የጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ (ESSENTIAL NEWBORN CARE)

Elsabet Azezew
Feb 23, 2026
undefined

                                 የጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ (ESSENTIAL NEWBORN CARE)

ጨቅላ ህጻናት(Neonate) የምንላቸው በተወለዱ በመጀመሪያዎቹ 28 ቀናት ውስጥ ያለ አዲስ የተወለደ ህጻናትን ነው። 

በአለም አቀፍ ደረጃ በ 2019 የአለም ጤና ድርጅት ባደረገዉ ጥናት በአማካይ 2.4 ሚሊየን ህጻናት  በመጀመርያ አንድ ወራቸዉ ይሞታሉ ይህም ማለት በቀን እስከ 6700 ጨቅላ ህጻናት ህይወታቸዉን ያጣሉ።

ይህን የጨቅላ ህጻናት ሞት ለመቀነስ በእርግዝና ጊዜ ክትትል ማድረግ፣ በጤና ተቋም ዉስጥ መውለድና በድህረ ወሊድ ጊዜ ለጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ ማድረግ ዋነኞቹ ናቸዉ።

                             ለጨቅላ ህጻናት እንክብካቤ ለመስጠት የሚያስፍልጉ ነገሮች                                              

  •  በቂ ልምድ ያለዉ ጤና ባለሙያ(skilled birth attendant)
  •  መድሀኒቶች(antibiotics , vitamin k)
  • ክብደት መለኪያ ሚዛን
  • ሙቀት መለክያ መሳሪያ(thermometer)
  •  ሰአት መቁጠሪያ
  • ሞቃትና ጽዱ ማዋላጃ ክፍል
  • ጓንት
  • ፅዱና ለብ ያለ ዉሃ ዉስጥ የተነከረ ፎጣ ወድያዉ እንደ ተወለዱ አይናቸውን ለማፅዳት
  • አተነፋፈስን ለማስተከካል የሚረዱ መሳሪያዎች                                   
  • እትብት መቋጠሪያ                                                                                                              

                            ለጨቅላ ህጻናት የሚሰጡ ወሳኝ እንክብካቤዎች

ወዲያዉ እንደተወለዱ አተነፋፈሳቸዉን መመልከት ፦በራሳቸዉ መተንፈስ ያልጀመሩትን አፋቸዉንና አፍንጫቸዉን ማፅዳት።

የሰዉነታቸዉን ሙቀት መቆጣጠር ፦ያለምንም ችግር የተወለዱ ህጻናት ሰዉነታቸዉን በማድረቅ ከእናታቸዉ ጋር ሰዉነታቸዉን በማነካከት ሙቀታቸዉ እንዳይቀንስና ጡት ማጥባት እንዲጀምሩ ማድረግ።ችግር ያለባቸዉ ከሆኑ ደግሞ ወደ ሙቀት ክፍልና የተለየ እንክብካቤ ወደሚሰጣቸዉ ቦታ ይወሰደሉ።

የእትብት እንክብካቤ መስጠት ፦ ከተወለዱ ከ 1-3 ደቂቃ ዉስጥ በማሰር መቁረጥ። ምንም አይነት ባአድ ነገር እትብት አለመቀበት

ጡት እንዲጠቡ በመጀመርያ 1 ሰአት ዉስጥ ማስጀመር እና ለመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከእናት ጡት ውጪ  ሌላ ተጨማሪ ምግብ(ውሃንም ጨምሮ) አለመስጠት በ 24 ሰአት ዉስጥ ከ8 እስከ 12 ጊዜ ማጥበት አለበቸዉ ይህም ማለት በየ2 እስከ 3 ሰአት ልዩነት ተኝተዉም ከሆነ ተቀስቅሰዉ መጥባት አለበቸዉ።  የአይን እንክብካቤ፦ረጠብ ያለ ፎጣ(ፋሻ)በመጠቀም ከውስጥ ወደ ውጭ ማጽዳት እና ቴትራሳይክሊን ማድረግ·         

