰው ልጅ አጥንት የሚገባውን ያክል የካልሲየም ክምችት ሳይኖረው ሲቀር እና ደካማ ሲሆን የአጥንት መሳሳት(Osteoporosis) ይባላል። በዚህ ጊዜ አጥንት በቀላሉ ተሰባሪ ይሆናል።

♠ሁሉንም የሰው ዘሮች እና ሁለቱንም ጾታዎች የሚያጠቃ ሲሆን በተለዬ ተጠቂ የሆኑ አካላት አሉ፦
     -አፍሪካዊያን
     -ኤሲያዊያን
     -እና ሴቶች የበለጠ ተጠቂ ናቸው።

♠መንስዔዎቹ፦
-እርጅና
-ሴት መሆን
-ከቤተሰብ ተመሳሳይ ታሪክ መኖር
-በጣም ቀጭን መሆን
-የሆርሞን መዛባት(የመራቢያ ሆርሞን፣የጎይተር ሆርሞን)
-የአመጋገብ ሥርአት መዛባት(በጣም ቀጭን ለመሆን ራስን ማስራብ፣ካልሲዬም ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ

ምን ላድርግ?

♠መቼ ወደ ህክምና ልሂድ?
-ከቤተሰብ ውስጥ በአጥንት መሳሳት ምክንያት የዳሌ ስብራት ተከስቶ ከነበር
-የወር አበባ ከ45 እድሜ በፊት ከቀረ
-እድሜ ሲገፋ ወንድ ከ70 ዓመት ሴት ከ50 ዓመት እድሜ በላይ
-የአጥንት መሳሳት ሊያመጡ የሚችሉ መድሐኒቶችን እየወሰዱ ከሆነ።

♠ምን ችግርን ያስከትላል?
-በቀላሉ የመሰበር እድል ከሌሎች ከፍ ያለ ይሆናል።
-የጀርባ አጥንት(Vertebral bone #)፣የዳሌ አጥንት ሥብራት፣የመዳፍና የክርን አጥንት ሥብራት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
-የዳሌ የአጥንት ሥብራትን ተከትሎ በሽተኛውን ለተጨማሪ እንገልትና ስቃይ ብሎም ቶሎ ካለረታከመ ለሞት ይዳርጋል።

♠እንዴት መከላከል ይቻላል?
-በሐኪም የሚሰጥን የቅድመ መከላከል ምክር ተግባራዊ ማድረግ
-የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
-የአመጋገብ ሥርዓትን ማስተካከል። በካልሲየምና በቫይታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ 

Comments (4)

Tilahun Getaneh
Jun 15, 2025

ጤና ይስጥልኝ፤ እባክዎን ጉልበቴ ሳጥፍና ስዘረጋ በተለይ ቁጭ ካልኩበት ስነሳ በጣም እቸገራለሁ።በመጠኑም የማቃጠልና የቁርጥማት ስሜት ይሰማኛል። ጅማቴም ይወጠርብኛል፤ ምን ማድረግ ይኖርብኛል??

Eyob undefined
Jun 24, 2025

Eyob undefined
Jun 24, 2025

ጤና ይስጥልኝ : እንዴት ነዎት? የጉልበት ህመም ብዙ ምክንያቶች አሉት ። ስንት ጊዜ ሆነው ህመሙ? እድሜዎት ስንት ነው? እብጠት አለው ወይስ ?ትኩሳት አለ?

Eyob undefined
Jun 24, 2025

ጤና ይስጥልኝ : እንዴት ነዎት? የጉልበት ህመም ብዙ ምክንያቶች አሉት ። ስንት ጊዜ ሆነው ህመሙ? እድሜዎት ስንት ነው? እብጠት አለው ወይስ ?ትኩሳት አለ?

Eyob undefined
Jun 24, 2025

ጤና ይስጥልኝ : እንዴት ነዎት? የጉልበት ህመም ብዙ ምክንያቶች አሉት ። ስንት ጊዜ ሆነው ህመሙ? እድሜዎት ስንት ነው? እብጠት አለው ወይስ ?ትኩሳት አለ?

SISAY SIYUM
May 21, 2025

WeCare Admin
May 21, 2025

Thank you Doctor!

null null
May 21, 2025

thank you doctor for sharing an important message.