ከመጠን ያለፈ ውፍረት በሽታ(obesity)
ከመጠን በላይ የሰውነት ስብ መከማቸት የሚያስከትል ውስብስብ በሽታ ነው። ከመጠን ያለፈ ውፍረት የውበት ሥጋት ብቻ ሳይሆን እንደ የልብ ህመም ፣ የስኳር በሽታ ፣ የደም ግፊት እና የተወሰኑ ካንሰሮች ያሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች ተጋላጭነትን የሚጨምር የጤና እክል ነው ፡፡
አንዳንድ ሰዎች ከመጠን በላይ ውፍረትን ለማስወገድ የሚቸገሩባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ከመጠን ያለፈ ውፍረት በዘር እንዲሁም ከአከባቢ፣ ከግል አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ምርጫዎች ጋር ተዳምሮ ይከሰታል።
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ምልክቶች
ከቁመትዎ አንፃር የሰውነትዎን ክብደት ለማስላት የሚያገለግለው ቀመር (BMI) 30 ወይም ከዚያ በላይ በሚሆንበት ጊዜ ከመጠን ያለፈ የውፍረት በሽታ አለ እንላለን። ይህን ፅሁፍ በመጫን የእርስዎን BMI መጠን ማወቅ ይችላሉ
| BMI | ክብደት ሁኔታ |
| 18.5 በታች | ከተገቢው በታች |
| 18.5-24.9 | መደበኛ |
| 25.0-29.9 | ከመጠን በላይ ክብደት(overweight) |
| 30.0 እና ከዚያ በላይ | ከመጠን ያለፈ የውፍረት በሽታ(obesity) |
መች ወደ ጤና ተቋም መሄድ አለብኝ?
ከውፍረት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የጤና ችግሮች የሚያሳስብዎ ከሆነ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ስለቀነስ እና ለመቆጣጠር የተለያዩ የተረጋገጡ የህክምና አማራጮች ስላሉ ለእርስዎ የሚሆንዎትን ለማረጋገጥ ሀኪምዎን ያነጋግሩ፡፡
መጠን ያለፈ ውፍረት መንሰኤዎች
ምንም እንኳን በሰውነት ክብደትዎ ላይ የዘር ፣ የባህሪ እና የሆርሞን ተጽዕኖዎች ቢኖሩም በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በተለመደው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ከሚቃጠሉት የበለጠ ካሎሪ(calorie) ሰውነትዎ እነዚህን ካሎሪዎች እንደ ስብ በማከማቸት ውፍረት ያስከትላል።
ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው ሰዎች ከመጥገባቸው በፊት ብዙ ሊበሉ ፣ ቶሎ የረሃብ ስሜት ሊሰማቸው ወይም በጭንቀት እና በፍርሃት ምክንያት ከአስፈላጊ በላይ ሊበሉ ይችላሉ።
ከመጠን ላለፈ ውፍረት አጋላጭ ምክንያቶች
- ዘር እና የቤተሰብ ተጽዕኖዎች
- የአኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች
- ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ። ካሎሪ የበዛው እና በአትክልትና ፍራፍሬ የጎደለው የምግብ ስርዐትን ማዘውተር
- ፈሳሽ ካሎሪዎች እንደ የአልኮል እና ለስላሳ መጠጦች አብዝቶ መጠቀም
- እንቅስቃሴ-አልባ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ ካለዎት በየቀኑ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ማቃጠል የሚችሉትን ካሎሪዎችን በቀላሉ ወደሰውነትዎ ያከማቻሉ፡፡
