ምንነት
> ማጅራት ገትር በሽታ ማለት የአንጎልና የሰረሰር ልባስ ብግነት በሚኖር ጊዜ የሚከሰት ሆኖ በዋናነት የሰዉነት ሙቀት፣ ራስ ህመምና የንቃተ ህሊና መዛባት የሚያመጣና ማጅራትን ወይም አንገትን ገትሮ የሚይዝ በሽታ ነዉ፡፡
> ማጅራት ገትር በሽታ በብዛት ከ2 ወር የእድሜ ክልል በታች ያሉትን እና በህጻንነታቸዉ ክትባት ያልተከተቡትን ወጣቶች የሚያጠቃ ሲሆን ካልታከመ በቀር ገዳይ በሽታ ነዉ፡፡ ከታከሙት ዉስጥም እስከ 28% የአዕምሮ ጠንቅ(neurologic complication) የማምጣት አቅም አለዉ፡፡ ምናልባት ይህን ጠንቅ ህጻናትን በማስከተብና በሽታዉ በተከሰተ ጊዜ ቶሎ ህክምና በማግኘት ልንቀንሰዉ እንችላለን፡፡
መንስኤዎች
> በሽታ አምጭ ተህዋሲያን(ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች፣ ጥገኛ ተህዋሲያን፣ ፈንገሶች)
> የተለያዩ መድኃኒቶች(NSAID, IV IG)
> የጭንቅላት እጢዎች
አጋላጭ ነገሮች
> ህጻንነት ወይም በእድሜ መግፋት(ከ5 አመት ያነሰ ህጻን ወይም ከ60 አመት በላይ አባወራ)
> የተለያዩ ተጓዳኝ በሽታዎች መኖር(የስኳር በሽታ፣ የኩላሊቲ መድከም፣ የሳንባ በሽታ፣ የልብ በሽታ)
> በሽታ የመከላከል አቅም ደካማ መሆን(በኤዲስ በሽታ መለከፍ፣ ካንሰር)
> ሰዉ በበዛበትና በተጨናነቀ አካባቢ መኖር
> በተለያየ ምክንያት ጣፊያ ከሰዉነት በቀዶ ጥገና መዉጣት
> አልኮል ጠጭ መሆንና የጉበት በሽተኛ መሆን
> የአፍ፣ አፍንጫና ጆሮ በሽታ
> የጭንቅላት (ጉዳት፣ ቀዶ ጥገና)
> የጭንቅላት ዕጢ
> በደንብ ያልበለጸገ ጭንቅላት
> ተመሳሳይ በሽታ ካለበት ሰዉ ጋር ንክኪ መኖር
ምልክቶች
> የሰዉነት ሙቀት መኖር
> የራስና የአንገት ህመም
> የማጅራት መገታተር
> የንቃተ ህሊና መዛባት(መፍዘዝ፣ ግራ መጋባት፣ ማንቀላፋት ወይም ራስን መሳት ሊሆን ይችላል)
> ማቅለሽለሽና ማስመለስ
> ማንቀጥቀጥ
> ብርሀን መፍራት
> ጨቅላ ህጻናት ከሆኑ፡- የሰዉነት ሙቀት፣ ከፍተኛ የሆነ ቶን ያለዉ ልቅሶ፣ የባህሪ መለዋወጥና የእርግብግቢት (fontanelle) መነፋት ይኖራለ
ምርመራ
> የቃልና አካላዊ ምርመራ
> የደም ምርመራ፣ የኤሌክትሮላይት ምርመራ
> የአንጎልና የሰረሰር ፈሳሽ ምርመራ
> የኩላሊት ምርመራ
> የኤዲስ፣ የቲቢና የቂጥኝ ምርመራ
> የጭንቅላት ኢሜጂንግ
የበሽታዉ ጠንቅ
> የሰዉነት ፈሳሽ መሟጠጥ(shock)
> የልብ በሽታ
> ስትሮክ
> የቆዩ ነባር በሽታዎች ማገርሽት
> የጭንቅላት ግፊት መጨመር
> የሰዉነት ቅመሞች መዛባት(SIADH)
> የማንቀጥቀጥ በሽታ
> የጭንቅላት መምገል
ህክምና
> በደም ስር የሚሰጡ መድሃኒቶች
> የተለያዩ አጋዥ ህክምናዎች(የሙቀት ማስታገሻ፣ ግሉኮስ፣ ኦክስጅን፣ ጭንቅላትን ከፍ አድርጎ ማስተኛት)
> ሌሎች የበሽታዉ ጠንቆች ካሉ እነሱን ማከም
> ቀዶ ጥገና(መግል፣ ዕጢ… ካለ)
ምን እናድርግ?
× ማጅራት ገትር በቶሎ ካልታከመ ገዳይና ዘላቂ የሆነ ችግር የሚፈጥር ስለሆነ ከላይ የተጠቀሱ የበሽታዉ ምልክቶች ካሉ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መዉሰድ
× ከላይ የተጠቀሱ አጋላጭ ነገሮችን ማስወገድ
× በሀኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡና በትክክል መዉሰድ፣ የሚሰጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ
× የህክምና ክትትል ማድረግ
✍️ዶ/ር ኢዮብ ባየህ(ጠቅላላ ሀኪም)