ክብደት መለካት ፦ትክክለኛ የክብደት መጠን የምንለዉ ከ 2.5 እስከ 4 ኪሎግራም ሲሆን ሲወለዱ የሚኖራቸው  ክብደት ማወቅ የተለየ እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸውን ህጻናት ለመለየት እና የሚሰጣቸውን መድሃኒት ለማስላት ይጠቅማል። የህጻናት ክብደት ሲወለዱ ከነበራቸዉ የክብደት መጠን በ 6 ወራቸዉ እጥፍ ሲሆን በ አንድ አመታቸው ሶስት እጥፍ ይሆናል። ይህን ማወቅ የምግብ እጥረት እንደለበቸዉና እንደሌለበችዉ ለመለየት ይረደል።       

ለደም መርጋት የሚያገለግል(vitamin k) ፦ መስጠት የእናት ጡት ወተት ለህጻናት እድገት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ንጥረ ነገሮች ከ ቫይታምን ኬ ዉጪ የያዘ ስለሆነ ቫይታምን ኬ መስጠት አስፈላጊ ነዉ ።

ጨቅላ ህጻናት መቼ መታጠብ አለባቸዉ፦ ጨቅላ ህጻናት ከተወላዱ ከ24 ሰአት በኋላ ለብ ባለዉሃ መታጠብ አለበቸዉ።

ክትባት መስጠት ፦ ጨቅላ ህጻናት ወድያዉ እንደተወላዱ የቲቢ(BCG) እና የፖላዮ(OPV) ይከተባሉ።የመጀመርያ ቀጠሮ በ 6ተኛዉ ሳምንት ወይም 42ተኛ ቀን፣ ሁለተኛ ቀጠሮ በ 10 ሳምንት ወይም 2 ወር ከ 2 ሳምንት፣ ሶስተኛዉ  ቀጠሮ በ 14 ሳምንት ወይም 3 ወር ከ 2 ሳምንት፣አራተኛዉ ቀጠሮ በ9 ወራቸዉ እና የመጨራሻዉ በአመት ከ ሶስት ወር ነው።

ጸሀይ መሞቅ፦ ህጻናት ከተወላዱ ከ 7 ቀን ጀምሮ ማሞቅ ፤ወንድ ከሆነ ብልታቸዉን በፎጣ ወይም በ ጨርቅ ነገር መሸፈን ያስፈልጋል እንዲሁም ምንም አይነት ቅባት ጸሀይ ከመሞቃቸው በፊት ሰዉነታቸዉን አለመቀበት።

  

                          ጨቅላ ህጻናት ላይ የሚታዩ አሳሳቢ ምልክቶች

  • ጡት መጥባት ሲያቆሙ፣ሲቀንሱ፣ሲያቆራርጡ·፣ እየጠቡ የሚያልባቸዉ ከሆነ        
  • በጣም የሚያለቅሱ፣ የሚነጫነጩ ከሆነ፣የሚያስምጣቸዉ ከሆነ፣ ሲሸኑ የሚያለቅሱ ከሆነ        
  •  ቶሎ ቶሎ የሚተነፍሱ ከሆነ(በደቂቃ ከ 60 ትንፋሽ በላይ ከሆነ)
  • ሙቀታቸው ከ 37.5 ዲግሪ ሴልሽየስ በላይ እና ከ 35.5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ከሆነ፣እትብት አካባቢ መቆጣት፣መቁሰል ወይም መግል መፍሰስ ካለ
  • እንቅስቃሴ ከሌላቸው፣ከደከሙ፣በተደጋጋሚ የሚያስመልሳቸዉ፣ የሚያስቀምጣቸዉ ከሆነ·       
  • ወይቦ(jaundice) ፦ ሰዉነታቸዉ፣ የእጃቸዉ መደፍ፣ ዉስጥ እግራቸዉ እንድሁም አይናቸዉ ቢጫ ከሆነ 

በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋማት እንዲሄዱ ማድረግ ያስፈልጋል።

Comments (0)