- የተወሰኑ በሽታዎች እና መድሃኒቶች በአንዳንድ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንደ ፕራደር-ዊሊ ሲንድሮም(Prader Willi syndrome) ፣ ኩሺንግ ሲንድሮም(Cushing syndrome) እና ሌሎች የጤና እክሎች ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል በተጨማሪም እንደ አርትራይተስ() ያሉ የአጥንት ችግሮች እንቅስቃሴን ስለሚገድቡ ክብደት መጨመር ሊያስከትሉ ይችላሉ።
- አንዳንድ መድሃኒቶች ምግብ በመቀነስ ወይም በአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማርቆጣጠሩ ከሆነ ወደ ክብደት መጨመር ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህም መድሃኒቶች የተወሰኑ ፀረ-ድብርት መድኃኒቶችን ፣ የሚጥል በሽታ መድኃኒቶችን ፣ የስኳር በሽታ መድኃኒቶችን ፣ የአእምሮ መድኃኒቶችን ፣ ስቴሮይድ(steroid) እና ቤታ ብሎከሮችን(beta blockers) ያጠቃልላሉ ፡፡
- ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም ጤናማ ምግቦችን ለማግኘት እድል ከሌልዎ የሰውነት ክብደትዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል።
- ዕድሜ
- ከመጠን ያለፈ ውፍረት በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት ቢችልም ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ የሚመጡ የሆርሞን ለውጦች እና የእንቅስቃሴ ማነስ ለውፍረት የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ፡፡
- እርግዝና ከእርግዝና በኋላ ክብደት ለመቀነስ ጡት ማጥባት ተመራጭ ነው፡፡
- እንቅልፍ ማጣት
- ጭንቀት
- የአንጀት ባክቴሪያዎች (Microbiome)
ምንም እንኳን እነዚህ አጋላጭ ምክንያቶች ቢኖርዎትም በአካል ብቃት እንቅስቃሴ አመጋገብን በማስተካከል ወይም በባህሪያዊ ለውጦች ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መከላከል ይችላሉ።
ከመጠን ያለፈ ውፍረት መዘዞች
- የልብ ህመም
- ስትሮክ
- ዓይነት 2 የስኳር በሽታ
- የተወሰኑ የካንሰር አይነቶች የማህፀን ፣ የማህጸን ጫፍ ፣ የእንቁልጢ፣ የጡት ፣ የአንጀት ፣ የጉሮሮ ፣ የጉበት ፣የሀሞት ከረጢት ፣ የቆሽት ፣ የኩላሊት ካንሰር ተጋላጭነትዎን ሊጨምር ይችላል ፡፡
- የምግብ መፍጨት ችግሮች
- የማህፀን እና የወሲብ ችግሮች ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያላቸው ሴቶች መሃንነት እና የተዛባ የወር አበባ ሊያስከትል ይችላል። በወንዶች ላይ ስንፈተ ወሲብ ሊያመጣ ይችላል።
- በእንቅልፍ ወቅት ትንፋሽ ማጠር(sleep apnea)
- የአጥንት በሽታ(osteoarthritis)
- ከባድ የኮቪድ 19 ምልክቶች
- የህይወት ጥራት መቀነስ
- ድብርት
- የአካል ጉዳት
- ወሲባዊ ችግሮች
- ገለልተኝነት እና የጥፋተኝነት ስሜት
ከመጠን ላለፈ ውፍረት የሚደረግ ምርመራ
- ስለ ጤና ታሪክዎ የሚደረግ ቃለ ምልልስ
- አጠቃላይ አካላዊ ምርመራ
- BMI (ክብደትዎን ከቁመትዎ ጋር የሚያነፃፅር ቀመር)
- የወገብዎን ዙሪያ መለካት( waist circumference) ከ 89 ሴንቲ ሜትር በላይ የወገብ ዙሪያ ያላቸው ሴቶች እና 102 ሴ.ሜ በላይ የወገብ ዙሪያ ያላቸው ወንዶች ለተለያዩ የጤና እክል የበለጠ ተጋላጭ ናቸው
- ሌሎች የጤና እክሎችን ለመፈተሽ የልብ ምርመራዎች እና የተለያዩ የደም ምርመራዎች ይደረጋሉ።




